ልጥፎች

ከጁላይ 28, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

... ወጣትነት እና እኔ ሳንገናኝ ተላለፍን …

ምስል
ስንጥቅ ስንጥሩ በአግባቡ ይፈተሽ። (ከስምንት ዓመት በፊት የተፃፈ ለህትምትም የበቃ።) “ አቤቱ፣ በልቤ ውስጥ አመሰግንሃለሁ፣ ታአምራትህንም፡ ሁሉ እናገራለሁ። በአንተ፣ ደስ፡ ይለኛል፣ ሐሤትንም አደርጋለሁ።“ ( መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፱ ቁጥር ከ፩ እስከ ፪) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 28.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ) የኔዎቹ ይህ እ.ኢአ. በ2002 ከታተምው “መክሊት” የግጥም መድ ብ ል ላይ ያለነው። ዛሬ ላይ ሳነበው ግርም ብሎኝ ገጹንም ቁጥሩን ከነተፈጥሮ ሳላዛባ ነፃነቱንም ሳልነፍግ፤ ሳድስ ላይ ግድፍት ሁልጊዜ አለብኝ እና እሱን ብቻ አርሜ ለዛሬ ብያለሁኝ። ግጥሞቼን ስከውን ማሳሪጊያ ያደርኩት የወግ ገበታ ነው። እርእሱ  “ስንጥቅ ስንጥሩ በአግባባቡ” ይፈተሽ ይላል። ይሄ ዛሬም ለጠ/ አብይ አህመድ ካቢኔ የሚያግዝ ዕይታ ጭምር ነው። ያግኙት አያግኙት ጹሁፌን አላውቅም። የወንጌል ጥቅሱም መጸሐፍቴ ሲጀመሩ ሁልጊዜ ወንጌል ስላለበት መግቢያውን እሱን እንዳለ ወስጄዋለሁኝ። በተረፈ መልካም ቆይታ ከ2002 ዕይታዬ ጋር። ያ ዕይታ እና ዛሬ ሃዲድ የመስራት የእናንተው የ እኔዎቹ የውዴቼ ተግባር ይሆናል። ስሜቴን ሰብስቤ ለመጻፍ አቅም አጣሁኝ። ዜግነት በተማላ እንደላ ብቻውን ዘነዘናውነን ቁሞ ይታዬኛል። ዜግነቴ አረፈ ስል በመዲና ላይ በጠራራ ጸሐይ ካለ ጠበቂ፤ ካ ለ አንዳች ጠያቂ እንዲህ ሲሆን ለእኔ መራራ ሃዘን ነው። እኔ መጻፍ አቅቶኝ አያውቅም፤ ልክ ባንቧ ውሃ የመክፈት ያህል ነው። አሁን ግን አልቻልኩም ስለዚህ ነው ወደ ቀደሙት መሄድ ግድ ያለኝ። እንደ ማሰረጊያ …  መክሊተ መጸሐፈ የግጥም ስብሰብን ዕሴት።                   ስንጥቅ ስንጥሩ በአግባቡ ይፈተሽ። እዬራቀ