ኡምንሃጀር በፍሬ ነገር ሰከነ!

ዛሬ ከፍሬ
„የሰማነውን ነገር ማን አምኗል?“
ትንቢተ ኢሳያስ ፶፫ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ ሥላሴ Sergute Selassie
07.01.2018
ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ።




ዛሬ ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኡመንሀጀር ደንበር ላይ የሰላም ቡና ጠጥተዋል። በዚህ ሥርዓት ላይ ዶር ገዱ አንደርጋቸው እና ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤልም ተገኝተዋል።

የቅዱስ ዮሖንስ ዋዜማን በሰባዕዊ ጉዳዮች ላይ አውለው ዕለቱን በዛለ - አንበሳ ላይ ሰናይን የወረበ ጊዜ ያሳለፉት ጠ/ሚር አብይ አህመድ የገናን ባዕል ዋዜማ በቅድስት እመት ዘውዲቱ መሻሻ የልጆች የመርጃ ማዕከል ከቀዳማዊት እመቤት ጋር በመሆን አሳልፈው ገናን ደግሞ ኡሙናህጀር ላይ ፍቅርን አብብልኝ በማለት ከፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተገኝተዋል። በዚህ ዕለት ዶር ገዱ አንዳርጋቸው እና ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኤኬኤልም ህሊናዊ ፈተና ተሰጥቷቸዋል።

ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ዕውነት ለመናገር ብሄራዊ ባዕላትን ኤርትራን አልባ ማሳለፍ ጭንቅ  የሆነባቸው ይመስላል። ብቻ ሩቅ ናቸው በጣም። በአንፃሩም ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ናፍቆት ያለባቸው መሆኑን በሚገባ ተረድቻለሁኝ። ተመስገን! ይህ የብልህነት አዲስ ጥበብ ከወትሮው የተለዬ ባለጥልፍ ነው የኡምናህጀሩ ዉሎ እንዲህ ገርበብ አድርጌ ልተወው።  

ለመሆኑ በጠ/ሚር አብይ አህመድ ህሊና ውስጥ ምን ዓይነት መንፈስ ይሆን ያለው? ለመሆኑ በእሳቸው የዱብዕዳ ዘውትራዊ ዜና ነገን ማሰብ እንችል ይሆን? አቅም አለን? ዓለምንም እኮ በእሸታዊ ዜና አንበሸበሹት እኒህ አሜኑ።

አቤት! ከእኛ የተፈጠሩ ባይሆን ስንት መጸሐፍ ይጻፍላቸው ነበር። ዶር አብይ አህመድ በዓላትን አስተካው የሚያደርጓቸው እንዚህ ወሳኝ ጉዳዮች የትኛውን ኢትዮጵያ ቢመኙ ይሆን? ሌላ ቀን በዝርርዝር ብመለሰብትም ዛሬ ግን ይህ የምለጥፈው ሊንክ ትንሽ ሚስጢር ሹክ ይላችኋዋል  የርቀት መለኪያውን ታገኙት ይሆን? እስቲ እናንተም ፈተና ላይ ተቀመጡ? … ካልፈታላችሁ ግን ውቾቼ ዕድምታ ፈቺዎች ዘንድ መገስገስ ነው….

ብቻ የሰቲት የአብደራፊ፣ የኡምንሃጀር ነገር ሲነሳ ብዙ ሽው የሚሉኝ ነገሮች አሉብኝ። እኔ ብቻ ሳልሆን መላ ቤተሰቤም  …

ተከዜ ሆይ ማማይ …
የናፍቆቴ ሲሳይ ልበለውን? …  

v የዛሬ ፍሬ ስክነት!

/ / አብይ በኡመራ ኤርትራ Ethiopia Abiy Ahmed

/ / አብይ የኤርትራት ድንበር በኡመራ በኩል ከፈቱ Ethiopia Abiy Ahmed

https://www.youtube.com/watch?v=Zaq1jpEZ2ro

/ / አብይ በኡመራ ኤርትራ Ethiopia Abiy Ahmed


v የርቀት መለኪያ።

Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!


ሰላም የትውልድ ፈርጥ ነው!
ፍቅር ትውልድን ያበጃል!

የኔዎቹ ኑሩልኝ!
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።