ስለምን???
ስለምን???
ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ለምቾት የሚገነቧቸውን ፕሮጀክት መዋለ ንዋይ
ስለምን ለዩንቨርስቲወች ድጎማ፤ ለሠራተኛ ደሞዝ መክፈል ላቃታቸው አብይ ሠራሽ ክልሎች አይመድቡም። ደቡብ ደሞዝ
መክፈል ካቃተው፤ ደቡብ ዩንቨርስቲወችን መመገብ ከተሳነው ዛሬ ደቡብ ሰላም ነው ነው የሚባለው ይደፈርሳል። የማይቆም
ከቁጥጥር ውጪ የሆነ አመጽም ሊነሳ ይችላል። ዳቦ ለሚጠይቁም ቀለሃ ሊታዘዝባቸው ይችላል። ችግር ደርሶ ማኔጅ
ለማድረግ ከሚያቅት በእጅ ባሉ ነገሮች ቢያንስ ችግሮችን ለማስታገስ ጥረት ለምን አይደረግም። የኮሪደር፤ የጫካ፤
የሪዞልት ወዘተ እያሉ በፈንታዚ ከሚጓጓዙ። ድግሱም እንዲሁ ማዕቀብ ሊጣልበት ይገባል። የክልል አለቆችን በአጃቢነት
ከማሰለፍ የፀጥታ ኃይሎች በቂ ናቸው ጉዞ ካስፈለገ። ለነገሩ ወንበሩ ባዶ ነው ብዬ የፃፍኩት 2011 መግቢያ ላይ
ነበር።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
ሥርጉትሻ2024/05/27
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ