ይድረስ ለማከብረዎት ለብ/ ጄ/ አሳምነው ጽጌ ።
ይድረስ ለማከብረዎት ለብ/ ጄ/ አሳምነው ጽጌ ባህርዳር። „ወርቅና ብዙ ቀይ እንቁ ይገኛል የእውቀት ከንፈር ግን የከበረች ጌጥ ናት።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፳ ቁጥር ፲፭ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.01.2018 ከእማ ዝምታ - ከሲዊዝሻ። · መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=Swe0gQaJ8FU ETHIOPIA - '' አርበኞች ግንቦት 7 የውሸት ፖለቲካ እየተጠቀመ ነው። ' ' ቅሬታ አቅራቢ የግንባሩ ወታደር - NAHOO TV Nahoo TV Published on Jan 5, 2019 ጤና ይስጥልኝ የማከብረዎት ብ/ጄ አሳመንው ጽጌ እንዴት ሰነበቱ? ደህና ነዎት ወይ?እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰዎት። መታመን እንዳይደርቅ አስቸኳይ ምላሽ ቢሰጥበት መልካም ነው ለጥያቄዬ ... ከዚህ ሩህሩህ ዘመን በላይስ ምን ይናፍቃል? ያላዩት አገር ካለሆነ በስተቀር? · ምክንያታዊ ጥያቄ በትህትና … ግን የግድ መልስ ሊሰጥበት የሚገባ። አንድ ቃለ ምልልስ አሁን አዳመጥኩኝ በናሆ ቲቪ። በግዳጅ ጊዜ ብዙ ፈተና ስላለ አብዛኛ...