ልጥፎች

ከፌብሩወሪ 14, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ብፁዑ አባ ልቅና ማዕዶተ - ዕውነትን ተመገቡት። ጠጡት።

ምስል
  ብፁዑ አባ ልቅና ማዕዶተ - ዕውነትን ተመገቡት። ጠጡት።   "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"   "ዬኦሮምያ ህብረት ባንክ የቤተክርስትያኗን ቅምጥ ሃብት በካዝናው አስቀምጧል። እንሸነፍ ብለን። አዋሽ ባንክ፤ ዬኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ድርሻ አላቸው። ብዙም የረባ በንጠቀምም። አባይ ባንክ ግን ተወዳድሮ በገብያ ህግ አሸንፎ ነው። ከአማራ ባንክ ጋር ምንም ዓይነት ውል ዬለንም። ከእሱ ይልቅ ከሌሎች ተጨማሪ ባንኮች ጋር ዬጠበል ያህል አብረን እንሰራለን። የተሻለ ዬሚጠቅም ተወዳዳሪ ከመጣ ደግሞ ውላችን ይቀጥላል። " ……… ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ጋር ስለነበረው ውይይት ተጠይቀው ሲመልሱ ከመሄዳቸው በፊት እንደምን እንደ ተሰናዱ፤ ከዛም ከሞት ጋር ፊት ለፊት ቆመው እንደምን እንዳስረዱ ገልፀው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድን ትዕግሥት አድንቀው ጠቅላይ ሚሩ ሊያወያዮዋቸው እንደጠዬቁ እና ጠቅላዩ ማዕከላዊ ይሆኑ ዘንድ፤ መንግሥታቸው ያለበትን ኃላፊነት እንዲወጣ በትህትና ገልፀው የቤተክርስትያኗ ጉዳይ አወያዮዋም፤ አነጋጋሪዋም ውል አስፈፃሚውም ዶግማና ቅኖናዋ ስለመሆኑ እንዳስረዱ፤ በዚህም እንደተስማሙ ከገለፃው ዕድምታ ተረድቻለሁኝ። የእግር እና የጭንቅላት አስተዳደርን ፍልስፍናም ባርከውልናል። ሰላማዊ ሰልፍ የገኃዱ ዓለም እና የሰማያዊውንም ፍንትው አድርገው ገልፀውታል። በዚህ እንደ ተረዳሁት ሰማያዊው ሰልፍ በሚያስደምም አኳኋን መከወኑን አብሥረዋል። የአንድም ሦስትም ሆኖ የመምራት ዬማስተዳደር ክህሎትን፤ ዊዝደምን ሲገልፁም የእጬጌው የብፁወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ልዩ ስክነት እና ዬረጋ ብስለት እንዲሁም የበታቾች አባ ትምህርት ብፁዑ ዶር አቡነ ጴጥሮስ እና የአባ ልቅና ዬብፁዑ አቡነ አብርኃም አህቲ መስመር ዕውነት ስለመሆኑ በአጽህኖት ገልፀዋል።