ነገረ አዲስ አበባ "በእልህ ተነሳስተው አዲስ አበባን አስጨነቁ አንዳንድ አመራሮች" ምስጣዊ ጉዞ ………

 

ነገረ አዲስ አበባ "በእልህ ተነሳስተው አዲስ አበባን አስጨነቁ አንዳንድ አመራሮች" ምስጣዊ ጉዞ ………
እልህ ሊባል የሚገባው የወይብላ ማርያም ቀራኒዮ ዕለት ነበር። እኔ ከሥሩ ሳጠናው።
 
አዲስ አበባን መዋጥ በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የሚመራው ዬስውሩ መንግሥት ፕሮጀክት ነው። ግልጥ መንግሥታቸው ኢትዮጵያ እያለ ያነሆልልኃል። ስውሩ ደግሞ ከሥርህ ይነቅልኃል። ያመካኛሉ "ሸኔ" እያሉ።
 
በ15/11/2022 በነበረው የፓርላማ ውሎ ይልቅ አንድ ሚስጢር አውጥተዋል #ምክትል ከንቲባ ሆኜ እዬሠራሁ ነው ብለውናል።
"ዬቤትህ ቅናት በላኝ።"
 

 
 
ዬቧልተኛው፤ ዬአሳቸው የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ቲም ነው ይህን ዬሚለን። በአዲስ አበባ እዬሆነ ያለው ጥቂት አመራሮች በእልህ ዬሚያደርጉት እንጂ የታቀደ አይደለም ይላሉ እነ ዘመን አይፈሬ ማህበረ ኦነጋዊው አመራር። ይህን መረጃ ዬገለፀው ዋዜማ ራዲዮ ሲሆን ምንጩን ገልፆ በዘገባ ያቀረበው ለስላሳው ሚዲያ ኢትዮ ኒውስ ነው።
 
1) ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በ100 ቀን ትጋታቸው ስለምን በሚሊዮን ወጥቶ ዬደገፋቸውን ህዝብ ከሁሉም ክልሎች ለይተው ተውት?
2) ስለምን ከሱማሌ ክልል ግማሽ ሚሊዮን ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ በአዲስ አበባ እና በዙሪያው አሰፈሩ?
3) ስለምን ቡራዩ፤ ለገጣፎ ለገዳዲ፤ ሰበታ ያ ሁሉ ግፍ በጥዋቱ ተከወነ?
4) ስለምን ኦነግከነትጥቁ እንዲገባ ተደረገ?
5) ስለምን 600 ሺህ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪወች ከተለያዩ የኦሮምያ ክልሎች አዲስ አበባ እንዲገቡ ተደረገ? ዶር ለማ መገርሳ እራሳቸው ዬተናገሩት ነው።
6) አዲስ አበባ በአንድ መኖሪያ ቤት ከመቶ በላይ ለሆኑ ኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪወች መታወቂያ በህገ ወጥ እንዲሰጥ ተደረገ? የባልደራስ የመነሻ ምንጩ እኮ ይህ ነበር።
7) 1300 ዬአዲስ አበባ ነዋሪወች ስለምን ጦላይ በገፍ በጀምላ ታሰሩ?
በተለያዬ ጊዜ በአዲስ አበባ ነዋሪወች ላይ የማስደንገጫ ግድያ ተፈፀመ።
😎 5 ዬአዲስ አበባ ነዋሪወች በአደባባይ ስለምን ተረሸኑ? ለመሆኑ ቤተሰቦቻቸውስ በምን ሁኔታ ይገኛሉ? ስለ አዲስ አበባ ዝም አንልም ያሉ ባልደራሶችን ጽንሰት ሲሰሙ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ያን ያህል #በሰጨኝ አሉ?
ማርች 24, 2019
በሰጨኝ ለጠቅላይ ሚ/ር
ፈጽሞ አያምርም።
„እሳት በረድ ረሃብ ቸነፈር ይህ ሁሉ ሊበቀሉበት ተፈጠረ“
መጽሐፈ ሲራክ ፴፱ ቁጥር ፳፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute© Selassie
24.03.2019
ከእመ ዝምታ ከሲዊዝ።
9) ስለምንስ በባልደራስ ምሥረታ እና ሂደት ላይ ውጋት በዛበት? ሌላም በኦሮምያ ቋንቋ ተናጋሪ ዬተመሠረተ ድርጅትነበር። ዝንጥ በአለ አዳራሽ ስብሰባ ሲያካሂድ ምንም ሲገጥመው አላዬነም። ይለፋ ዝቀሽ ስለሆነ።
10) ስለ ምን ዬታከለ ኡማ ህግ ተረቀቀ?
11) ህገ መንግሥቱ ተጥሶ ኦሮምኛ ቋንቋ ለምን ተጫነ?
12) ወሮ አዳነች አበቤ ምደባ እንደምንያለ ነበር???
13) ከ1000 በላይ የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ መምህራን በሦስት እጥፍ ደሞዝ ስለምን አዲስ አበባ ተመደቡ?
14) ዬአደባባይ ሰልፍ አዲስ አበባ ላይ በስውር ስለምን ታገደ?
15) አዲስ አበባ ላይ የቅድስት ተዋህዶ በዓላት አከባበር ስለምን ቀራኒዮ ሆነ?
16) አዲስ አበባን ኢሪሌባንት ለማድረግ ስለምን ተፈለገ? በ12 ክፍለ ከተሞች፤ በ36 ወረዳወች፤ በ40 ቀበሌወች ሸገር ዬሚል ካቢኔ ፤ መቀመጫውን አዲስ አበባ እንዲሆን ስለምን በጀት ተመድቦለት ሥራ ውስጥ ገባ?
17) ዬአዲስ አበባ ዬምክር ቤቱ ሥአኮ አካላት ስለምን በኦህዴድ ታጨቀ? ስለምንስ ሙሉ ቁጥር ሆነ?
18) አቶ ምግባሩ ከበደ ስለምን ቂም ተያዘባቸው? ስለምንስ ተሰው? ነገረ አዲስ አበባ አይደለምን?
19) ዬአዲስ አበባ ጉዳይ አውራዬ ነው ያለው ባልደራስ ባይፀናበትም ብሄራዊም ሃሳብ ቢኖረውም ስለምን ከምሥረታው ቀን ጀምሮ በፖሊሲ ደረጃ ተዋከበ?
20) የመስቀል አደባባይ ዬባለቤትነት ጥያቄ ለምን ለሽሚያ ገብያ እንዴት ተከፈተለት?
21) የሬቻ በዓል ከቢሸፍቱ ኩሬ ተሰርቶ ስለምን ተስቦ ተለጠፈ?
22) ቀደምት ቅርሶች፤ ውርሶች ስለምን እንዲከስሙ ተደረገ? አርቲፊሻል ኩሬ እና ዬፓርኩ ጥድፊያ ዬቦታው ምርጫ እና ኩታ ገጠምበት ጥድፊያ ዬማንን ታሪክ ለመሥራት ይሆን? ቁጥጥር፤ ክትትል፤ ተጠያቂነት እግር ከወርች ታሥሮ፤ ተቀፍድዶ???
23) የቀደመ ቤተመንግሥትን ብወዛ ለምን አስፈለገ? ለምን ያሉት ጉዳዩን በኃላፊነት ዬሚመለከታቸው አቶ ዮናስ ደስታ በቀላጤ ከሥልጣናቸው ለምን ተባረሩ?
24) ወደ ጦላይ ከተወረወሩት 1300 መከረኞች ውስጥ ነጥላችሁ እስከ አሁን እስር ቤት እምታማቅቋቸው ንፁኃን ዬአዲስ አበባ ነዋሪወች በቀሉ ስለምንአሰበለ?
25) የወለጋ፤ ዬአጣዬ፤ ዬደራ፤ የሽዋ ሮቢት ዬአማራ ጭፍጨፋ እና ማፈናቀል ዬት ላይ ጫና ማመንጨት ስላሰባችሁ ይሆን?
26) አምስት ዓመት ሙሉ ከአማራ ክልል አማራወች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ዬሰርክ መጉላላቱ በኽረ አጀንዳው ምንድን ይሆን?
27) ዬአርቲስት ሃጫሉን ህልፈት አስየልክቶ አዲስ አበባ ትነድ ዘንድ ፈቃድ ከማን እንደ ተሰጠ፤ ተዋቸው አትከልክሏቸው ያሉት ዶር አብይ አህመድ አሊ ስለመሆናቸው እኮ ተራራ ሚዲያ ላይ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ገልፆታል? ለምን አዲስ አበባ እንደ ሻሸመኔ፤ ዝዋይ አመድ እንድትሆን ተፈቀደ? እስከ አሁን ቤተ ክርስትያናችን አናስነካም ያሉ እኮ እስር ቤት ናቸው።
29) በቅርቡበፓርላማ ዶር ትዕግሥት ጥያቄ ሲያቀርቡ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ስለምን ግሥላ ሆነው የፓርላማ ተመራጯዋን ከፍ እና ዝቅ አድርገው አዋረዱ?
29) አንድ ዬአገር መሪ፤ አንድ የዓለም የኖቬል ተሸላሚ እንዴት ቢያስብ ይሆን የዓለም ህዝብ መዲና ለሆነች ከተማ ህዝቡን "አዲስ አበባ ዬኦሮሞ ጠል" ነው ብሎ እንዴት ባለ ቃና? ቅላፄ? ብስጭት ሊገልጽ ቻለ? ውስጡ ያለው እንኩሮ ፈቃድ ምን ይሆን?
30) በማን ዘመን ይሆን ልጆች አዲስ አበባ ላይ እዬታፈኑ አድራሻቸው የሚጠፋ፤ በገንዘብድርድር ዬሚፈቱት? ምን ለማትረፍ? ማንን ለማስጨነቅ?
31) ዬወሰን ክልል አካላዩስ፤ ተካላዩስ ማን እና ማን ነበሩ? ገዳ ለገዳ? ኦዳ ለኦዳ? ኦነግለኦነግ? ግን ፍሪዳ መጣሉ እንደምን እረሳችሁት? ዬበሬ ደም መቋደሻ ተርቲምቋቅ እስኪለን ስለጋታችሁን።
32) ዬአዲስ አበባን የመዋጥ ፕሮጀክት እኮ ነው የአማራ ክልልን ሞጋች አመራር የበላው። የፀጥታውን ኃይል ተቆጣጥሮ ያሻን ለመፈፀም ቅኑን ጄኒራል ሰዓረን አሳጣ።
33) ከጉለሌ ወደ ባህርዳር የተሸኙት አማራወች ስለምን ነበር? በቅርቡም ከወለጋ ዬተፈናቀሉት ዶሮ ኩስ ጋር ኑሩ መባላቸው የዜግነት ክብር ይሆን?
34) ኦህዴድ እኮ አዲስ አበባ የኦሮምያ ናት ብለው መግለጫ አውጥተው ጠቅላይ ሚኒሩ የሰጡት መልስ ከእኔ ውጪ ነው፣ አላውቀውም ሲሉ ጊዜ መግዛታቸው የገበጣ ጨዋታ ብቻ ነውን?
35) ዬኮንደሚንዬም ቤቶች ውርስስ ከዬት ይመደብ???
አዲስ አበባ ተጠሪነቷ ለኦሮምያ ያስደረጉት ዶር አብይ አህመድ አሊ ናቸው። ዋዜማ የማስቆሚያ መመሪያ መተላለፋን ቢገልጽም ወቅታዊ ሁነቱን ለማርገብ ነው። እንደ ማንኛው ኢፍትኃዊ ተግባር ደጋፊወቻችን ይቀበሉታል ብለው ለሙከራ የወሰዱት እርምጃ ወዳጅ ሁነኛ ደጋፊወቻቸውን ስላስቆጣ እና መጪው ግራጫማ ደወልን ለማቀዝቀዝ ነው። እንጂ አዲስ አበባ ለኦሮምያ ተስጥታለች። ለዘላቂ ችግር ዘላቂ መፍትሄ ይሻል። አለባብሰው ቢያርሱ ነው የሚሆነው።
በጠቅላላ አዲስ አባበ ኦነግ ከመግባቱ ቀድሞ ታስቦበት መስከረም 5/2011 ጀምሮ እምትመራው በገዳ ሥርዓት ነው። ዬገዳ ወረራ፤ ዬገዳ መስፋፋት፤ ዬገዳ አስምሌሽን፤ ዬገዳ ዲስክርምኔሽን እራሱ ሱሴ ሲታሰብ ጀምሮ ታቅዶ የተሰራበት ነው። ራዕይ ዬለም፤ ፍኖተ ካርታ ዬለም ዬሚሉ ፖለቲከኞች ይገርሙኛል።
ጠቅላይ ሚር አብይ እና ቲማቸው ዬህሊና ሰሌዳ ተጽፏል ሙያ በልብን እዬተረጉሙ ነው። ለደጋፊወቻቸው የውሃ ዳንስ፤ የመብራት ብልጭ ድርግም ከጋበዟቸው በቂ ነው።
ጉልበታም ፖለቲከኛ ቢኖርማ ፓን አፍሪካ ሙቨምንት ዛሬ ሳይሆን ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ በአሉታዊ ዴሞግራፊ መልክዓ ተፈጥሮን ሲቀይር ያኔ ነበር ትጋቱ ዬሚጀመረው ከኢንጂነር ታከለ ኡማ፤ ከወሮ አዳነች አበቤ ጋር አቲካራ ከመግጠም። ዛሬ ጉዳዩ የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ በሆነ ነበረ።
የገዘፈ ችግር እያለ በብጥቅጣቂ ጉዳዮች ብቻ ላይ ሳይሆን ዬነበረው አትኩሮት ቤት ሳያፀዱ ጓሮ ላይ ነበር አትኩሮቱ። በሳል አስተዋይ ዬሰከነ ምራቁን የዋጠ ፖለቲካ መነሻውም መድረሻውም እርዕሰ መዲናዋ ትሆን ነበር። አንበሳው ዶር ለማ መገርሳ ኡርባን ፖለቲክስን እንደምን መሠረት አስይዘው ኦነግ ዘውድ እንደደፋበት አዬን።
ያ ሁሉ አቅም ሙት መሬት ላይ ለሽ ብሎ የኦነግ ፖለቲካ ፍሬ ኑሮት ይኽው ያስደገድጋል። ዬሆነ ሆኖ ማህበረ ኦነግ ተረት ተረቱን ተውት።
ፕሮፖጋንዲስ ዬማያስፈልገን ሰወች አለን። ፕሮጀክቱን ዬሚመሩት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ናቸው። ለዛውም አዘንጠው፤ ቅብጥ እና ቅልጥ አድርገው። ሌላውን ደግመው አጋድመው አስተኝተው።
ሙት መሬት ላይ ሆኖ ዬሃሳብ አቅም ሳይኖር እንደማይቻል ስለሚያውቁ ለአቅመ አዳም ስትደርሱ ብቅ በሉ ብለው ቀልደውባችኋል። ይህም ብቻ አይደለም ከጉዟችንዬሚያስቆመን ዬለም። 40/50 ቢሊዮን አትበሉ ከ400 ቪሊዮን በላይ ነው ፕሮጀክታችን፤ እንጨርሰዋለንም ብለዋል።
1) እሳቸው ሊቆጣጠሩት ዬማይችሉት ዬሰማዩን ቀጠሮ፤
2) ዛሬ ሰጥ ለጥ ብሎ የሚሠራው ህጋቸው መቅኖ ዬሚያጣበት ቀን ከመጣ፤ አስጊው አቅጣጫው ነው ……
በሁለቱ ሁሉም ይሸበለላል ለዛውም ለዘር ሳይበቃ።
"እግዚአብሔር ይስጥልኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
19/12/2022
ጊዜ ራዲዮ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።