የሰማያዊ ፓርቲ የቆራጣ የኮፒ ራይት ሩጫ ተረኛ ነው ለፍጥጫ!
የጢባ ጢቦ የኮፒ©ራይት ሽሚያ እንደ ተለመደው። „የነጎድጋድህ ድምጽ በአውሎ ነበር፣ መብረቆች ለዓለም አበሩ ምድር ተናወጠች ተንቀጠቀጠችም። ምዕራፍ 72 ቆጥር 18 ከሥርጉተ ሥላሴ 18.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።) · የእነ ጭልፊት ነገር ሞትለፍ ነው። https://www.youtube.com/watch?v=TZZCmLn_XTo Ethiopia: የኢትዮጵያ ሰንደቀ አላማ መሀል ላይ ያለዉ አርማ እንዲቀየር ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ አቀረበ የዕውነቱ ዕንብርት በሚዛን! https://www.satenaw.com/amharic/archives/59868 ሰንደቅ አላማና የአማራ ህዝብ ስሜት – ንግሱ ጥላሁንና ቢቢሲ …. ( አያሌው መንበር ) · ልሙዱ አቋራጭ። ሌብነት እንደ ትልቅ የፖለቲካ ስልትና ስትራቴጅ እዬተለመደ መጣ። እኔ በሌላ ድርጅት እንዲህ ዓይነት ኩነት አይቼ አላውቅም። ሰምቼም አላውቅም። ምክንያቱም አነሰም በዛ የፖለቲካ ድርጅት ፈጣሪዎች ሃሳብ ይዘው ነው የሚነሱት እንጂ ሃሳብ ካለው እጣዳለሁኝ ብለው አገር ሲያምሱ እና ሲያተራምሱ ተገጥሞ አይታወቅም። የአማራ ተጋድሎ እንደ መጣ በዚያው ሰሞን ተጨማሪ የራዲዮ ጣቢያ ተከፈተ የቅንጅትን መንፈስ እንጠራለን ተብሎ „ትሳንኤ ራዲዮ“ ትንሳዬ ራዲዮ ቅንጅንትን የደገፈ እና በፅኑ የረዳ ራዲዮ ዝግጅት ነበር፤ እኔም ለተወሰነ ጊዜ እርጅን ብለውኝ ሰርቼ ነበር። አሁን ታሪክ እራሱን ይደግማል እንዲሉ የሰሞኑ አቤቱ ሰማያዊ ጥድፊያ ደግሞ ይሄው ነው። ሰማያዊ አዲስ አስቂኝ ጉዳይ ለኢት...