ዕውነት #ጋራጅ #የለውም። #የአማራ #የማንነት #ተጋድሎ፦ 2) #የአማራን #የህልውና #ተጋድሎን ውስጥ ማድረግ ይገባል።
#ጤና ይስጥልኝ።
ትናንት ጦር ግንባሩ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ነበር።
ካቴና ላይ ያሉ ወገኖቻችንም ይታወሱ። የተፈቱም ይኖራሉ።
መሬት ላይ ትክክለኛ ዘጋቢ ስለለ ነው። ቢፈቱም መልሰው ያስሯቸዋል። ልቀቁ ነው። እዬለቀቁላቸው ነው። በውነቱ ለእስረኛ #ሙግት ቀርቷል። እንደ ነውርም እዬታዬ ነው።
ሲያነክተን ውሎ በሚያድር የምጠዬፈው "#የሰበር ዜና" ቁምነገር የማሳት አቅሙ ልክ የለውም። የሰበር ዜና ሚዲያው ወዘተረፈ እንደ ሥልጣኔም የታዬ ይመስለኛል። ነርብን፤ ካርቲሌጅን የሚሰባብር ።
ብዙ ወገኖቻችን እንዳጣን ይሰማኛል። ብዙወቹ የእኔ ቅኔው ጎጃም ነበሩ።
እስካሁን አልመጡም። እንጃ ኢንተርኔቱ ካልተሟላ አላውቅም።
ቸር ያሰማን። ቸር እንሁን። ቅንም እንሁን። ቢያንስ ለተጎዱ ወገኖቻችን #ስስ አንጀት ይኑረን።
ትናንት ሙሉ ቀን ፌቡ የዋልኩት ህዳር ከታጠነ ወዳጆቼን አገኛለሁ በሚል ነበር።
#የገዘፈውን … ጣምራ የተጋድሎ አመክንዮ አንኳር አጀንዳ ይሁን። ማህንዲሱም፤ ፓስተሩም ስለተበራከተ እንጂ ብዙ እጅግ ጥንፍ ተጋድሎ አማራን ይጠብቀዋል። ዛሬ ይህ ከሆነ የዛሬ 15/20 ዓመት ይታሰብ። እኔ ብቻም ነኝ የትግሉ ዘርፍ በዚህ መልኩ የማቀርበው።
2) #የአማራን #የህልውና #ተጋድሎን ውስጥ ማድረግ ይገባል። እያገረሸ የሚፈትነን የቀራንዮ ሥነ ስቅለት እያለብን በሰናፍጭ ጉዳይ አቅም አናባክን። ሊቃናቱ ይገናኛሉ። ማገዶነታችን በልክ ይሁን። ሁሉም ጥሞና ቢወስድ መልካም ይመስለኛል።
"የቤትህ ቅናት በላኝ። "
ሸበላ ቀን። ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉትሻ 2024/07/18
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ