አቶ ፍጹም አረጋ ከሃላፊነታቸው ተነሱ።
አዲስ የፕሬስ ሴክረታሪ ለውጥ በጠ/ሚር ጽ/ቤት። „አቤቱ በልቤ ሁሉ አመሰግንህ አለሁ። ተአምራትህንም ሁሉ እናገራለሁ።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ 05.11.2018 ከገዳማዊቷ አገር ከሲዊዝ። በአዲሳዊነት ቀመር ፋታ ሳይሰጥ እዬገሰገሰ ያለው የጥጋናዊ ለውጥ ማዕበል ዛሬ ደግሞ አዲስ ነገር እያሰደመጠን ነው። አንዱንም በቅጡ አጣጥመን ሆድ ዕቀውን ዛረጋግፈን ፈትሸን ሳንቃኘው በዬዕለቱ በአዲሳዊነት መርህ ግብር ወደ ፊት የሚገሰግሰው የለማ አብይ ካቢኔ አሁን አዳምጡኝ እያለን ነው። በፎቶ በተደገፈ አጫጭር መረጃዎችን በማዕከልነት ሲያሰተናግዱ የቆዩት አቶ ፍጹም አረጋ በሌላ መተካታቸውን አዲስ ዜና እያደመጥን ነው። "ከአረጋ" ሥያሜ አንድ ቀነሰ እንደ ማለት፤ አቶ ፍጹም "አረጋ" አቶ አዲሱ አረጋ አቶ ዳዊት "አረጋ።" የሆነ ሆኖ እርእሱ እንዲህ ይላል። „Ethiopia:ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ስር የተቋቋመው የፕሬስ ሴክሬታሪ በይፋ ስራ መጀመሩን አስታወቀ“ ማድመጡን ትንታኔውን ለእናንተው የቤት ሥራ ሰጥቼ ሥርጉትሻ ሹልክ … https://www.youtube.com/watch?v=rBfiQz1fH0Q ሰላም ሲሆኑበት ችግርን የመፍተት አቅሙ አንቱ ነው። መሸቢያ ጊዜ። ትሁት አካባሪያችሁ።