#ምርጫው ቢራዘምስ? መሪው የምርጫ ምልክት #ነዶ ምርጫው ታስቀጥል ይሆን? ብታራዝመው አይሻልህምን?

 

መሪው የምርጫ ምልክት #ነዶ ምርጫው ታስቀጥል ይሆን? ብታራዝመው አይሻልህምን? 
 
ግን ቆረጠ #ብልፄው 7ኛ አገራዊ ምርጫውን ለመፈጸም?
 
አገራዊው፤ አህጉራዊው እና ሉላዊው ሁነት ሲታሰብ ምርጫን መፈጸም ወይንስ ማረዝም የቱ ይቀል ይሆን?
 
ማራዘም ላይ ተጫኝ ሁለገብ ችግሮች አይለዋል። ገና ሳይጀመር ሞት አለ። ራስ ጋይንት ላይ አሳዛኝ ሁኔታ ነው ያለው። ሞቱ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ነው።
 
ማስጠንቀቂያውም እንዲሁ ነው። በከፋኝ ዱር ቤቴ ባሉ ታጣቂወች በኩል #ዋ! ብትመርጥ// እጩ ሆነህ ብትመረጥ፤ በብልፄው በኩል ዋ! #ባትመርጥ ባትሳተፍ /// እጩ ሆነህ ባትቀርብም ህዝባችን ወከባ ላይ ነው። ጭንቅ ላይ። 
 
#ምርጫው ቢራዘምስ?
 
#ግን ጉዳዩን ለመንፈቅ ወይ ለ፩ ዓመት ምርጫው #ቢራዘምስ? አልኩኝ እኔው። ርጋታ የለም። የተረባበሼ መንፈስ ነው ያለው። ውጥረቱ የመንፈስ አና ብሏል። ከኑሮ ውድነቱ፤ ከሰላም እጦቱ ጋር ምርጫ + ጫን ተደል ጭንቀት ተሸክሞ ምጥ ላይ ነው???? 
 
በነገራችን ላይ ዴሞክራሲን ባለመለሙ፤ ሰላማቸው በተረጋጋ አገሮች እኮ ምርጫ ልብ ያንጠለጥላል፤ ዘናም ያደርጋል፤ ፋክክሩ ሲጦፍ ትዕይንት ነው። 
 
"አቤቱ የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
እኔ ምርጫ መብት ነው ብዬ አምናለሁኝ። መምረጥም /// መመረጥም የመብት ቅኔ ናቸው። ዕድሉ ባያፈስ የሚመለከታችው ሁሉ ቢሳተፋ፤ ሁሉም ቢሳተፋ ጥሩ ነው።
 
#ግን አጤ ሆርሙዝ ሁለገብ ተጨማሪ ራህብን አውጇል፤ የቤርሙዳ ትርያንግል ያህል እዬከበደ ነው። ከስምምነት ቢደረስ እንኳን የተረጋጋ ሁነት ለመፍጠር ዘለግ ያሉ ወራቶች ያስፈልጉታል እዬተባለ ነው። የኃይል አሰላለፍም ብወዛ፤ ሽግሽግ እያመጣ ነው።
 
ሌላው #ደቡብ አፍሪካ ላይ ያለው የፋመ መከራ አለ። ለእኛ በጣም ቅርባችን ነው።
#የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይም ነፍስን ይፈትናል።
አገራችን ላይ እቴጌ ትግራይ ሙሉ ለሙሉ አትሳተፍም። በስድስተኛውም ይሁን በሰባተኛው ብሄራዊ ምርጫ ትግራይ አትሳተፍም። ከዚህም ከፍ ያለ #ሞጋች ጉዳይም አለ። አቤቱ ህወሃት እያንገረገበው ያለው ቀውስ። 
 
አማራ #በአብዛህኛው ገጠራማ ቦታወች የምርጫ ተሳትፎ የሚኖር አይመስለኝም። አማራ ክልል ላይ የፓርላማ ውክልናው ወጣ ገብ፤ ተሳትፎው አባጣ ጎባጣ ይሆናልም። ኦሮምያም መሰል ችግር አለ። ግን ከአማራ ክልል በርቀት ሆኜ ስገመግመው የሚሻል ይመስለኛል። ባልተሟላ ውክልና ብልፄው 50+ ከዚህም በላይ ቢያመጣ የምርጫው ሌጋሲ በምን ያህል % ይመዘናል? ከስሜን አስተማማኙ አፋር ብቻ ይመስለኛል። 
 
#የሰላም እጦት አለ።
#የነዳጅ የዋጋ ውጣ ውረድ።
#የብልፄ የውስጥ አለመረጋጋትን በስፋት እያዬሁ ነው። አንዲት የሙግት የሃሳብ ዘለላ፤ ከአንድ አልበም ውስጥ አንድ ክሊፕ ደንግጥ በል ያሰኜዋል ብልፄው። ሠርቻለሁ፤ የህዝብ ነኝ ያለ ዓውራ ፓርቲ #ሊባትት አይገባም ነበር። ሥራዬ ደጀኔ፤ ሥራዬ ዕድሌ ብሎ ሊያስብ ይገባ ነበር። የማዬው ግን ……… 
 
ብልፄው ጥሞና ቢወስድ።
ጊዜ ወስዶ ቢረጋጋ።
 
የአገር ውስጥ ችግሮችን በስክነት ለመፍታት ጨምቶ ቢያስብ። እና ወደ ተግባር ተሎ ቢገባ። የተሻለ ይመስለኛል። ብዙ ብዙ ሁነቶች #ያረገረጉ ናቸው። ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ወይንም የደቡብ ብቻ አይደለችም።
 
ሙሉዑነት በጎደሎነት ሊወራረድ አይችልም። ስድስተኛው ምርጫ ትግራይን አልቦሽ፤ ሰባተኛው ምርጫ አማራ ክልል ታከለ። በስሱም ቢሆን ጋንቤላ ወዘተ ……… ብልፄው 50+ ማምጣት የሚቸግረው አይመስለኝም። ግን ቀለሙ ይጎድልበታል። የተወሰኑ ክልሎች ተሳትፎ ብቻ በቂ አይመስለኝም። 
 
#በስሱም ቢሆን።
 
በርከት ያሉ መምረጥ የሚፈልጉ፤ ለመወዳደርም የሚሹ ዜጎችስ ጉዳይ ሊታሰብበት ይገባል ባይ ነኝ። በማሟያ ምርጫ ማስተካከል ይቻላል፤ ግን ስንቱ ቦታ? እነኝህ የሚፈልጉ ግን በአንድም በሌላም ምርጫውን የሚሹ ኢትዮጵውያን ፍትህ ይሻሉ፤ በመብታቸው መጠቅም ይሻሉ ለምሳሌ ነገረ ወልቃይት ጠገዴ ወገራ አውራጃ እና ስሜን --- ሙሉ 8 ዓመት በምጥ??? በሌላ በኩል #ሰማዕትነትን የሚጠይቁ ባድማወች አሉ። ፍጥጫ ላይ ያሉ። ዋና ዋና የአማራ ከተሞች። እስር ቤት ያሉም ፖለቲከኞች መወዳደር ቢሹ ይህም ዝግ ነው።
 
#ለሽበሉ አይበጅም።
 
ብልፄው በተለይ አገር ላይ ያሉትን ችግሮችን ለሽ በሉ ፖለቲካ አይጠቅምም። ወሳኝ አመክንዮወችን ቅልጥፍ ያለ ትጋት ይሻሉ። #ሳያስተኛ ቅደም ተከተል አውጥቶ ወደ ተግባር ለመተርጎም ቁርጠኛ አቅም እና ውሳኔ ካለው፤ ምርጫውን አራዝሞ ቢያዬው ጥሩ ነው። ግንዕድሉን የሚሠራበት ከሆነ ነው። የትኛው የፖለቲካ አቋም ይበጃል ለህዝብ እና ለአገር ብሎ አስልቶ መነሳት ብልህነት ይመስለኛል።
#ክርክሩን ሁሉንም ባይሆን አይቸዋለሁኝ። 
 
ከውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ጀምሮ ብልፄው ሚኒስተሮችን አሳትፏል። ይሄ ጥሩ አክብሮት ነው። በዚህ ውስጥ የሚኒስተሮች ጉዳያችን ነው የማለት ብቻ ሳይሆን፤ ዝቅ ብለው ለሙግት መሳተፍ፤ የመንግሥት መሪወች የብልፄም አባል መሆናቸውን ከሃሜት እዩ መባሉ አይከፋም። የመድረክ አቅማቸውን፤ የሰብዕናቸውን ልኬታም ማስተዋል አስችሎኛል።
 
በክርክሩ ግን ወጥ ፎርማቱ #ነገ ሳይሆን #ትናንት ተኮር ነበር። አንድ ጠንከር ያለ ሃሳብ ከሞጋቾቻቸው ሲቀርብ የደነገጡ አይቻለሁኝ። ይህ የሪህርሳል ችግር ይመስለኛል። አንገታቸውን ይደፋሉ፤ ወይ በስሜት እላፊ ሄደው ሞደሬተሮች ያስቆሟቸዋል። የምረጡኝ ዘመቻ እና ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የሚደረግ የማኒፌስቶ ራዕይ እና ግብ ፕሮፖጋንዳ፤ መፈክር ፋክት ሲሆኑ፤ ብቁ አመክኒያዊ #መካች ሊሆኑ አይችሉም። 
 
ስለዚህ የራስን አቅም ከራስ ጋር በሥርዓት የማደራጀት ሂደት ለሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ያስፈልጋል። ከፍም ዝቅም ያላሉ በጀመሩት አቅም ልክ በየመድረኩ የመጠኑም አይቻለሁ። ያ ጥቂት ሊሂቃን ብቃት ግን በዚህ ውጥንቅጡ በውጣ የዘመኑ ግሎባል የፖለቲካ ባህሬ የአገር፤ የአፍሪካ ቀንድ፤ የአህጉር እና የዓለም ዓቀፍ ሁነት ጋር አጣጥሞ ምርጫን ማካሄድ ቢቻል በማሸነፍ ውስጥ የሚገኙ ዕድሎች ምን እና ምን ይሆናሉ፤ ህሊናዬን የሞገተ ጉዳይ ነው።
 
በሌላ በኩል በትብትቡ ችግር ውስጥ የሎጅስቲክስ አገልግሎት፤ ሁሉንም በአውሮፕላን አጓጉዞስ ይሆናል ወይ? ዘርፈ ብዙ ሞጋች ፈታኝ ሃሳቦችን ወደ ውስጥ አስገብቶ ቢፈተሹ ይበጃል። በስጋት፤ በጭንቀት፤ በፍርሃት መንፈስ የተወጠረ መብት እራሱ ማረፊያ ያጣል።
#ርጋ በምን ሁኔታ።
 
እርጋታን በሚመለከት መራጩ ህዝቡም፤ ተወዳዳሪወችም፤ አስፈፃሚ አካሉ ምርጫ ቦርድም፤ ኃላፊነት ያለበት ዓውራው ፓርቲ ብልፄውም ቢሆን ሁሉም የተሰናዳ የውስጥ ሰላም ስክነት እና በቂ ጊዜ የሚያስፈልጋቸው ይመስለኛል። የአምስት ዓመቱ ቆይታ ከደራሽ ብሄራዊ፤ ቀንዳዊ፤ አህጉራዊ እና ሉላዊ ችግሮች ጋር አመጣጥኖ ሚዛን ጠብቆ የታሰበውን ዕቅድ በታሰብ ጊዜ ለመፈጸም ከበድ ያሉ ሞጋች ክስተቶች እያዬሁበት ነው። 
 
#ምርጫው ቢራዘም ደግሞ።
 
ምርጫን ብታካሂዱ ዋ ያሉ አካላት፤ ለምን ተራዘመ ብለው ሙግት ያነሳሉ። የቅኔው ጎልማሳ ቴዲ አፍሮ በቅርቡ ለንደን ሄዶ ሙዚቃ አቀረበ ተብሎ "ተደመረ፤ በለጸገ" ብዙ ፈተና ነበር። እዮሪካ ሲመጣ አንድ ዩቱበር ከ20 በላይ ሙሉ መሰናዶ ሰርቷል።
 
በሌላ በኩል ከምርጫ ውልፍት አሉ ተብለው ውግዘት ሲዘንብባቸው የባጁት አለቃቸው ብልፄ አራዘምኩ ብሎ ቢያውጅ ሌላ ተውኔት ደግሞ እናያለን። ስክን ብለው በጥሞና የቆዩት ደግሞ ከምስራቅ፤ ከደቡብ፤ ከስሜን እና ከደቡብ የሚነሱ ወጀቦች አይነቀንቃቸውም። ዕውነታቸው #ሳይደነግጥ፤ ሃቃቸው #ሳይበረግግ በልካቸው ልክ ሆነው ይዘልቃሉ። ዕውነት ቦታውን ለቆ አያውቅምና።
 
ማህበረ ቅንነት ልስልስ ያለ ምሽት ይሁንላችሁ። አሜን።
 
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን ቀና እንሁን። አሜን።
 
ኑሩልኝ። አሜን።
 
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
 
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
04/05/026.
 
ዕውነት ወጌሻ ወይንም ጋራጅ አያስፈልገውም።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።