ልጥፎች

ከጁላይ 21, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"ሆድ ሲያውቅ ..."

ምስል
„ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ።“ „በውኑ ደንግል ረግረግ በሌለበት ቦታ ይበቅላልን?“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፲፩) ከሥርጉተ © ሥላሴ 21.07.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።) ·        በር። ዛሬን ደብሮታል። ደምኗል። እሜቴዋም ብቅ አልልም ብላ ጫጉላዋ ላይ ናት። እናም እኔም መውጣቱን አልፈለግሁትም። ስለዚህም ይህ ተኮለመ።፡ ·        የ ግራሞት ክራሞት! ከያንያን ምክንያት አይደሉም፤ ወይንም የአዲስ አባባ ከንቲባ ሹመት ምክንያት አይደለም። መሰረታዊ ጉዳይ የጠ/ ሚር አብይ የፍቅር ጉዞ እና ቀጣይ ተስፋው ነው መከራው። አጀንዳ ስለሚያሳጣ። ደጋፊ ስለሚያሳጣ።  ጸረ የአብይ ጸረ አብይ መንፈስን ከሳተናው ድህረ ገጽ በስተቀር፤ ብሎጎች፤ ታላላቅ ሚዲያዎች፤ የኮሚኒቲ ራዲዮኖች ሁሉም የባጁበት ነው። ምክንያታዊ በሆኑ ጉዳዮች አይደለም ሲታመሱ የባጁት ሁሉም ሚዲያ። ለአገር ተቆርቋሪነት አልነበረም ሁሉም በጓዳው ደብቆ ያቆዬው የታቆረ ዓላማ እንጂ፤ ብጥብጡንም ሞከካረው መሬት ላይ እሱም ለግብ አላበቃም። ትንሽ ራፊ የ  ዕውቅና ከማሰገኘት በስተቀር ሞጋዳዊ ለውጡን፤ ሰላሙን በማወክ ያስገኘው ፋይዳ የለም። እንዲያውም እትጌ ኤርትራ የምሥራቹን ጀባ ብላ አቅልም ቀልብም በዚያ ላይ ሰከነ።    …. እራሱ  የአሜሪካ እና የጀርመን መንግሥት በጀት መድቦ የሚያሠራቸው ሚደያዎች ሳይቀሩ በምን ሁኔታ ላይ ሲታተሩ እንደነበሩ ይታወቃል። ይህ የለውጥ መንፈስ በጥዋቱ ተሰብሮ እንዲቀር በዕድሜ ሁሉ ሲያላግጡ ነበር። እንዴት ዶር አብይ አህመድ 14 ዓመት ትግል ውስጥ ገባ የሚል ታሪክ አዳመጥን የሚል የማጣጠል ተግባር ሁሉ ተደምጧል። ለውጡ ከስቶ፤ ለውጡ መክኖ ወይንም ተሰብሮ ባልታወቀ አቅጣጫ እንዲያመራ ነበ

".... ፈራጄን እለምን ነበር"

ምስል
„ፃድቅ ብሆን ኖሮ አልመልስለትም ነበር፤ ወደ ፈራጄም እለምን ነበር“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፲፭) ከሥርጉተ©ሥላሴ 21.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ትር                 አለች   ብር           ማለች     ንር~~~~~ መታች     ውርር ዘፈነች ፍርፍር ጨፈረች ስርስር ኮለኮለች ብርብር ለበሰች ንህርር ጣመች ሳቀች ተፍነከነከች ፍርፍር አስክትል አጣጣመች ጥመር ~~~~~~ አለች                        ተዋህደች                          ተቀባች።                           ፈሰሰች-ቀለጠች ተ~~~~~~ለ~~~~~~ሰ~~~~~~ነ~~~~~~ች ሃሴትን ቀለበች አምሳልን ተቀኘች። ·          ተጣፈ መሰከረም 24 ቀን 2002 ዓ.ም ትንሿ አንደልፊንግን ባድ።     እርእሱ ተለሰነች ነው ።                ፍቅር የእውነት ብር አንባር ነው፤ ሌብነትም የዕብለት! የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ሰንበት።

ደባ ...

ምስል
ጽልመታዊ-ቅብብሎሽ          *** „እግዚአብሄር ቁጣውን አይምልሰም፤ ከእርሱ በታች ረዓብን የሚረዱ ይዋረዳሉ“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፲፫) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 21.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ)               ቅብብሎሽ                 ለጥፈት-ግጥግጦሽ                   ለምክነት-ምልልሶሽ                      አሪዎሳዊ-ድግግሞሽ                        ጨለማዊ-ድርብርቦሽ።                             ማቅ አልባሽ                                ጽልመታዊ-ጥሎሽ።                                    ጽንፋዊ-ትምክኽቶሽ                                      ደመናዊ-ህልሞሽ።                                         ዬሳዖል-መንትዮሽ ቅልሞሽ፤                                            ደባን አምራች ቅብብሎሽ … ·          ተጣፈ ጥቅምት 22 ቀን 2002 ዓ.ም ሲዊዘርላንድ ·         ተስፋ መጽሐፌ ላይ ለህትምት የበቃ። ዕውነት ያሸንፋል! የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ሰንበት።

ዕውነት!

ምስል
ት ታ ያ ለ ሽ „ስለዚህም አፌን አልከለክልም፤  በመንፈሴም ጭነቀትን እናገራለሁ፤ በነፍሴ ምሬት በኀዘን አንጎራጉራለሁ።“ (መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፯ ቁጥር ፲፩) ከሥርጉተ ©ሥላሴ 21.07.2018 (ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ) ት ታ ያ ለ ሽ     *** ቀና አትይም ...         ትጎብጫለሽ። የለሽ ሲባል ...         ትገኛለሽ። ሞተች ሲሉም ...         ትነሻለሽ። አፈ ታሪክ ...         እልም አይደለሽ። ቁልጭ ብለሽ         ትታያለሽ። ሚዛን ዕውነት...          ትፈረጃለሽ። ለዝንታዓለም፣ ለአንችነትሽ ...           ... ትቆሚያለሽ!                                                          ·         ሥጦታ ፣ ...       የግንባር ሥጋ ለሚሆኑ ጽኑ ወገኖቼ።       1985 ዓ.ም ድል ገብያ ገብርኤል-አዲስ አበባ       ዕርዕስ ምር በመምህርት ወ/ሮ ካሳነሽ ቢሆነኝ። ·         ተስፋ መጸሐፌ ላይ ልህትምት የበቃ። ዕውነት ያሸንፋል! የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ሰንበት።