ልጥፎች

ከሜይ 7, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"የድምጻችን ይሰማ" ስኬት ተመክሮ ዕድምታ በሥርጉተ ሥላሴ ዕይታ።

ምስል
 እንኳን ወደ ቀንበጥ ብሎግ በሰላም መጡልኝ  "የድምጻችን ይሰማ" ስኬት ተመክሮ            ዕድምታ በሥርጉተ ሥላሴ           ዕይታ።   „የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“   ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፱ 07.05.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዚሻ። ·        መግቢያ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ፧ የቀድሞው ፕ/ ዶር ነጋሶ ጊዳዳን ነፍስ ይማር አላልሽም። ለምን የሚል ጥያቄ ቀርቦብኛል። ከቶ እንደ እኔ ስለ ግለሰቦች መልካም ነገር የሚመሰክር ጸሐፊ አለን? ማንም እኮ ስሌለው አድንቆ፤ አክብሮ፤ ተበራታልኝ ብሎ አይጽፍም። እኔ ግን ሲሞላ እና ሲጎድል የተፈጠርኩኝ አይደለሁም። እውነት ነው በምልበት ሁሉ እተጋለሁኝ። ለዛውም የማይደፈረውን ሁሉ ነው የምደፍረው። ሰተት ብዬም ነው ፈተና ውስጥ ራሴን እምማግደው። መጠለያ ጥግ ሳይኖረኝ። ስለሆነም እሳቸውን በሚመለከት ብዙ ጊዜ ጽፌያለሁኝ። ቅሬታዬንም አክብሮቴንም። ኦዴፓ እንኳን ስላደረገላቸው መልካም ነገር አድንቄ ሁሉ ጽፌያለሁኝ። ህልፈታቸውን ሳዳምጥም በድንጋጤ ተውጬ እንዲያውም አንድ ቀን ካደርኩኝ፤ ከተረጋጋሁኝ በኋዋላ ጽፌለሁኝ። አንጀቴ ስስ ስለሆነ አገር ቤት ስለ አንድም ሰው በህይወት አለመኖር ተነግሮኝ አያውቅም። እንደ ጹሁፎቼ እና እንደ ሙግቶቼ ጠንካራ አይደለሁም። ከምትጥብቁት በላይ አዛኝ እና ሩህሩህ ነኝ። ሌላው ደግሞ የማልችላቸው ጊዜያትም ሊኖሩ ይችላሉ። የጤናም ጉዳይ አለ፤ ድካም አለ። እንዲሁም በአመዛኙ ደግሞ እኔ ብዙ አትኩ...