".... ፈራጄን እለምን ነበር"
„ፃድቅ ብሆን ኖሮ አልመልስለትም
ነበር፤
ወደ ፈራጄም እለምን ነበር“
(መጽሐፈ እዮብ ምዕራፍ ፱ ቁጥር
፲፭)
ከሥርጉተ©ሥላሴ
21.07.2018
(ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ)
ትር
አለች
ብር ማለች
ንር~~~~~ መታች
ውርር ዘፈነች
ፍርፍር ጨፈረች
ስርስር ኮለኮለች
ብርብር ለበሰች
ንህርር ጣመች
ሳቀች ተፍነከነከች
ፍርፍር አስክትል አጣጣመች
ጥመር ~~~~~~ አለች
ተዋህደች
ተቀባች።
ፈሰሰች-ቀለጠች
ተ~~~~~~ለ~~~~~~ሰ~~~~~~ነ~~~~~~ች
ሃሴትን ቀለበች
አምሳልን ተቀኘች።
- · ተጣፈ መሰከረም 24 ቀን 2002 ዓ.ም ትንሿ አንደልፊንግን ባድ።
- እርእሱ ተለሰነች ነው።
ፍቅር የእውነት ብር አንባር ነው፤ ሌብነትም የዕብለት!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ሰንበት።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ