የአትሌት ሲሳይ ለማ #አብነትነት ትውልዱ፤ የፖለቲካ ድርጅት መሪወች ምን ይማሩበታል?
የአትሌት ሲሳይ ለማ #አብነትነት ትውልዱ፤ የፖለቲካ ድርጅት መሪወች ምን ይማሩበታል? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ግን እንዴት ሰነበታችሁልኝ ማህበረ ቅንነት? ደህና ናችሁን? ሰሞኑን ተጠፋፋን። የዘንድሮን ኦሎንፒክ ብዙም አልተከታተልኩትም። ምክንያቴ ውዝግቡ አውሎማ ስለነበር ብቻ ሳይሆን መክፈቻው ላይ የነበረው ሁነትም ብዙ በትጋት እንድከታተለው አልገፋፋኝም። የሆነ ሆኖ የሴቶቼ 10 ሺን፤ የወንዶች ማራቶን እና የሴቶች ማራቶን ተከታትያለሁኝ። በውድድር ማሸነፍ እና መሸነፍ እኩል ዕውቅና ሊሰጣቸው ይገባል ብዬ አምናለሁ። ድካሙ #እኩል ስለሆነ። በልፋት፤ በጥረት የሚገኝ መሸነፍም ቢመጣ ከባለ መዳሊያው ጋር እኩል ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል ባይ ነኝ። አሰልጣኞችም ቲሙም እንደሚያስገኙት ውጤት ሊመዘኑ ይገባል ባይም ነኝ። አራቱ ኮከብ አትሌቶች መዳሊያ ያስገኙት በዛ ውዝግብ ላይ ሆነው ነው። ይገርማል። እንደምን ተረጋግተው ለድል እንደበቁ ሚራክል ነው - ለእኔ። የውስጥ ሰላም ከሌለ የጎረስከውን እህል እንኳን በቅጡ አጣጥሞ መዋጥ ያቅታል። በአፍህ ውስጥ ከርታታ ስደተኛ ይሆናል። ይተናነቅኃልም። አትሌቶች ተሰናድተው ሄደው ግን የውድድር ዕድል ተነፍጓቸው ሲመለሱ፤ የተፈቀደላቸውም አሰልጣኛቸውም ግዳጃቸውን ሳያጠናቅቁ #ተመላሽ ሲሆን፤ በቀጥታም ይሁን በተጠባባቂነት የተመረጡትም ተመላሽ ሲሆኑ በራሱ በቀሪ ተወዳዳሪወች ላይ ሊያመጣ የሚችለው #ተጽዕኖ ከባድ ነው። ተስፋቸው ይኮማተራል። አትሌቲክ ብቻ ሳይሆን ስፖርት የአንድ አገር #የውጭ #ጉዳይ ሚር ማለት ነው። ኢኮኖሚካሊም የሚክስ፤ ለተሳታፊወች የመኖር ዕድላቸውን ቧ አድርጎ የሚከፍት፦ ታሪክን በዓለም አደባባይ የሚያበጅ ልዩ አርት ነ...