"በቀኃሥ ዘመነ መንግስት ወቅት፤ የሠራዊቱ ልሳን በመሆን ያገለግል የነበረው ጋዜጣ ስሙ "ወታደርና ዓላማው" ይባል ነበር።
"በቀኃሥ ዘመነ መንግስት ወቅት፤ የሠራዊቱ ልሳን በመሆን ያገለግል የነበረው ጋዜጣ ስሙ "ወታደርና ዓላማው" ይባል ነበር።
ይህ ጋዜጣ በደርግ ዘመን ስሙ "ታጠቅ" በሚል ተቀይሮ እስከ ግንቦት 1983 ዓ.ም. ድረስ የሠራዊቱ ድምፅ በመሆን አገልግላል።
እዚህ ጋዜጣ ላይ የምትመለከቷቸው የወቅቱ የኢትዮጵያ ሰራዊት ከፍተኛ የጦር አዛዥ መኮንኖች በግርማዊ ቀኃሥ ሹመቱ የተሠጣቸው፤ በ1954 ዓ.ም. ላይ የነበረ ሲሆን፤ ዜናው በወቅቱ "በልዕልት እቴጌ መነን" እና "የልዑል ሳህለሥላሤ" የሞት ሀዘን ምክንያት ዘግይቶ "በወታደርና አላማው" ጋዜጣ ላይ የወጣው ከአመት በኃላ ጥቅምት 24/1955 ዓ.ም. ነበር።
በወቅቱ ከሜጀር ጀነራል እስከ ኮሎኔል የማዕረግ እድገት ያገኙት የጦር መኮንኖች የሚከሉት ናቸው።
1. ሜ/ጀ እያሱ መንገሻ፤
2. ሜ/ጀ ዋቅጅራ ሰርዳ፤
3. ሜ/ጀ ወልደስላሴ በረካ፤
4. ሜ/ጀ አማን ሚካኤል፤
5. ብ/ጀ ጃገማ ኬሎ፤
6. ሌ/ጀ ኢሳያስ ገ/ስላሴ፤
7. ብ/ጀ አበበ ገመዳ፤
8. ብ/ጀ ወልደዮሃንስ ተክሉ፤
9. ብ/ጀ ሽፈራው ተሰማ፤
10.ብ/ጀ አበበ ተፈሪ፤
11.ብ/ጀ ኃይሌ ባይከዳኝ፤
12.ብ/ጀ ወልደዮሐንስ ሽታ፤
13.ብ/ጀ አበበ ወልደመስቀል፤
14. ኮ/ል ይልማ ሺበሺ፤ መሆናቸው ጋዜጣው አስፍሯል።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ