ልጥፎች

ከኦክቶበር 4, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጥርጣሬ ማምረት ለውጡን አይጠቅመውም።

ምስል
የማይጠቅም። „እንግዲህስ እነግርህ ዘንድ እንደ ባለ አዕምሮ ሰው ቁም አለኝ።“   መጽሐፈ ዕዝራ ሱታኤል ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፵፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 04.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ሳተናው ላይ ስገባ አንድ ጹሑፍ አገኘሁኝ። ጠቅላለ መንፈሱ ቢጠቅም መልካም ነበር። ግን የማይጠቅም አስተሳሰብ ስላለው ትንሽ ማለት ፈልግሁኝ። የሚጠቅመውን አልነካካውም፤ አይጠቅምም የምለውን ሐረግ ብቻ ነው የማነሳው። አግረ መንገዴን አብን ስለተነሳ አንድ ነገር አያይዛለሁ፤ መንፈሱ በቀጥታ ርስቱ አህቲነት ስላለው። መቼም በአብን ላይ  ያለው ማዕት ብአዴን/ አዴፓ ላይ ተሰውሮ የተያዘ መከራ ስለመሆኑ ልብ ሊለው ይገባል አዴፓ/ ብአዴን።  https://www.satenaw.com/amharic/archives/65486 የሐዋሳው የኢህአዴግ ጉባኤ እና የለውጥ ሂደቱ ፈተና ! – ኤርሚያስ ለገሰ ፤ ·        የተከበረ ው ጸሐፊ አቶ ኤርምያስ ለገሰ እንዲህ ይላል…   „ የቀድሞው ብአዴን የአሁኑ አዴፓ ከህውሃት ጋር በጠላትነት ከመፈራረጃቸው ባሻገር ጨዋታቸው ኢኮኖሚስቶቹ ” የአውራ ዶሮ ጠብ ” (Chicken Games) መሆኑ በግልፅ ወጥቷል። ለህውሓት ከአዴፓ ይልቅ የአብርሃ ደስታ አረና ፓርቲ ወዳጁ ነው። ለአዴፓ ከህውሓት ይልቅ አብን ወዳጁ ነው። ልዩነታቸው እኔ የወከልኩትን ሕዝብ የበለጠ የሚጠቅም አጀንዳ አለኝ የሚለው ላይ ነው። በሀሳብ መተጋገዝ ካየነው ለዶክተር አቢይ አህመድ የሚቀርበው ዶክተር ደብረፂዮን ሳይሆን ...