ልጥፎች

ከኤፕሪል 19, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ሬሳ² አብረን እንቅበራቸው።

ምስል
  ·        ሬሳ² አ ብረን እንቅበራቸው።   ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“ (ትምህርተ - ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17) ·        ሬሳ xሬሳ= ሬሳ² ·        የ ሙታን ማህበር። አብረን ብንቀብራቸው ከተቀበረው የ አማራ ቀን ጋር ደስ ይለኛል። ኑረውም አላመረባቸውም ማህበረ የቁም እንቅልፍ። ሎሌነትም አለው አይነት፤ ግርድናም አለው አይነት። ባርነትም አለው አይነት። እንደምን ለድንጋይ ዘመን ጠቀራ እንደዚህ የ እንብርክክ እንደሚሄዱ ይገርመኛል። ለነገሩ ሙጃ ለከብት እንኳን አይውልም እንኳንስ ለሰው ልጅ። እኔ እሬሳ ቁሙ የሚሄድ ነው የሚሰለኝ። አብረን ተረዳድተን   እንጦርጦስ ብንልካቸው ምርጫዬ ነው። ሁሉ ነገር ኦነጋዊው ኦህዴድ ከ እናኝህ ሙታን ጋር ተመካክሮ፤ መስጥሮ ኢሁንታ ተሰጥቶበት ነው የሚከወነው። እሰቡት ሬሳ ለድርድር፤ ሬሳ ለውል፤ ሬሳ ለክርክር ሲበቃ። ሬሳ +ሬሳ= ሬሳ! ማህበረ ሬሳ ሬሳነታቸውን የተሸከመው የሬሳ ሳጥን ህሊናቸው ገበርዲን እና ከረባት ሲሰቀለብት ግርም ይለኛል። እነኝህ ማሽንኮች የ ኢትዮጵያ፤ የስሜን ፖለቲካም ነቀርሳወች ናቸው። ኢትዮጵያን ከ አቶ ሌንጮ ለታ፤ ከዶር ዲማ ነግዖ ጋር ሆነው ቀበሯት። ለዚህ ነው አብረን እንቅበራቸው እምለው። ማህበረ ከንቱ ልጅም ቤተሰብም ሊኖራቸው ይችል ይሆናል። አገር ውስጥም ውጭም። ግን የታሪክ አተላ ነው ልጆቻቸው ተሸክመው ይኖሩ ዘንድ የፈረዱባ...

አብረን እንፍራ! ፍርኃት ሊገድለኝ ነው።

ምስል
  ·        አብረን እንፍራ! ፍርኃት ሊገድለኝ ነው። ዕለተ ሰኞ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“ (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)   ·        ቆ ራጣ ትህትናዊ ማሳሰቢያ።   ወዶቼ ዛሬ ማዕዶተ ጠበቂ ነው። የቀናው አጀንዳ ሁሉ አሰሳም፤ ዳሰሳም የሚካሄድበት። ቅን እና ቀና ቀን ነው። ድካም እስከ ገደበኝ ድረስ እሰራለሁኝ ዕናባዬን ዋጥ አድርጌ። ዕንቅልፍም ቢያንገላጅጀኝም። ስለሆነም አብራችሁኝ ሁኑ ስል በትሁት መንፈስ እጠይቃለሁኝ።   ስዘገይ ፖስት ሳደርግ፤ ፎቶ ስጨምር ስቀንስም ግር እንዳይላችሁ። ኮንፒተሬም ስልኬም ጤናቸው እንደ እኛው ከታመመ ወር ሊሆናቸው ነው። ስለዚህ ቅልጥፍናዬ እንደ ወትሮው ላይሆን ይችላል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።     ·        ፍርኃቱ ሊገድለኝ ነው።   አዲስ አበባ ላሉ የ አማራ ሊቃናት፤ የተዋህዶ ልጆች ስጋት አለብኝ። ይህ ስጋቴ አጣኜ፤ ካራቆሬ ከነደዱ በኋላ ነው የተከሰተብኝ። እስር ቤት ያሉ የቲም እስክንድር አባላት የቤተ መንግሥቱ ጫካ ከወለጋው ጫካ ጋር ተባብሮ እስር ቤቱ ተሰብሮ ተወሰዱ እንዳይባል በስጋት ነው የሰነበትኩት። ፈርቻለሁኝ። በተጨማሪ ለአቶ ልደቱ አያሌው፤ ለኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ ለዶር ደሳለኝ ጫኔ፤   አቶ ክርስትያን ታደለም ወዘተ እንዲሁ ፈርቻለሁኝ። ሽፍታው ተስማምቶ እንዳያ...

ውጽፍተ ወርቅ ሆይ እባክሽን ተለመኝን?

ምስል
  ·        ው ጽፍተ ወርቅ ሆይ እባክሽን ተለመኝን?   ዕለተ ሰኞ ማዕዶተ ጠባቂ በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። „የሰው ልጅ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“ (ምሳሌ 16 ቁጥር 9)   በሰመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አህዱ አምለክ አሜን።   አንቺ የሰማይ እና የምድር ንግሥት ሆይ! አንቺ የሰማይ እና የምድር እመቤት ሆይ! አንቺ የሰማይ እና የምድር ልዕልት ሆይ! እባክሽን ድረሽላት ለ ኢትዮጵያ! እባክሽን ጠባቂ እረኛ ለሌላቸው ልጆሽ ድረሽላቸው?   አብክሽን እንባችን እሚያብስ ሙሴ ስጭን? እባክሽን አይዟችሁ የሚል የአሮን በትር ስጪን? እባክሽ የመፍትሄውን ጎዳና ቀይሽልን? እባክሽን ከ ዕንባችን ጎን ቁሚልን? እባክሽን አንቺ የንጽህና፤ የድንግልና፤ የቅድስና ብጽዕት እናታችን ሆይ ድረሽልን? መጽናናቱን፤ መረጋጋቱን አስልኪልን። ከልጅሽ ከወዳጅሽ አንድዬን ተማጸኝልን።   ·        ቅ ድስቴ ሆይ! ዕውነቱን ብነግርሽ ውስጤ አለቀ፤ ውስጤ ተጎዳ፤ አቅመ ቢስነት ይሰማኛል። ለሁላችንም አጽናኝ አረጋጊ መንፈስ ይልክልን ዘንድ ከአማኑኤል አማልጅን። አስከፍተነዋል። ደስታችን ልክ አልነበረውም። ደስታችን በቅጡ አላስተዳደርነውም። የተሰጠን ማስተዋል በውል አልተጠቀምንበትም እና ምርቃታችን ተነሳ። አብረንም ወደቀን። ኢትዮጵያ በማህበረ ዲያቢሎስ እጅ ወድቃለች። በባዕድ መንፈስ እዬነደደች ነው። እሙ እናት ዓለም፤ እናት ዓለም ሆዴ ድ...