ቅኝቴ ነሽ!

„እኔ ብናገር ህመሜ አይቀንስም፤
 ዝም ብል ከእኔ አይወገድም።“
(መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፮)
ሥርጉተ© ሥላሴ
28.07.2018
(ከዝምተኛዋ ሲዊዝ)



ይህ ፎቶው ያነሳችኝ መምህሬ ናት - የሥነ ጹሁፍ ክፍለ ጊዜ ላይ፤ ለሦስት ተከታታይ ዓመት በሳምንት አንድ ቀን አንድ የስደተኛ መጋዝን ዝግጅት ውስጥ ከነበረው ቡድን ጋር እሰራ ነበርኩኝ፤  ያው በነፃ ማገልገል እግረ መንገድም መማር ስለሆነ። ለመጽሄቱ የመጀመሪያውን የሥነ - ግጥም አምድ ያስጀመርኩት እኔ ነበርኩኝ። ከዛ በኋዋላ ነበር መምህሬ እና አለቃዬ  የዓለምን ዕውቅ የሥነ ግጥም ባለቅኔዎች ማሰስ የጀመረቸው።  ሌላው አለቃዬ ሁልጊዜ ስትናገር ሥርጉተ ተማሪ ብቻም አይደለችም ባልደረባዬም ናት ትል ነበር። ብዙ ጌዜ መጋዝኑን እርእስ እኔ እረዳት ነበር፤ ለይ አውቱንም፤ በተጨማሪም ኬኒያ ለሰባዕዊ መብት ጉባኤ የሄደችው ዋና አለቃችን  እኔን የሚያውቅ ሰው አግኝታ ዝርዝር መረጃውን በኢሜል ስትልክላት የነበራት ደስታ ይህ ነው አይባልም። አልናገረም ነበር እኔ ምን እንደነበርኩኝ። መረጃ የሰጣት ወንድሜ ሙሉ ስብዕናዬን እና ተመክሮዬን ነበር። የቅርብ አለቃዬ እና መምህሬ የልጆች ጋዜጠኛ ነበረች። አሁን ሌላ ፕሮጀክት ውስጥ ነው የምትሰራው። 

እኔን ወደ ልጆች ራዲዮ አዘጋጅነት እንዳተኩር ያደረገኝም የእሷ ተመክሮም ጭምር ሲሆን ለኢትዮጵያ የነፃነት ትግል ብዙ ደክማለች። መረጃ በማሰባሰብ እረግድ ብቻ ሳይሆን በመሰጠት እረገድም። አብሶ በስብዕዊ መብት ረገጣዎች ጉዳዮች ላይ ሰፊ አትኩሮት አላት። እኔም በብዙ ሁኔታ አግዛኛለች። ቤቷ ስሄድ እንደኛው ባህል አልጋዋን ለቃ እሷ ከታጣፊ አልጋ ተኝታ ታስተናግደኝ ነበር። እሩቅ ግን በሽኝት ሄጄ እምሰራበት ራዲዮ የኢትዮ ኮሚኒቴ ፕሮግራም ስለነበር፤ ይህም ያው ነጻ አግልግሎት ነው። ሙሉ ዝግጅቱንም ትከታተላዋለች፤ ትቀዳዋለችም፤ አሁንም እንገናኛለን ... እጅግ አድርጌ አመሰግናታለሁኝ ለነበረን የቅንነት ደግ ጊዜ። 

     ወደ ቀደመው መቅድመ ጉዳይ...  እንዴት ናችሁ የእኔዎቹ አዱኛዎቼ … ዛሬን ከፍቶታል …

  • ·       የሆነ ሆኖ ይህ ግጥም ….


ውል መጸሐፌ ሦስተኛው  አዋቂዎች የተሠራ የግጥም መጸሐፌ ነው። ለእናቴ ለክብርቴ በሥጦታ የተሰጠ ነው። እብዬ ለሁሉም እናት ስለሆነች በአገሬ በአላዛሯ ኢትዮጵያ ብመሰላትም አላፍርባትም።
እሷም ከልጅነት እስከ ዕውቅት የምትለው „እኔ አላዛር ነኝ“ ነው። ይህን ግጥም ውል መጸሐፌ ላይ ለህትም የበቃ ነው።

በዜግነት ሰጪ እና ነሺዎች፤ በሴራ ፖለቲከኞች እና አራማጆች፤ በጉልበተኞች የህሊና ምርቶቼ ታፍነው የመጋዝን እራት ናቸው። ሥራዎቹ በዲዛይን የተሠሩ ብቻ ሳይሆን እርእሱቹ የተገባውን ያህል ነፃነት የተሰጣቸው ስለሆኑ ካሻቸው ላይ እንደ ፈቀዱ እንዲቀመጡ ተወስኖላቸዋል።

ስለሆነም እርእሱ በድምቀት የተጻፈው „ቀጸላዬ“ ነው። ጎንደር ቀጸላ የተለመደ ሥም ነው። ትርጉሙም በጥቂቱ  ዋና፤ አውራ፤ በህረ ጸጋ፤ አምድ፤ ጉልላት፤ አንጎል፤ ነፍስ፤ ህይወት፤ የጎላ፤ መንብር እንደማለት ነው። ስለዚህ “ቅጽል“ ከሚለው ሰዋሰዋዊ ክፍለ አካል ትርጉም ጋር  በእጅጉ የወጣ ግን ሁለገብ የሆኑ የመሪነት፤ የብቃት፤ የክህሎት፤ የጥብብ ልቅናን የሚገለጥ ነው።

               መዝሙሬ
          ሙናዬ        ጋሻዬ
     መቅድሜ               ጠበቃዬ።
   ዓለሜ                    ሥሬ ነሽ ….
   ሁነኛዬ                   … ዜናዬ
    አቫዬ                    ጤናዬ።
                             ልሳኔ ነሽ …
                             … ቧንቧዬ
                             አዬሬ።
                             ሟተቴ
                             በኵራቴ ነሽ
                             የደም ዋጋዬ።
                             ነፍሰ - ሥጋዬ
                             ዝማሪዬ። 
                             ቅኝቴ ነሽ
                             ቀፀላዬ!
                             ድንቅ ነሽ
                             አርበኛዬ።
                             ዘብ አደሬ፣
                             የነፃነት ገበሬ፣
                             ጽኑ መምህሬ፣
                             ውስጠ-ሀገሬ!
·        ተጣፈ ሰኔ 3 ቀን 2001 ዓ.ም  ሄርሽን ሆቴል - ሲዊዘርላንድ

v አነባቡ ከአጋጭ ይጀምር እና ወደ ታች ይወርዳል።
                 ከትህትና ጋር አመሰግናለሁ።

ሲዊዞች አይገርማችሁም ለረጅም ጊዜ አሜሪካኖች በቁጥር ይበልጧችሁ ነበር፤ በዚህ ሳምንት ግን እናንተው በለጣችሁ። እናም ደስ አለኝ። በሌላ በኩል እስከ አሁን ሪከርዱን ደረጃውን ያላስደፈረው ቤልጄም ነው። ቤልጄም ያሉ ታዳሜዎችን በአካል ባገኛቸው እንዴት ደስ ይለኝ ነበር መሰላችሁ። ናፈቁኝ። ምን አድርጌላቸው ነው እንዲህ በጽናት አብረውኝ የሆኑት። የሚገርመው በከፋኝ እጅግም በጉልበተኞች በተጠቀጠቅኩበት ሰዓት መሆኑ መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸው አንድ ልዩ ቅብዕ እናዳላቸው አስባለሁኝ። የእነሱ ድጋፍ የሥነ  -ልቦና አቅም ፈጥሮልኛል።  
     ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

ኑሩልኝ እሾሕ አሜኬላ አይንካብኝ። ድንግልዬ አብራችሁ ትሁንልኝ።
የኔወቹ ቅኖቼ እዮባዊያኖቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።