በበታችነት ቀውስ ማዕበል ውስጥ ተኮትኩቶ ያደገው የአብይዝም አንዱ ባላንጣ አማርኛ ቋንቋ ነው።

 

በበታችነት ቀውስ ማዕበል ውስጥ ተኮትኩቶ ያደገው የአብይዝም አንዱ ባላንጣ አማርኛ ቋንቋ ነው።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
 
 
 
 
 
 
 
የኢትዮጵያ #አልማዝ፤
የአማራ ዘመነ ሥልጣኔ #አውራ፤
የአፍሪካ #ፒላር ብቸኛ ባለ #ፊደል በኽረ ልጅ፤
የዓለም ቋንቋ ጀርጋዳ #ማህበርተኛ፤
ቃናህ #ቅኔ፤
ገጽህ #ፃዕዳ፤ ዕንቁ አማርኛ ቋንቋ #አርበኛው፤
#ሳተናው አማርኛቋንቋ በቀናተኛው ማህበረ ኦነግ አብይዝም በጠላት እጅ በመውደቅህ ባዝንም፦
ቀንህ #የማይመሽ፤
ዘመናይነትህ #የማይወይብ፤
ሥልጣኔህ #የማይደበዝዝ መሆኑን ሳስተውል እጽናናለሁ፤
አይዞህ የእኔ #አጤ ጃርታዊው ሥርዓት በገባበት እግሩ በራር ስንብት ይሰናበታል ሂደት ቀጣይ ነውና፤
አንተ ግን #ዘንካቴው ደመ ግቡው የአማርኛ ቋንቋ፥ በዓለም ሁሉ #ከብረህ፤ #ጎልተህ፦ #ጸድቀህ ትዘልቃለህ #ሐዋርያ ነህና።
#እንኳን ተፈጠርክ፤ እንኳንም ተወለድክ፤ የእኔ ልዩ ፍጹም ልዩ #ድንቅ!
"የጸደቀው የትምህርት ፖሊሲ ሀገር አፍራሽ ነው - ዶ/ር አዳነ ካሳ"
የእኔወቹ እንዴት ናችሁ?
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
01/02/2025
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።