የአዲሱ ለውጥ ትሩፋት።
መንትዮሾቹ የተግባር ልዕልቶች በደግነት ማዕዶት! „የፃድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፤ ሙሉቀን እስኪሆን ድረስ እዬተጨመረ ይበራል።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 30.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። አዲሱ ለውጡ አደጋ ያመጣል የሚሉት የአባ ቆስቁስ የአቶ በረከትን የኑዛዜ መስቃ እንዲህ መናነቱን ተግባር ቁሞ ይመሰክራል። የአባ ቆስቁስ የአቶ በረከት ስምዖን ሙገት ቁሞቀርም መሆኑ እንዲህ ይታያል። ይህ ተግባር አላዛሯ ኢትዮጵያ የተፈጠረችበትን የደግነትን፤ የቸርነት ትውፊቷን አህዱ ብላ መጀመሯን ያሳያል። ሲጀመር ጀምሮ ለውጡ ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ ነው በማለት ነበር ስሞግት የባጀሁት። አዲሱ የኢትዮጵያ መንገድ ይሄውና ዛሬም የበጎ ምግባርን ተግባር ተስፋን ሰንቆልናል ... ይህ ድርጀት መቄዶኒያ በራስ አነሳሽነት ከመንገድ ላይ የወደቁ አቅመ ደካሞችን በራስ ጊዜ፤ ጉልበት እና አቅም የተጀመረ ነው። መስራቹ ቅዱስ ብቻቸውን የጀመሩት ተቋም ዛሬ እንዲህ አፍርቶ ለወግ ለማዕረግ በቅቶ ለዚህ ቀን በቅቷል። ቤተ መንግሥትም እንዲህ እንሆ ታደመበት። ወይ ጊዜ እንዲህ ትክሳለህ! ሁለት ዳጋጋውያን አንስቶች እራሳቸው ደካሞችን በማስተናገድ የተሰለፉበት ይህ የቸርነት መንገድ አዲሱ የለውጥ መንፈስ እንዲህ ቅንድስና፤ ብጽዕና ያለው መሆኑን ያመላክታል። ይህ የቸርነት ጉዞ ትንሽ ራቅ አድርጌ የዛሬ አምስት ዓመት የት ትደረስ ይሆን ብዬ ስጠይቀው „አይተሽ ፍረጂ ብሎኛል።“ እናንተም አይታችሁ ፍረዱት ልበል በተሰጠኝ መልስ መሰረትነት። የኔ ውዶች የጹሁፌ ታዳሚዎች ትንሽ ገፋ አድርገሽ ወደ 10 ዓመትስ ስለምን አለወሰድሽውም ትሉኝ ይሆ...