... ወጣትነት እና እኔ ሳንገናኝ ተላለፍን …

ስንጥቅ ስንጥሩ በአግባቡ ይፈተሽ።
(ከስምንት ዓመት በፊት የተፃፈ ለህትምትም የበቃ።)

አቤቱ፣ በልቤ ውስጥ አመሰግንሃለሁ፣ ታአምራትህንም፡ ሁሉ እናገራለሁ።
በአንተ፣ ደስ፡ ይለኛል፣ ሐሤትንም አደርጋለሁ።“
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፱ ቁጥር ከ፩ እስከ ፪)
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 28.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)



የኔዎቹ ይህ እ.ኢአ. በ2002 ከታተምው “መክሊት” የግጥም መድል ላይ ያለነው። ዛሬ ላይ ሳነበው ግርም ብሎኝ ገጹንም ቁጥሩን ከነተፈጥሮ ሳላዛባ ነፃነቱንም ሳልነፍግ፤ ሳድስ ላይ ግድፍት ሁልጊዜ አለብኝ እና እሱን ብቻ አርሜ ለዛሬ ብያለሁኝ። ግጥሞቼን ስከውን ማሳሪጊያ ያደርኩት የወግ ገበታ ነው። እርእሱ  “ስንጥቅ ስንጥሩ በአግባባቡ” ይፈተሽ ይላል።

ይሄ ዛሬም ለጠ/ አብይ አህመድ ካቢኔ የሚያግዝ ዕይታ ጭምር ነው። ያግኙት አያግኙት ጹሁፌን አላውቅም። የወንጌል ጥቅሱም መጸሐፍቴ ሲጀመሩ ሁልጊዜ ወንጌል ስላለበት መግቢያውን እሱን እንዳለ ወስጄዋለሁኝ።

በተረፈ መልካም ቆይታ ከ2002 ዕይታዬ ጋር። ያ ዕይታ እና ዛሬ ሃዲድ የመስራት የእናንተው የ እኔዎቹ የውዴቼ ተግባር ይሆናል። ስሜቴን ሰብስቤ ለመጻፍ አቅም አጣሁኝ። ዜግነት በተማላ እንደላ ብቻውን ዘነዘናውነን ቁሞ ይታዬኛል። ዜግነቴ አረፈ ስል በመዲና ላይ በጠራራ ጸሐይ ካለ ጠበቂ፤ ለ አንዳች ጠያቂ እንዲህ ሲሆን ለእኔ መራራ ሃዘን ነው። እኔ መጻፍ አቅቶኝ አያውቅም፤ ልክ ባንቧ ውሃ የመክፈት ያህል ነው። አሁን ግን አልቻልኩም ስለዚህ ነው ወደ ቀደሙት መሄድ ግድ ያለኝ።



እንደ ማሰረጊያ …  መክሊተ መጸሐፈ የግጥም ስብሰብን ዕሴት።                  


ስንጥቅ ስንጥሩ በአግባቡ ይፈተሽ።

እዬራቀ መሄዱ ግራ ሳይሆን ቀኝ ይመስለኛል። አሰልችነቱም ግራ ሳይሆን ቀኝ ይመስለኛል። አዳካሚነቱም ግራ ሳይሆን ቀኝ ይመሰልኛል። ይመስለኛል መብዛቱ ጭብጡ በጥናታዊ መረጃ፣ በቁጥር ምን ያህል እጁ ሚዛን እንደ ደፋ የምርመር ሥራ ስለ አልተከወነበት ነው። ለነገሩ ለግል ነፃነት ተንታኝም፣ በታኝም፣ ሳይንቲስትም አያሰፈልግም። ስለ ምን? የኦክሰጅን መተላለፊያው ሲዘጋም ሆነ ሲከፈት የሚያውቀው ተጠቃሚው ወይንም ባለቤቱ ነው እና።

ከአቅም በላይ በሆኑ፣ በእጅ በማይከወኑ ጉዳዮች ዙሪያ ግራ ነው ማለት ይቻላል። ነገር ግን በመዳፍ በአለ በዓይን ወስጥ በሚገኝ ወይንም በሚዳሰስ፣ በሚጨበጥ ጉዳይ ላይ የሚፈጸሙ ግደፈቶች ሁሉ ግን ግራ ሳይሆኑ ተፈቅደው እና ተወደው የሚከወኑ በመሆናቸው ቀኝ ናቸው። (በማወቅም ይሁን ባለማወቅ)

1.               አንድ ሰው በቅድሚያ ለነፃነቱ ጠላት የሆነውን አካል፣ የጠላትነቱን የፍላጎተ-ዒላማ, በሚገባ ማወቅ ያሰፈልገዋል።

2.               ጠላቱን ለማጥቃት፣ የራሱን የውስጥ ፍላጎቱ በማይናወጽ መሰረት ላይ በውስጡ እንደ ጽላት መተከል ወይንም ማዋቀር አለበት። ወይንም እንደ ተክል በውስጠ-ወስጡ ማልማት ወይንም ማብቀል አለበት።

3.               በልቡ የጠላቱን- ጠላትነት፣ አምኖ መቀበል ብቻ ሳይሆን፣ የጠላቱ መርዝ ምን ያህል እንደ ጎዳው መመርመር አለበት፣ መለካትም። አብሶ በመንፈሳዊ ዕሴቶች ላይ በበቂ ሁኔታ ህመሙ ያሰከተለውን ጠባሳ ማጤን ይኖርበታል-በእጅጉ።

4.               ጠላቱ፣ ጠላት ስለ መሆኑ ያረጋገጠባቸውን ጭብጦች በሚገባ በልቡ መዝግቦ፣ በደሉን ከራሱ ጋር መጋባት አለበት። ሕሊናው ሙሉዑ ለሆነ ሰው በደሉ ይጠዘጥዛል፣ ይቆጠቁጣል። ያንጊዜ ይቆርጣል። ይወስናል።

5.               ትናንትን፣ ዛሬን፣ ነገንም በማስማማት የበደሉ ቅሪት ሊያሰከትል የሚችለውን ዘርፈ ብዙ ግጠቶችንም ማጥናት፣ በተናጠል እና በጋራ በሚገባ ማገናዘብ። ተወራራሽ እና ተዛማጅ ወይንም ንኪኪ የሌላቸውን ክስተቶች ሳይቀር በአግባቡ መዝኖ፡ በትኖ፣ በረድፍ-ረድፍ አደራጅቶ፣ ለተግባሩ ቅደም ተከተል ቢያንስ በሕሊናው ማሰናዶውን ማሟላት አለበት።

6.               ከእራሱ ጋር ሳይተላለፍ፣ እራሱን ለማግኘት በፍላጎቱ ውስጡ “እራሱ” የጉዳዩ ባለቤት መኖር መቻል አለበት።

7.               በመጨረሻ የጠላቱን ዘላቂ እና ጊዜያዊ ፍላጎት በማሰተዋል መርምሮ፤ ነገን አስልቶ፣ ጥቃቱን ሊመክት ከሚችልበት ሁነት ጋር ውስጡን አስማምቶ፣ የራሱን ድርሻ መወሰን እና መንቀሳቀስም ይኖርበታል።

በዚህ ስሌት ስንሄድ በአመዛኙ የተከወነ ይመስለኛል። ጠላታችን እናውቃለን። የጠላታችን ፍላጎት መነሻም ይሁን መድረሻ በሚገባ አበጥረን እንገነዘባለን።

ስለሆነም ሳሰተን ነፃነታችን እንፈልጋለን። እሰከዚህ ድረስ ሁሉ የሚቆርብበት ጉዳይ ነው። ችግሩ ያለው ጠላትን ለማጥቃት ከመንቀሳቀስ በፊት የራስን ድርሻ አለማወቁ ላይ ይመስለኛል። ከሁሉም በፊት በዓብዩ ፍላጎታችን ውስጥ እኛ እራሳችን ከነሙሉ ጸጋችን በትክክል መኖር አለብን። ፍላጎታችንም በበኩሉ እኛ በውስጡ መኖራችን ማረጋገጥ ይኖርበታል። መንገድ እንዳይጠፋብን መሪያችን እሱ ነው እና።  ግን እንችላለ --- ን?

ገፅ …. 240

ነገር ግን ችግር አለፍላጎታችን በልባችን እንደ ጽላት በቋሚነት ቦታ አልሰጠነውም። ስለሆነም የቋሚው ፍላጎታችን ዕጣ ፈንታ በተለያዬ ምክንያት ሲዘም ወይንም ወጀብ ዋክበው፤ ጓዝ ጥቅለላ ይሆናል።

በሌላ በኩል ደግሞ በመሬት ላይ በአለው የመኖር እና አለመኖር መሰረታዊ ጉዳይ ሳይሆንላሜ ወልዳ ጥጃው ከዬት ይታሰራል ነው?“ ውርክቡ መጀሪያ ላሟ መኖር አለባት። ቀጣዩ መሰረታዊ ጉዳይ ደግሞ ላሟ እንድትወልድም የሚያግዛት ሥነ-ተፈጥሯዊ ሁነቶችም መሟላት አለባቸው። ይህ በሌለበት መቼም ላም አታረግዝም፣ ብትኖርም መሲና ልትሆን ትችላለች

በጣም ወሳኙ ጉዳይ ደግሞ ራስን ታግሎ ሳያሸንፉ ነው ጠላትን ለማጥቃት የሚቃጣው። ይህ ደግሞ በር እያለ በጣሪያ ለመግባት መታገል ይመስለኛል። በውስጣችን ያልፈታነው ጥቅል፣ የተቆጣጠረ ችግር አለ። የታመቀ፣ ያልተማሰለ፣ የተከደነ፣ የሚያምሰንእኔ በግሌ የመዳህኒዓለምን ሥልጣን ሳልጋፋ የኢትዮጵያ ትንሣኤ በጣም እርቆ ነው የሚታዬኝ። አንድ ሰው እራሱን ለመተካት ከራሱ የተሻለውን እለፈኝ ለማለት እስካልደፈረ፣ የሚበልጠውን አግዞ እና ደግፎ የጋራ ፍላጎትን ለማሟላት እስከ አልተጋ ድረስ፣ ያለው ትብትብ መፍቻ ምን ሊሆን እንደሚችል ፈጣሪ አምላክ ይወቀው።

የሚበልጥ ወገን እኮ አንጡራ ባላንጣ ነው! ጦር ይታወጅበታል፣.. እርቃኑን እንዲቀር መሳሪያ ይቀባበልበታል፣ የሰበሰበውን፣ የደከመበትን፣ ዕድሜ ለዚህ የሥልጣኔ ዘመን በአንድ ጀንበር ማቅ ይለብስበታል። ለተጋ ወገን እግዚአብሄር ይስጥህ፣ አንተ ይህን ሸፍነሃል እኔ ደግሞ በምን ልገዝህ የለም፣ የሽታ ሽቶሽ መከትከት። ሽንፈት ሲመጣ ደግሞ በጋራ መቆዝም። ደም የሚያሰቀምጠው ፊት-ለፊታችን ያለው መራራ ሀቅ ይህ ነው።

ደማችን ወጥቶ አዲስ ደም ቢቀዬር ከቶ ይታደገን ይሆን?! በዚህ ወጣ ገባ ባህሪያችን የኢትዮጵያ የደም ዕንባ አንደበት ቢኖርው ለሰማዩ ዳኛ ይከሰን በነበር. ፍርድ እንዳይርቅም ይማጸነው ነበር። ከዚህ ላይ አንድ ምሰሌ ባ’ነሳ ደስ ይለኛል

. ግማሽ ጣሳ ላይ አፈር አድርጉ፤

. ውሃ ጨምሩበት እና በቅጡ ከተዋህደ በኋዋላ ባቄላ ትከሉ፤

. በምቹ የአዬር ጸባይ ሳታውኩት፣ ሰላም ሰጥታችሁ አደላድላችሁ አስቀምጡት፤

ከዛ ከተወሰነ ቀን በኋላ ባቄላው ይበቅላል። አፈሩ ግማሽ ነው ብያለሁ፣ከበቀለ በኋዋላ በቀረው ክፍት ቦታ ላይ አፈር ሙሉበት እና ከተሰማማማው ቦታ አንስታችሁ ጨለማ ውሰጥ አስቀምጡት። ምን ይሆናል? ጥያቄና መልስ አያሻውም፣ ይሞታል፣ በቃ! የኛ የትግል ስልትም ይህው ነው። አገላለጹ ሊመር ይችላል፣ ግን አፍጥጦ የሚታዘበን የሃቅ እንክብል አስኳሉ ይህ ነው።

እና መራራውን እናጣጥመው። ሀሞት በፈቃድ ከሆነ ይጥማል አይደል ….?

የወጣው አዲስ ቡቃያ ማፍራት ቀርቶ ሲበቅል ዬልምላሜው ቀለሙ ለዓይን እንዴት ደስ ያሰኛ ነበር። ትንሽ ዘለግ አስኪል ድረስ እንኳን ከብዙ ነገሮች መታቀብ በእጅጉ ይሳነናል። አቅል እናጣለን። የኢትዮጵያዊነታችን አንዱ መላያችን ትእግስት ነበር፣ ግን ማን በላው ይሆን? ቡቃያው እንዲያሰደስት ትንሽ ከፍ ብሎ እንድናዬው እንኳን አንሻም። …. በፍጹም።

እንኳንስ አሰኪያፈራ ልንጠብቅወይ ጉድ! ድርቅ ሲመታው ሐሤታችን ነው። መሥጥረን ይፋ ሳናደርገው፣ በውስጣችን እንደሰታለን። ይህ ገሃድ ነው። በገዛ አካላችን ሽንፈት፣  ሆነ ፍርድ ተጣኖ፣ ሚዛን በወያኔ ሲያለቅስ፣  ትችትም ወቃሳም አለበት …. ግን መንፈሳችን ፈቅዶልን ይሆን ወይንስ ተጭነነው?

ገፅ … 241


ሌለው መልካም ነገር ለምቶ ማዬት ለዓይናችን ጤናው ሳይሆን በሽታው ይመስለኛል። ይህም እውነት ነው። እኛን የሚንገበግብን የባለቤትን፣ የሥም፣ የዝና ጉዳይ እንጂ የእልፍ ደም ዕንባ ጥግ ማጣት አይደለም። ይህ እንግዲህ ከሊቅ እሰከ ደቂቅ አብዛኞቻችን የምንታመስበት  በሽታ ነው። ሁሉ ልጅ ሲወለድ መክሊት ይዞ ነው የሚወለደው። እያንደንዱ ልጅ ያለው መክሊት ደግሞ እንደ እጅ ሆነ እንደ እራስ አሻራ የተለያዬ ነው ….
ሁሉም ባለ ሃብት ነው። ነገር ግን ያለውን ሃብት በአግባቡ ጥቅም ላይ ለማዋል ግልኝነት አንቱ ብሎ ባሪያ አድርጎ ውስጣችን ካለተቀናቃኝ እዬገዛን ነው። ታዲያ በምን ታልፎ ነው የብዙኃኑ መክሊት ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለው? ስለሆነም፣ ደክመው …. ደክመው፣ የታከታቸው ወገኖች በቃኝ ተሰናብተው፣ ከቻሉ የግል ጥረታቸውን በተናጠል፣ ሳይችሉ ወይንም መንገድ ሲታጠርባቸው ደግሞ እህህን እያማጡ፣ ከትግሉ ጎራ ያለ ይግባኝ አምጠው ይሰናበታሉ።

…. እና እንዴት እና እንዴት ተብሎ ነው በእኛ የእንቅስቃሴ አድማስ፣ ከጥንካሬያችን ሆነ ከድክመታችን እየተማረ፣ ሌት እና ቀን እዬሠራ፣ ሰነሰለቱን እያጠበቀ፣ የአገዛዘዝ ዘመኑን እኛን በእኛ እዬገደለ ያለውን አሰተዳደርን ወያኔን መገላገል የምንችለው?! የወያኔ የትግል ስልት እኮ በፍጹም ትጋት እና በሙሉ ኃይል (Incentive and Intensive) ነው።

በእውነት አብዛኞቻችን ፍላጎታችን ርቀነዋል።  እና ለእኔ የድል ቀን ሩቅ ነው። እንደ አራቅነው ፍላጎት። ስለሆነም ይህ ለእኔ ግራ አይደለም። ፈልገን ስለ ምናደርገው ቀኝ ነው። ስንጥር ስንጠቁ ሁሉ በአግባቡ በተደሞ ሊፈታተሽ ይገባል። የእኛው ጠላት ወያኔ ብቻ ሳይሆን እኛም ነን።

በተጨማሪ የሴቶች ጸጋ በሙሉ ቀን የተፈጠረ ነው ብል ማገነን አይሆንም። ተዘርዝሮ ፈጽሞ ማለቂያ የለውም። ሴቶች ሁሉንም ናቸው። ታዲያ ለሴቶች ያለው አክብሮት ከአንደበት ያለፈ አይደለም። ሰፈ እጅ፤ መጠነ ሰፊ ዕውቀት፤ ብቃት፣ ኃይልም ከእናትነት ልዩ መክሊት ጋር የተቸራቸው፣ የማድረግ አቅማቸው ሙሉዑ የሆኑት ሰፊ የህብረተሰብ ክፍሎች ተዘለው ነው ሁሉ ነገር የሚወጠነው። ታግለው ቢወጡ እንኳን የወጡባትን ዕለት ሳያከብሩ በጨፈቃ ይዳፈናሉ

እንዲሁም የወጣቶች ተሳትፎንም ስንመለከት የሚሰጠው አትኩሮት እጅግ አናሳ ነው። ዕድሜም እኮ ሌላው ቅምጥ ሀበት ነው። ብዙ አስተዋጾ አለው። ወጣትነት በራሱ የባለ ሙሉ ትጥቅ እና ስንቅንት ልዩ ጸጋም ነው። በሌላ በኩልም ወጣትነት ገዢ መሬት ላይ ያለ አጥቂ ሠራዊት ማለት ነው።

በእነርሱም ለመጥቀም፣ ለመተካት ሆነ አምሳያን ለመፍጠር፣ ያለው ጣምራ ቀርቶ ቀንጣዊ ጥረትም ደብዛዛ ነው።. ነገ የእኛ አይደለም። ነገ የእነሱ አንጡራ ሃብታቸው ነው። ነገን ለእነሱ ለመስጠት ያለው ፈቃደኝነት ደግሞ ዝግ፣ የተቆለፈ. ይህ እንግዲህ … “ሁሉን ነገር በቀጥታና በንፁህነት ለሚያይ የወጣትነት እድሜ” (ከጸሐፊ ዶር. ብርሃኑ ነጋ ጎህ ሲቀድ፣ መግቢያ ላይ ገጽ 7) ሰሜቴን ያገኜ አገላለጽ ነው።

በእያንዳንዱ የእንቀስቃሴ ቀለበት ውስጥ ቀንበር አለ፣ የማያፈናፍን የብረት ካቴና። ጠላት የሚፈጥርው ብቻ ሳይሆን እራሳችን የምንፈበርከው። በእያንዳንዱ የተግባር ቀን ላይ ማዕቀብ አለ፣ ጠላት የጣለብን ብቻ ሳይሆን እኛው የምናሽሞነሙነው - ሙጃ።

በእያንዳንዱ የብቃት መጠን ላይ ሚጢሚጣ አዘል ትቢያ ይበተንበታል፣ ጠላት የሚያደርገው ብቻ ሳይሆን እኛም እራሳችን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በምንሰነዝረው ጥቃት በመርዝ የተሸበለለ። በእያንዳንዱ የቅንነት እንቅስቃሴ ላይ ስውር የሸር ሽቦ አለ፤  ታዲያ በምን ስሌት ነው የዕንባን ጥሪ ተጋርቶ የድርሻን መወጣት የሚቻለው!?!


ገፅ …. 242

ሁሉንም ነገር ሳናርቀው ከራሳችን ጋር አቀራርበን እናስተያያው። ምን እያደረግን እንደ ሆነ እንፈትሸው?! ገና ነን በጣም ገና ነንላይ ላዩን ሳይሆን፣ ሥረ መሰረታችን፣ ውስጣችን እንመርመር፣ እንገስጽ፣ እንረም፣ ሌላ ሃያሲ አንጠበቅ። ይህን ብናደርግ ማሸነፋችን ያለ በመዳፋችን ውስጥ ነው።

ምን የሌለን ነገር ከቶ አለ እና?! ወያኔ እና እኛ እኮ በተመሳሳይ ትውልድ የምንገኝ፣ ለዛውም እሱ እናቱን የበላ እኛ ደግሞ እናታች ከሞት ለማዳን አነሰ በዛም የምንደክምዝቀሽ ተመክሮ ከብሄራዊ ብቁ ስሜት ጋር፣ የተባ መክሊት ያለን ነን። ግን እርማቱን ከራሳችን መጀመር ተሰነን፣ ግለኝነት ገዛን፤ ከሱ ብንፋታ ተስፋችን መንፈሰዊ ሃብታችን መሆን ብቻ ሳይሆን መተያዬትም እንችላለን

ሌላው ማንሳት የምሻው ቁም ነገር ለፍላጎታችን ግልጽ አይደለነም። ዕውነት ፈላጊነታችን ከራሳችን ላይ ሲደርስ ልጠዋል። ለልባችን ፍላጎት ታማኝነታችን ከመናገር ልፍ አይልም። ፍትህ ጥማታችን በወንድማችን ላይ እኛው ስንፈጽመው (ስንበድል) ይደርቃል።

በጣም የምናዘግምበት፣ በጣም ተራርቅን የምንኖረው የውስጥ ገመና አለብን፣ ግለኝነት የሚሉት አረም፣ እሱን ካላንጠለጠልነው በስተቀር አይደለም ድል እንደ ዜጋ ለመጠራትም ፈቃዱ ከራሳችን የሚተን ይመስለኛል። ይህን ደግሞ ሌላ ሳይጠብቅ የማይሸሹት፣ የማይሸሸጉት፣ የማይሾልኩት ዳኛ ሕሊናችን በራሱ ጊዜ ቆርጦ ያሰዬን እና ሁል ጊዜ እንደ ባተትን፣ በጭንቀት ደመመን ተውጠን እንደ ማሰን እንኖራለን። ሰው መኖር ከአለበት ለሕሊናው። መፍራትም ከአለበት ከሥላሴ በታች ሕሊናው ነው።

አሁን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አቧራ ለብሶ መሬት ላይ ወድቆ ብናገኘው፣ አቧራውን አራግፈን እናነሳዋለን፣ እንለብሰዋለን ወይንስ ረግጠነው እንሄዳለን? ከታመቀው የውስጥ ሽምቅ ፍላጎታችን እንደንፋታ የሚጠይቀው የዕውነት ብሄራዊ ጥሪ ይህ ይመስለኛል።

ኢትዮጵያዊነት ማለት እኮ ሚሥጥር ነው። ሚሥጥር የተከደነ ነው። ወደ ተፈጥሯችን እንመለስ። ያን ጊዜ እናሸንፋለን፤. ከራሃብ እንላቀቃለን፤ ከጥማችን እንፈወሳለን፤ ከመበተን እንድናለን በሰተቀር ግን እንደ አሁኑ አያዛዛችን ድሉ እሩቅ ነው። ወያኔ የሚፈጥረውን ችግር ማንሳት መጣል ሆነ መደጋገም አያሰፈልግም። መጀመሪያ እኛ ውስጣችን እንርታ። ከራሳችን ጋር አንተላለፍ ከፍላጎታችን ጋር አንተላለፍ፣ ከራዕያችን ጋር አንተላለፍ፣ ጥያቄውን ወደ ራሳችን፣ … መልሱንም እራሳችን እናመልስው

አብሶ ውጭ ያለው ሕብረተሰብ የሚያመካኘው ምንም ነገር የለም። የእናቴ መቀነት ጠላፈኝ ካልሁነ በስተቀር፣  ከገሃዱ መሬት ላይ ከአለው ነገር እንነሳ፣ ከሁሉ በፊት ግን ማሸነፍ ካለ፤ ቀድሞ ራስን መሸነፍ ነው።

የግለኝነትን ደብቅ ጎጆን እናፈራርሰው። ቅን እንሁን፣ ቅን እናስብ። በበጎ ለመተርጎም እንሞክር፣ እሩቅ ሳንጓጓዝ  አጠገባችን ያለውን ሀብት በአግባቡ እንጠቀም፣ ወጪውም ይቀንሰል። የአለንን እናድንቅ፤  ፍቅርን ለሥነ-ተፍጥሮው ስንል እንኳን እናክብረው፣ የምናገኘውንም ፍቅር አትኩሮት ሰጥተን በአግባቡ እናስተዳድረው፤ ፈጣሪያችን የሰጠንን እንጠቀምበት፣ መመቅኝትን ከሥሩ እናፍልስው፣ ኢትዮጵያን መውደድን በመሆን መቻል እናቅልመው። ትግልን ከወረተኝነት ጋር እናፋተው፣ ከሥነፍና ጋርም እንለያዬው።

                         የሠራዊት ጌታ እዬሱስ ክርስቶስ በቃችሁ ይበለን አሜን!

                           ዕልፍ ነን እና ዕለፍነታችን በተግባር እልፍ እናድርገው!
                          ትውልዳዊ ድርሻችን በጋራ ለመወጣት፣ ከራሳችን እንጀምር!
                                                   አመሰግናለሁ።
ገፅ … 243

                                          

                                        ... ወጣትነት እና እኔ ሳንገናኝ ተላለፍን



((((((((((((((((((
((((((((((((((((((((
((((((((((((((((



ነሀሴ 12 ቀን 2002 .
ሲዊዘርላንድ

(((((((((((((((((((
(((((((((((((((((
((((((((((((((((



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።