#ምርጫው ቢራዘምስ? መሪው የምርጫ ምልክት #ነዶ ምርጫው ታስቀጥል ይሆን? ብታራዝመው አይሻልህምን?
መሪው የምርጫ ምልክት #ነዶ ምርጫው ታስቀጥል ይሆን? ብታራዝመው አይሻልህምን? ግን ቆረጠ #ብልፄው 7ኛ አገራዊ ምርጫውን ለመፈጸም? አገራዊው፤ አህጉራዊው እና ሉላዊው ሁነት ሲታሰብ ምርጫን መፈጸም ወይንስ ማረዝም የቱ ይቀል ይሆን? ማራዘም ላይ ተጫኝ ሁለገብ ችግሮች አይለዋል። ገና ሳይጀመር ሞት አለ። ራስ ጋይንት ላይ አሳዛኝ ሁኔታ ነው ያለው። ሞቱ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ነው። ማስጠንቀቂያውም እንዲሁ ነው። በከፋኝ ዱር ቤቴ ባሉ ታጣቂወች በኩል #ዋ ! ብትመርጥ// እጩ ሆነህ ብትመረጥ፤ በብልፄው በኩል ዋ! #ባትመርጥ ባትሳተፍ /// እጩ ሆነህ ባትቀርብም ህዝባችን ወከባ ላይ ነው። ጭንቅ ላይ። #ምርጫው ቢራዘምስ? #ግን ጉዳዩን ለመንፈቅ ወይ ለ፩ ዓመት ምርጫው #ቢራዘምስ ? አልኩኝ እኔው። ርጋታ የለም። የተረባበሼ መንፈስ ነው ያለው። ውጥረቱ የመንፈስ አና ብሏል። ከኑሮ ውድነቱ፤ ከሰላም እጦቱ ጋር ምርጫ + ጫን ተደል ጭንቀት ተሸክሞ ምጥ ላይ ነው???? በነገራችን ላይ ዴሞክራሲን ባለመለሙ፤ ሰላማቸው በተረጋጋ አገሮች እኮ ምርጫ ልብ ያንጠለጥላል፤ ዘናም ያደርጋል፤ ፋክክሩ ሲጦፍ ትዕይንት ነው። "አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።" እኔ ምርጫ መብት ነው ብዬ አምናለሁኝ። መምረጥም /// መመረጥም የመብት ቅኔ ናቸው። ዕድሉ ባያፈስ የሚመለከታችው ሁሉ ቢሳተፋ፤ ሁሉም ቢሳተፋ ጥሩ ነው። #ግን አጤ ሆርሙዝ ሁለገብ ተጨማሪ ራህብን አውጇል፤ የቤርሙዳ ትርያንግል ያህል እዬከበደ ነው። ከስምምነት ቢደረስ እንኳን የተረጋጋ ሁነት ለመፍጠር ዘለግ ያሉ ወራቶች ያስፈልጉታል እዬተባለ ነው። የኃይል አሰላለፍም ብወ...