ነገረ አዲስ አበባ "በእልህ ተነሳስተው አዲስ አበባን አስጨነቁ አንዳንድ አመራሮች" ምስጣዊ ጉዞ ………
ነገረ አዲስ አበባ "በእልህ ተነሳስተው አዲስ አበባን አስጨነቁ አንዳንድ አመራሮች" ምስጣዊ ጉዞ ……… እልህ ሊባል የሚገባው የወይብላ ማርያም ቀራኒዮ ዕለት ነበር። እኔ ከሥሩ ሳጠናው። አዲስ አበባን መዋጥ በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የሚመራው ዬስውሩ መንግሥት ፕሮጀክት ነው። ግልጥ መንግሥታቸው ኢትዮጵያ እያለ ያነሆልልኃል። ስውሩ ደግሞ ከሥርህ ይነቅልኃል። ያመካኛሉ "ሸኔ" እያሉ። በ15/11/2022 በነበረው የፓርላማ ውሎ ይልቅ አንድ ሚስጢር አውጥተዋል #ምክትል ከንቲባ ሆኜ እዬሠራሁ ነው ብለውናል። "ዬቤትህ ቅናት በላኝ።" ዬቧልተኛው፤ ዬአሳቸው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ቲም ነው ይህን ዬሚለን። በአዲስ አበባ እዬሆነ ያለው ጥቂት አመራሮች በእልህ ዬሚያደርጉት እንጂ የታቀደ አይደለም ይላሉ እነ ዘመን አይፈሬ ማህበረ ኦነጋዊው አመራር። ይህን መረጃ ዬገለፀው ዋዜማ ራዲዮ ሲሆን ምንጩን ገልፆ በዘገባ ያቀረበው ለስላሳው ሚዲያ ኢትዮ ኒውስ ነው። 1) ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በ100 ቀን ትጋታቸው ስለምን በሚሊዮን ወጥቶ ዬደገፋቸውን ህዝብ ከሁሉም ክልሎች ለይተው ተውት? 2) ስለምን ከሱማሌ ክልል ግማሽ ሚሊዮን ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ በአዲስ አበባ እና በዙሪያው አሰፈሩ? 3) ስለምን ቡራዩ፤ ለገጣፎ ለገዳዲ፤ ሰበታ ያ ሁሉ ግፍ በጥዋቱ ተከወነ? 4) ስለምን ኦነግከነትጥቁ እንዲገባ ተደረገ? 5) ስለምን 600 ሺህ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪወች ከተለያዩ የኦሮምያ ክልሎች አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደረገ? ዶር ለማ መገርሳ እራሳቸው ዬተናገሩት ነው። 6) አዲስ አበባ በአንድ መኖሪያ ቤት ከመቶ በላይ ለሆኑ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪወች መታወቂያ በህገ ወጥ እንዲሰጥ ተደረገ? የባልደራስ የመነሻ ምንጩ...