ልጥፎች

ከሜይ 28, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሆደ ሰፊ አይደለም። ግልፍተኛ ነው። ግልቢያም አለበት።

 የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሆደ ሰፊ አይደለም። ግልፍተኛ ነው። ግልቢያም አለበት። ግልፍተኝነቱ ደግሞ ሥልጣን ላይ ሆኖ የዲፕሎማሲ ማህበረሰቡን እንደምን መያዝ እንደሚገባው እንኳን አያውቅም። ለዘርፋ ደም የሚያፈላ እርምጃ፤ ደም የሚያፈላ ንግግር ይደረጋል። ከዛ ፀጋ ይደፋል። ፀጋ ከተደፋ በኋላ ደግሞ ልምምጥ ይመጣል። አብሶ #ካድሬወቹ #በዲፕሎማሲ #ጉዳይ ላይ #እንዳይዘነቁሉ #በህግ #ሊታገዱ #ይገባል ። ፓን አፍሪካኒስት ኢትዮጵያ ዛሬ ያለችበትን ደረጃ የማይመጥናት ላይ ናት። በሌላ በኩል #በዘርፋ #ሙያ #ጠገብ #ኢትዮጵያውያን #በነፃነት #እንዲሠሩ #ሊፈቀድ #ይገባል ። ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ። በተለይ ማህበራዊ ሚዲያ አመጣሽ ሰብዕና ረቂቁን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ላይ እንዲታቀቡ ሊደረግ ይገባል። ኢብን ሙሁራን ቢሆኑም። ኢትዮጵያ በትርፍ ተናጋሪወች ልትለካም አይገባም። ለዚህ ነው እኔ ኢትዮጵያ ለሁላችን ከብዳናለች የምለው። ለአገር ክብር ብርቱ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። ተቋም አለ። ውጭ ጉዳይ ሚር። የዳበረ ልምድ ያለው። በነፃነት ይሠራ ዘንድ ይፈቀድለት። ከዞግ እሳቤ ተወጥቶ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ2024/05/27

ስለምን???

  ስለምን??? ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ለምቾት የሚገነቧቸውን ፕሮጀክት መዋለ ንዋይ ስለምን ለዩንቨርስቲወች ድጎማ፤ ለሠራተኛ ደሞዝ መክፈል ላቃታቸው አብይ ሠራሽ ክልሎች አይመድቡም። ደቡብ ደሞዝ መክፈል ካቃተው፤ ደቡብ ዩንቨርስቲወችን መመገብ ከተሳነው ዛሬ ደቡብ ሰላም ነው ነው የሚባለው ይደፈርሳል። የማይቆም ከቁጥጥር ውጪ የሆነ አመጽም ሊነሳ ይችላል። ዳቦ ለሚጠይቁም ቀለሃ ሊታዘዝባቸው ይችላል። ችግር ደርሶ ማኔጅ ለማድረግ ከሚያቅት በእጅ ባሉ ነገሮች ቢያንስ ችግሮችን ለማስታገስ ጥረት ለምን አይደረግም። የኮሪደር፤ የጫካ፤ የሪዞልት ወዘተ እያሉ በፈንታዚ ከሚጓጓዙ። ድግሱም እንዲሁ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል። የክልል አለቆችን በአጃቢነት ከማሰለፍ የፀጥታ ኃይሎች በቂ ናቸው ጉዞ ካስፈለገ። ለነገሩ ወንበሩ ባዶ ነው ብዬ የፃፍኩት 2011 መግቢያ ላይ ነበር። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ሥርጉትሻ2024/05/27

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነት የነጠፈበት ነው።

 የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቅንነት የነጠፈበት ነው። ቅን ለሆነ ህዝብ ቅንነት የነጠፈበት ፖለቲከኛ በምን ሂሳብ ሊደማመጥ ይችላል? አይመጣጠንማ! ሥርጉትሻ2024/05/27

Zerihun and me on various Ethiopian issues ...

ምስል

ዋ! ያቺ ዓድዋ

ምስል