በበታችነት ቀውስ ማዕበል ውስጥ ተኮትኩቶ ያደገው የአብይዝም አንዱ ባላንጣ አማርኛ ቋንቋ ነው።
በበታችነት ቀውስ ማዕበል ውስጥ ተኮትኩቶ ያደገው የአብይዝም አንዱ ባላንጣ አማርኛ ቋንቋ ነው። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" የኢትዮጵያ #አልማዝ ፤ የአማራ ዘመነ ሥልጣኔ #አውራ ፤ የአፍሪካ #ፒላር ብቸኛ ባለ #ፊደል በኽረ ልጅ፤ የዓለም ቋንቋ ጀርጋዳ #ማህበርተኛ ፤ ቃናህ #ቅኔ ፤ ገጽህ #ፃዕዳ ፤ ዕንቁ አማርኛ ቋንቋ #አርበኛው ፤ #ሳተናው አማርኛቋንቋ በቀናተኛው ማህበረ ኦነግ አብይዝም በጠላት እጅ በመውደቅህ ባዝንም፦ ቀንህ #የማይመሽ ፤ ዘመናይነትህ #የማይወይብ ፤ ሥልጣኔህ #የማይደበዝዝ መሆኑን ሳስተውል እጽናናለሁ፤ አይዞህ የእኔ #አጤ ጃርታዊው ሥርዓት በገባበት እግሩ በራር ስንብት ይሰናበታል ሂደት ቀጣይ ነውና፤ አንተ ግን #ዘንካቴው ደመ ግቡው የአማርኛ ቋንቋ፥ በዓለም ሁሉ #ከብረህ ፤ #ጎልተህ ፦ #ጸድቀህ ትዘልቃለህ #ሐዋርያ ነህና። #እንኳን ተፈጠርክ፤ እንኳንም ተወለድክ፤ የእኔ ልዩ ፍጹም ልዩ #ድንቅ ! https://www.youtube.com/watch?v=NOuP929Y3RU "የጸደቀው የትምህርት ፖሊሲ ሀገር አፍራሽ ነው - ዶ/ር አዳነ ካሳ" የእኔወቹ እንዴት ናችሁ? ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 01/02/2025 ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።