ልጥፎች

ከኖቬምበር 16, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የዶር. ደብረጽዮን "አንጠልጥለን እንሰጣለን?"

ምስል
የዶር ደብረጽዮን „አንጠልጥለን እንሰጣለን“ ከምላስ        ወይስ ከአንጀት ተረቡ? „ከቁጣው ጢስ ወጣ ከፊቱም የሚባላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ በራ።“ መዝሙር ፲፮ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ  16.11.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።                               ዘመን ሲሰጥ። እንዴት አላችሁልኝ ውዶቼ? ትናንት አንድ ዜና ሽው አለኝ እና የውነት ይሆን ብዬ ስፈታትሽ እውነት  ነው ተባለ። ዶር ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ከህግ በላይ ማንም ስሌለ አንጠልጥለን እንሰጣለን በእነሱ ሥማችን አይጎድፍም ማለታቸው ነው የተደመጠው እድምታው በትርጉም ሲቃና። ግን ይህ የአፍ ወለምታ ነው ወይንስ የልብ? እኔ አኮ እውነት ተናገሪ ብባል ዶር ደብረጽዮን በራሳቸው ፈቃድ ራሳቸው ጠይቀው አባታችን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቀሪዮስን ሄደው በአካል ሲጠይቁ ከህሊናቸው ጋር ምህረት አውርደዋል ብዬ ነበር። በረከት ይዘው ተመልሰዋል፤ ተባርከዋል፤ ተቀድሰዋል፤ ምርቃታቸውን ሳያባክኑ እንደ ሰው ተፈጥሮ ይሆናሉ የሚል ሙሉ ዕምነት ስለነበረኝ በሐሴት ራሱን አስችዬ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ታዲያ ምን ይሆናል ከዛ ከተባረከው ተግባራቸው ማግስት እትጌ ትግራይ ጎራ ሲሉ ያው የለመደበዳቸውን ፉከራ ቀጠሉ፤ ይባስም ብሎም በራያ ሌላ ደም ፈሰሰ። እናም ደነገጥኩኝ። በወቃይትም ሌላ ርግጫ ቀጠለ። በውነቱ እኔ ነገሮችን በቅንነት ስለማይ እግዚአብሄር ፈቅዶ ነው ይህን መልካም ነገር ሊያደርጉ ያነሳሳቸው ብዬ አስቤ ሰልነበር ከዛ ከቀደመው ትዕቢታዊ ጭካኔ ጋር ይፋታሉ የ...