ልጥፎች

ጥበብ ማለት ነገን ማሰብ ነው።

ምስል
ጥበብ ማለት ነገን ማሰብ ነው። „መባህን አግባ አስበህ ስንዴህን አግባ፤ የተቻለህን ያህል     መሥዋዕትነትህን አብዝተህ አቅርብ።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፲፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 04.10.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ ውዶቼ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የኢህአዴግን ጉባኤ ስከታተል። የእህት ነው የሚባሉትንም  የእነሱንም እንዲሁ። የአንዳቸውንም ጉባኤ ተከታታይ አላውቅም። እንቅልፍ ክኒን ቫልዬም መግዛት አያስፍልገኝም ነበር። ለውሸትም መጋዝን ቤት አልነበረኝም። አሁን የሁሉንም ተከታትያለሁኝ። ትግራይ ላይ አንዲት ቀና ሴት ወደ ክልሉ ምክር ቤት ተመርጠዋል። ጤነኛ መንፈስ ነው ያላቸው። ከሁሉም ትግራይ ያሳዝናል። አሁንም በገመድ ተጎተት እዬተባለ ነው። ለውጥ ናፈቀው ግን ተገደበበት። ወደ እርእስ ጉዳዬ ስገባ ማሰብ ጥሩ ነገር ነው። ጥበብ ማለትም ነገን ማሰብ ማለት ነው። ለዛሬ መገኘት ትናንትን መርሳት ማተበ ቢስነት ነው። ዛሬን ለማግኘት የቀድሞው ጠ/ ሚር የነበሩት አቶ ሃይለማርያም ደስአለኝ ያደረጉት መልካም ነገር ሊረሳ አይገባውም። በሌላ በኩል ም/ጠ ሚር አቶ ደመቀ መኮነን የወሰዱት እርምጃ ደግሞ ራስን መስጠት ብቻ ሳይሆን የአማራን ህዝብ ታሪክ፤ ትውፊት፤ ትሩፋት፤ ዕድል፤ የሥነ - ልቦና ልዕልና፤ ተጋድሎ፤ እና ትንሳኤ አሳለፍው ነው የሰጡት። የድርጅቱንም የቀድሞውን ብአዴን የዛሬውን አዴፓንም ዕንቁ ተስፋውን አሳልፈው ፈቀደው ነው የሰጡት። ማድረግ የሚቻለው ሥልጣን ሲኖር ነው። ክብሩ መጎሱ የተለዬ ነው። ያን አልሻም ማለት መቼም ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ድርሳን  ያጽፋል።   ይህን ዕድልን አሳልፎ መስጠት ለዛውም ሲነሪቲው እዬፈቀደ፤ መርሁ እዬፈቀደ ፈጽሞ በህልም የማይታሰብ ታምራዊ ገድል ነበር። ይህም ብቻ አይደለም

ገለማኝ/ ግጥም

ምስል
„የሚመካ ግን በጌታ ይመካ እግዚአብሄር የሚያመሰግነው እንጂ ራሱን የሚያመስግን እርሱ ተፈትኖ የሚወጣ አይደለም።“ መልክት ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፲፯ እስከ ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 03.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ገለማኝ         *    አለኩ ተጓዳጅ           ተጋፊ መጂ ገለማኝ ነ ጋ ጅ።        ማተበ - ፈት- ትእግስት ፈጅ            ይሉኝታ ቢሰ መጅ።              ስውረ - ህሊና፣ ውላጅ አረም የበላው ደጅ።            ጥቅምን፣ ... አሳዳጅ                ግላዊ አሸርጋጅ።                                                                                                                                                                                              ·         ውል መጸሐፍ ለህትምት የበቃ።    v    ተጻፈ፣--- ሰኔ 3 ቀን 2001 ዓ.ም  ሄርሽን ሆቴል - ሲዊዘርላንድ ·                                                                                                                             በቃችሁ ይበለን!                                                              ቅኖችን ያለምልምልኝ፤                                                    ጠማሞችን ያቃናልን አዶናይ።

የፊደል ሥህን።

ምስል
„ነገር ግን በሞኝነት እላለሁ፤ ማንንም በሚደፍርበት እኔ ደግሞ እደፍርበታለሁ። ዕብራውያን ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ። የአብርሃም ዘር ናቸውን? እኔ ደግሞ ነኝ። የክርስቶስ አገልጋዮች ናቸውን? እንደ እብድ ሰው እላላሁ፤ እኔ እበልጣለሁ በድካም አብዝቼ፤ በመታሰር አትርፌ፤ በመሞት ብዙ ጌዘ ሆንሁ።“ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልክት ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፲፩ ከቁጥር ፳፪ እስከ ፳፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 03.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ሀ.          የኪዳን ዘለበት                                 የመኖር ሰንሰለት ለ . ታማኝነት - መዳህኒት            ስክነት የፍጽምና - ክብረት።                  መለከት               ተግባረ - ማህሌት           ሐሤት አንድ ለአንድ አብነት።                      በአህቲ ስብኃት።              ሐመረ-ህብረት                      ለይኩነ- ሰናይት ቤተ- የምኽረት።                             በአህድዮሽ ሕይወት።             የመተሳሰብ ገነት                           ሥምረት ንጹህ፣ ፍቅረ-ብሥራት።                                        ዕ             የሦስት ጉልቻ ሰገነት                                  ር                     በባለ ማርዳ - የውስጥ ዕምነት                 ገ                                            ጽናት እስከ ዕልፈ .---- ት ። አነባቡ ... ከላይ ከ“ሀ“ ተነስቶ ወደ ታች ይወርድ እና

የትውፊት አብራክ /ግጥም/

ምስል
„ስለ ነፍሳችሁ በብዙ ደስታ ገንዘቤን እከፍላለሁ፤ ራሴን እንኳን እከፍላለሁ፤ ከመጠን ይለቅ ብወዳችሁ በዚህ ልክ ፍቅራችሁ የሚያንስ ነውን?“ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልክት ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ከ፲፭ እስከ ፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 03.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።       የትውፊት አብራክ        ***                     ክክ    ክክክ                  ክክክ ልክክክ                          ክክ ስልክክ                              ክክ የጎበዝ ክክ ሙክክ!                  ክክ                አይልም ሹልክ!            ሙክክ                             ያስኬዳል በእንብርክክ!                                      ጠላትን አሳክክ                                      የጥበት ን ንክ                                      ያሳውቃል ልክ!                                      ደሙ አለው ውብ መልክ!                                      የትውፊት ውል አብራክ!                                                                                                                                                                                                    ·         ውል መጸሐፍ ለህትምት የበቃ።            ተጻፈ፣--- ሰኔ

የሥነ ቃል ላሂ።

ምስል
„ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው። ሁሉ ነገር በሁለትና ሦስት ምስክር አፍ ይጸናል።“ ወደ ቆረንቶስ ምዕርፍ ፲፫ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 03.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ የትዝታ እፍታ      ሲመጣ          በአንድ አፍታ ለታታ          ልቤ በኃይል መታ።      ለታታ                         () መንፈሴ ተረታ                        ሳይሰጠኝ ተርታ    በታታ         የትዝታ ህቅታ።       በታታ     ብርታቴ ተፈታ                  ጽናቴ ተረታ                                     ሳልደርስ ለገበታ                         ከርታታ።                                                                        ·         እርእስ የትዝታ ህቅታ። ·         ውል መጸሐፍ ለህትምት የበቃ።            ተጻፈ፣--- ሰኔ 3 ቀን 2001 ዓ.ም  ሄርሽን ሆቴል - ሲዊዘርላንድ   v ውዶቼ የሥነ ግጥሙን መጠኑን ለመጨመር ዲዛይኑ ስለሚበላሽብኝ እንዲሁ ትቼዋለሁኝ። ለንባብ ደቀቅ ቢልም ረጅም ባለመሆኑ አይከብድም የሚል እምነት አለኝ ብዬ አስባለሁኝ።   ·         በቃችሁ ይበለን! ቅኖችን ያለምልምልኝ፤ ጠማሞችን ያቃናልን አዶናይ።

ግጥም።

ምስል
„መከራ ከሚያጽኑባቸው ሰዎች እግዚአብሄር እንደ ወደደ ያድናቸው ነበር።“ መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ 03.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ሲነጥቁ       ሳያላምጡ               መዋጡ፣                    ነገረ ፈጂ- የጣልቃ ፈንጂ                                     የምላስ መጂ። ·         እርእስ የምላስ መጅ። ·         ውል መጸሐፍ ለህትምት የበቃ።            ተጻፈ፣--- ሰኔ 3 ቀን 2001 ዓ.ም  ሄርሽን ሆቴል - ሲዊዘርላንድ ·         በቃችሁ ይበለን ቅኖችን ያለምልምልኝ፤ ጠማሞችን ያቃናልኝ አዶናይ።

ሥነ ግጥም፤

ምስል
ዝምም ዝምዝም ዝምዝምም ዝምምዝምም ዝምምምምምዝም ዝምምምምምዝምምም ዝምምምምዝምምምምምም እምምምዝምዝምምምምምምም መዝመምመዝመምዝምምምምዝም ዝምም- የተስፋ ህመም  ራዕይን አናዝመምም አናሰምም ስንፍናን አናስታምም፣ ዛሬን እናስቀድም፡  በድርጊት እናቅልም። ድክመት አንደጋግም  አንጋደም፡ ትግል እንዳይለግም በታቱ አናዝግም። ·         እርእስ አናዝግም ። ·         ውል መጸሐፍ ለህትምት የበቃ።            ተጻፈ፣--- ሰኔ 3 ቀን 2001 ዓ.ም  ሄርሽን ሆቴል - ሲዊዘርላንድ በቃችሁ ይበለን  አዶናይ ቅኖችን ያለምልምልኝ አዶናይ፤ 

የሃይማኖት ተቋማት የህዝብ ሰቆቃ አጀንዳቸው አይደለም።

ምስል
ሃይማኖት ምንድን ነው? „ልጄ የበደልከው በደል የሳትከው ነገር አንዳለ እወቅ  ከዚህ በኋዋላ ዳግመኛ አትበድል ስለ ቀደመው ሃጢያትህ ንስሓ ገብተህ ተቀመጥ።“ መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ© ሥላሴ 02.10.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እኔ ውዶቼ ስለ ሃይማኖት ፍልስፍና ልናገር አይደለም። ይህ ጸጋ የአቨው የሃይማኖት ሊቃውንት መክሊት ነው። ሃይማኖት ማለት ምንድን ነው ብዬ የምጠይቀው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሃይማኖት ተቋማት ከንፈር ከመምጠጥ በስተቀር በዚህ የመከራ ቀን ከህዝብ ጎን ሊቆሙ አለመቻላቸው ሃይማኖት አለ ኢትዮጵያ ውስጥ ለማለት ከበደኝ። የእውነት ከበደኝ ሃይማኖት አለኝ ለማለትም። የእውነት ይጭነቃል። ጂጂጋ ላይ ያን ያህል ሐዋርያት ሲታረዱ፤ አድባራት ሲነዱ፤ ምዕማናን ያን ያህል መከራን ሲቀበሉ አንድም ልዑክ  ከቅዱስ ሲኖዶስ ተልኮ ሄዶ ቦታውን እስከ አሁን ድረስ አላዬም። ለመሆኑ ፕትርክና ምንድን ነው? ምዕመናን እቦታው ድረስ ሄዶ ካላጽናን? ዓምት ሙሉ መፈናቀል?  ዓመት ሙሉ በሰው ሰራሽ ችግር እንዲህ ፍዳ መክፈል። ተቆጭ የለ። መካሪ የለ። የሚገስጽ የለ። ግርጫማ ጸጉር ያለው የለ። የሚፈራ የለ። በሃይማኖታዊ ተቋማት ለተጎዱት አንዳችም ነገር አልተደረገም። ማውገዙን እማ እኛ ድሆችም እናወግዘው የለ። በቃ ሚዲያ ላይ ወጥቶ መናገር የሃይማኖት አባትነት ያሰጣልን? ሃይማኖት ለዚህ መከራ ቅርብ ካልሆነ ማን ሊሆን ነው? በዬቦታው ለቅሶ ነው። በዬቦታው ዋይታ ነው። የመንግሥት መሪዎችን አይገስፁ የሚቆጣቸው የለ፤ የሃይማኖት አባቶች ቸልተኞች እና ግድየለሾች። ለነገሩ የራሰቸው ገማና ከሆነስ? ሌላው ቀርቶ ቡራዩ ላይ እስከ 15 ሺህ ተፈናቀለ የተ