አብረን እንፍራ! ፍርኃት ሊገድለኝ ነው።

 

·       አብረን እንፍራ! ፍርኃት ሊገድለኝ ነው።

ዕለተ ሰኞ ጠባቂ

በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና

በቢሆነኝ የተብራራ ብራ

በሰብለ ህይወት አዝመራ

ለራህብ የሚራራ።

 

„ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁኝ።“

(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ 3 ቁጥር 17)

 


·       ራጣ ትህትናዊ ማሳሰቢያ።

 

ወዶቼ ዛሬ ማዕዶተ ጠበቂ ነው። የቀናው አጀንዳ ሁሉ

አሰሳም፤ ዳሰሳም የሚካሄድበት። ቅን እና ቀና ቀን ነው።

ድካም እስከ ገደበኝ ድረስ እሰራለሁኝ ዕናባዬን ዋጥ አድርጌ።

ዕንቅልፍም ቢያንገላጅጀኝም። ስለሆነም አብራችሁኝ ሁኑ ስል

በትሁት መንፈስ እጠይቃለሁኝ።

 

ስዘገይ ፖስት ሳደርግ፤ ፎቶ ስጨምር ስቀንስም ግር እንዳይላችሁ።

ኮንፒተሬም ስልኬም ጤናቸው እንደ እኛው ከታመመ ወር

ሊሆናቸው ነው። ስለዚህ ቅልጥፍናዬ እንደ ወትሮው ላይሆን

ይችላል። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።  

 



·       ፍርኃቱ ሊገድለኝ ነው።

 





አዲስ አበባ ላሉ የ አማራ ሊቃናት፤ የተዋህዶ ልጆች ስጋት አለብኝ።

ይህ ስጋቴ አጣኜ፤ ካራቆሬ ከነደዱ በኋላ ነው የተከሰተብኝ።

እስር ቤት ያሉ የቲም እስክንድር አባላት የቤተ መንግሥቱ ጫካ ከወለጋው ጫካ ጋር ተባብሮ እስር ቤቱ ተሰብሮ ተወሰዱ እንዳይባል በስጋት ነው የሰነበትኩት። ፈርቻለሁኝ።

በተጨማሪ ለአቶ ልደቱ አያሌው፤ ለኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ ለዶር ደሳለኝ ጫኔ፤  አቶ ክርስትያን ታደለም ወዘተ እንዲሁ ፈርቻለሁኝ። ሽፍታው ተስማምቶ እንዳያሳግዳቸው። ተሰወሩብኝ እንዳይል።

ይህ የቤተ -መንግሥት ወዘተረ አራዊት መንፈስ ብዙ ነገር ነው ያደራጀው፤ ፎሌ፤ ቄሮ፤ አባቶርቤ፤ የጫካ ወታደራዊ ክንፍ፤ ስውር የከተማ ሽምቅ ተዋጊ ኃይል ሥሙ የማይታወቅ፤ በኢትዮጵያ አቅም በራሷ መዋለ ንዋይ እና መንፈስ እሷን ለማክሰም ብዙ በጣም ብዙ ሠርቷል።

የእኛ ፖለቲከኞች፤ የእኛ ጋዜጠኞች „ተረኝነት“ እያሉ ቁልቁል በሆነ የፖለቲካ ትንተና አቅም በችግሩ ልክ ጎልብቶ እንዳይወጣ አክስተውታል። በቅንንትም፤ በግርዶሽም ያሉት። ያው ሆድ አደሩ ካድሬ ቢያደርገው ብዙም አይደንቅም። ልምድ፤ ተመክሮ ዕውቀቱ ያለው ግን ሦስት ዓመት ሙሉ „ተረኝነት“ ይልኃል። የሚገኙ መረጃወች አቅም አሰባስቦ መካች እንዳይሆኖም ያደመነው ይህ የመታገዬ ማእከላዊ ጭንቅላት ስለተዘለለ ነው።  

ለዚህ ነው እኛ ሙት መሬት ላይ እነሱ ገዢ መሬቱን በሁሉም ዘርፍ እዬተቆጣጠሩ የሚገኙት። ሩጫ አለ ግን ከችግሩ አስኳል ላይ ያልተነሳ። መባከን አለ የችግሩን መነሻ እና መድረሻ ላይ መነሳት የተሳነው።

ለዚህም ነው ተስፋችን እዬራቀ መፍትሄው እዬተወሳሰብ የሚገኜው። ሁልጊዜ የእነ ቶሎ ተሎቤት ነው። አንድ ማህበራዊ ንቅናቄ ሲፈጠር መንፈስ ይሰባሰባል ከዛ ይበርዳል። ግጥምጥሞሽ የፖለቲካ ተጋድሎ 50 ዓመት ለገነገነ መከራ የመፍትሄ አምንጭነቱ ያው አፍሶ መልቀም ለቅሞ ማፍሰስ ነው።

በ ሰባዕዊ መብት የሚሠሩ ድርጅቶችም ሊያተኩሩበት ይገባል። በተለይ ካቴና ላይ ባሉ ወገኖቻችን ሌላ ተጨማሪ ሰቆቃ እንዳያስተናግዱ ሊታሰብበት ይገባል። ፈጣጣ፤ ካህዲ፤ ሙልጭ ያለ አጭበርባሪ አመራር ነው ኢትዮጵያ ያላትና።

እባከዎት እማክብረዎት ኮሚሽነር ዶር ዳንኤል በቀለ ይህን ጉዳይ ባሊህ ይበሉት ስልት በትህትና አሳስባለሁኝ። እስረኞቹ ሊታገዱ ይችላሉ። ትናንት አዲስ አበባ ፈንጅ ፈንድቷል ሰምቻለሁኝ። ከዚህም የከፋ ነገር እጠብቃለሁኝ። የቤተ መንግሥቱ መሰናዶ ይኸው ነው እና።

እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

 


ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

19.04.2021  

ጎዳናዬ የኢትዮጵያን ትንሳኤ መናፈቅ ነው።

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።