"አማራ ማለት እዬሞተ የሚባዛ ጀግና" ወጣት አውነቱ ታዘበው።
አማራነት የዘር ሀረግ ነባቢት እንጂ የድርጎ ችሮታ አይደለም።
„ከወደዱትም አላሳጣቸውም፤ መብላቸውም
ገና በአፋቸው ሳለ፣ የአግዚአብሄር ቁጥ
መጣ፣ ከእንርሱም ከፍ ያሉትን ገደለ፤
የእስራኤልን ምርጦች አሰናከለ።“
(ምዕራፍ ፸፯ ቁጥር ፴፩)
ከሥርጉተ©ሥላሴ
18.07.2017
(ከውቢቷ ሲዊዝሻ)
የሚገርመኝ ግን ይህን የሰሙ የብአዴን አማራር እንዴት እንቅልፍ ወስዷቸው አንደ አደሩ ነው የሚገርመኝ። እነኝህ ወጣቶች ወደ ፈላስፋነትም ይወስዳቸዋል።
ሙሁሩ ወጣት አቶ እውነቱን ታዘበው እንዲህ ይለናል። „ከፊትም ከኋዋላም ጊዮርጊስ ብቻ ነው ያለኝ። አማራ ማለት እዬሞተ የሚባዛ ጀግና፤ ዝቅ ብሎ ከፍ ያለ፤ ተሸንፎ ግን ያሸነፈ ህዝብ ነው! „ አጅግ ሳሰሁላቸው ለወጣት ብርሌው አስራት ወጣት ላይችሉህ ደሜ፤ ወጣት አለነ አገኘሁ፤ ተሰማ ካሳሁን ስጋቴ አንድ ነገር እንዳያስደርጓቸው ነው። በመኪና አደጋ ወይንም በምግብ ብክለት። መቼም አላዛሯ ኢትዮጵያ መከራዋ ብዙ ነውና። ስክነታቸው፤ እርጋታቸው፤ ድፍረታቸው፤ የአነጋገር ጥበባቸው፤ የችግሮችን ዓይነት ከመሰረቱ ለማጥናት የሄደቡት መንገድ፤ የአገላለጽ ጥንቃቄያቸው፤ ቅኒያዊ ውስጣችው እጅግ ተስፋ ሰጪ ነው። እንጉልቻ ላይ ላለው ለብአዴን የምክር አገልግሎት ጽ/ ቤት የከፈቱለት ይመስለኛል። ማጣሪያ ማንዘርዘሪያ ወንፊትም።
Ethiopia - የዚህን ወጣት ጥልቅና ገራሚ ንግግር ያዳምጡ ~ ሁሉም የበብአዴን አባሎች ደጋግማችሁ ስሙት
Ethiopia - የወጣቶች መድረክ በእንጅባራ ግሩም የወጣቶች ቆይታ እንዳያመልጥዎ!|| Amara Youth ||
- ጠብታ!
ዛሬ ከንጋቱ 5.00 ሰዓት ላይ እንደ ሲዊዝሻ አቆጣጠር ከእንቅልፌ ተነሳሁኝ። ተነስቼ ቴሌቪዥን ስከፍት ይህን አገኘሁኝ። ልቤ ስለሆነም ማጠናከሪያ ልጽፍበት ተሰናዳሁኝ። እስቲነጋ ጠብቄም እንዲህ ማለትን ወደድኩኝ። አማራነትን በሚመለከት ከአማራ ታገድሎ በኋዋላ ብዙ ጹሑፈችን ጽፌያለሁኝ።
እንዲያውም መጀመሪያ ላይ በዝምታ ነበር የተከታተልኩት። ለዛውም በባዕቴ ላይ በፈነዳው በአማራ አብዮት ላይ በጫታ ቆዬሁኝ። ቁጭቴ የመጣው ውጪ አገር የተጋድሎውን መንፈስ ሙልጭ አለ ዘረፋ እና መገለል ሲመጣ፤ የወጣት ፍርህያት የማነ እና የወጣት ንግሥት ይርጋ የልዩነት አያያዝ፤ የቅዳሜ ገብያ መቃጠል ዝምታዬን ላልመለሰበት ወስኜ ተነሳሁኝ።
ከዚያ በፊት ለእኔስ ሰው መሆኔ ብቻ ይበቃኛል ነበር መርሄ። እኔ ይሄን ብልም ነጻነቴን ያስገኝልኛል ብዬ ያመንኩት ድርጅት ግን በማተቡ፤ በታማኝነቱ ሊገኝ አለመቻሉን ሳስተውል ቢያንስ ለራሴ ህልውና እና ለተበላው ዕምኔቴ ዘብ መቆም ዛሬ ካልቻልኩ ብዬ ጀመርኩት።
ከሁሉም በላይ የታሪኩ ተዳፍኖ መቅረት ውስጤ ስለሆነ ሳይቸግር ስለምን ጤፍ ብድር ይሁን እኔ ልጁ አማራ እያለሁለት ስለምን ለብዕርስ የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ ይጠመን ብዬ ተነሳሁኝ። ወደፊትም ቀጥዬ እሰራበታለሁኝ። በህይወት እስከ አለሁ ድረስ።
- · ባለቤት አልቦሹ የአማራ ወጣት ሥነ ልቦና!
ከሁሉ የሚያንገበግበኝ የአማራ ወጣት ሥነ - ልቦና እንዲቀጠቀጥ መፈለጉ ነው። ይህ መቼም የውስጥ ረመጤ ነው። በዬትኛውም ሁኔታ አማራ ወጣት ላይ ሲደረስ የሌሎችም ተብሎ ነው የሚታለፈው።
ዛሬ ላለው ህይወት ለዘራበት ኢትዮጵያዊነት አማራ እራሱን እየስገበረ በአንጋችነት ያቆዬው እንጂ በዬልቡ ተቋጥሮ የኖረውን የቁርሾ ክምር እማ ይሄው እዬታዬ ነው። ዘመን ጥሩ ነው ይዘርግፈዋል፤ ያንጠባጥበዋል። አሁን ደግሞ ቢከፋኝ ብመለስ ተሁኗል።
የሆነ ሁኖ ዛሬ ያለው መሬት ላይ የሚገኘው አማራ እንዲህ እዬጠነከረ መምጣቱ እጅግ ተስፋ ሰጪ ጉዳይ ነው። አማራን በሚመለከት እንኳንስ ትናንት ነገም ባለቤት እንዲኖረው የሚፈለግ አይደለም። እኔ እምታዘበው እንደዛ ነው። አሁን የጠለፋ መረብም ተዝርግቷል። በሥሙ የሚምሉ ግን የራስ ተሳማ ናደውን ሌጋሲ ለማስቀጠል ቆርጠው የተነሱ ጦሮ መንፈሶች ሁሉ አያለሁኝ።
በቀጣይነትም ሆድ አደር ስለማያልቅ ተለጣፊዎች ይዘጋጁለት ይሆናል። ግን ተጠማኝ ናቸው። 20ሺህ አማራ በገበረው ድል ላይ አብን ተመሠረትኩ ብሎ ሲያውጅ የሰማያዊ ፓርቲን ቅራሪ የእኔ ብሎ፤ ቁልፍ ቦታውን አስረክቦ ነው ጉባኤውን በሰማየዊ አልባሳት አድምቆ ነው። አንድነት የወደቀበት ምክንያት ይሄው ነው። ሌላም ነገ ጊዜ የሚገልጠው ገመናም ይኖራል። ተቀላቀልኩኝ፤ ተዋህድኩኝ ይለናል።
አማራ በትክክል በጠራ ሁኔታ ወካይ ድርጅት የለውም። አማራ ራሱን ችሎ እንዲወጣ አሁንም የሁሉም ስጋት ነው። ስለምን? አማራ እና ሌላው የሚታዋወቁበት መሥመር ስላለ።
ውጪ አገርም ቢሆን ትንሽ ከሌላ ዘር ቅልቅል ያላቸው ናቸው ከወጥ አማራዎች ይልቅ ተማራጮች። በሁሉም ቦታ ጥናት ሊደረግ ቢታሰብ ከዜሮ በታች ነው አማራን የማስጠጋት ሁኔታ። ወይ ቅማንት ወይንም አገው ወይንም ወይንም ትግሬ ወዘተ እንደዛ የዘር ሐረግ ካልተገኘበት ወጦች በዬተገኙበት ነው በስውር ሴራ አቅማቸው ተሰብሮና ተቀብሮ የሚገኙት።
እነዚህ ከሁለት እና ከዛም በላይ ከደም ዝርያ የተወለዱት ደግሞ የአማራን ሥነ - ልቦና ሙሉውን ለመሸከም ተፈጥሯቸው አይፈቅድላቸውም። አማራ እንደ አማራ የመንታ እናት ተንጋላ ሞትች እንደሚባለው ነው የሆነው። እሱ! ዝም በል! ከዚህ መጣ ከዛ መጣ አትበል ኢትዮጵያዊነት እስከ አቀነቀነ ድረስ ያንተ መሪ ሊሆን ይገባል ዓይነት ነው የሚሆነው። አማራን ራሱ መምራት ያቅተዋልን? አማራ ለራሱ መሪ መሆን ያንሰዋልን? አማራ የተማሩ ሊቀ ትጉሃን የሉትንም?
ሌላው እራሱም አማራ፤ አማራ ነኝ ብሎ ከመውጣት ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ዘር አልባ ነኝ ብሎ ነው የሚወጣው። ይህ ሌላው የመከራ ተራራ ነው ለአማራ የህለውና ተጋድሎ። አማራ ተጎዳ ብሎ እንኳን ለመናገር ድፈረት የለም። በማንነት ጥቃት አለ ነው። የትኛው ማንነት? ገዜጠኞችም አይጠይቁትም ዘለውት ይሄዳሉ? ሁሉም ለበዳዩ እንጂ ለተባዱዬ መከራ ያፈርበታል ወይንም ወገንተኛ አይደለም። አማራ ተጎዳ የሞል የፖለቲካ ሊሂቅ እኔ ሰምቼ አላውቅም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ተጎዳ ነው።
የሚቀረቡት ከሌላ ጋር የደም ዝርያ ወይንም የጋብቻ ዝምድና ያላቸው ናቸው። የአማራ ድምጽ ከፍተህ አማራ አይደለሁም ለሚል ሰው ሰጥተህ የአማራን ተጋድሎ የድምጽ አገልግሎት እሰጣለሁም የሚያዋጣ አይሆንም። አይመጣም። ምክንያቱም ፋክቱ ስለማያራምድ። አማራ ስትሆን ከውስጥህ የሚመጣ የቁጭት ነዲድ አለ። ያን ስሜት ያ ማይክራፎን ማስተናገድ አይችልም።
አማራነት አማራ መሆንን ይጠይቃል። አሁን እኔ እንደ ትግራይ ልጆች ልሁን ብልም፤ እንደ ኦሮሞ ልጆች ልሁን ብልም አልችልም። እንደ ኢትዮጵያዊ ልሁን ስል በዛ ህብር ውስጥ ሁሉም ተቀምሞ ሊኖረኝ ይችላል። እንደ ኢትዮጵያዊ ልሁን ስልም አማራዊ ደሜ የሰጠኝን ንጥረ ነገር ተጭኜው፤ ተጨቁኜው ሳይሆን ይዥው ከነክብሩ በእኩልነት አደላድዬው ነው።
- ፍልስ ግንዛቤ።
ሌላው አምርኛ ቋንቋ የተናገረው ሁሉ አማራ ነው የሚልም ፍጹም የተፋለሰ ግንዛቤም አለ። አማርኛ የተናገረው አማራም አማራም ላይሆን ይችላል። የወል ማንነታቸው፤ አውራ ማንንታቸው ኢትዮጵያዊነት ሊያገናኛቸው ይችላል እንጂ አማራ አማርኝ ቋንቋም ሳይናገር የዘር ሐረጉ አማራ ከሆነ አማራ ነው።
ውጪ አገር ተወልደው የሚያድጉ፤ በጉድፊቻ የሚመጡ ልጆች አማርኛ አይችሉም ግን አማራዊ ደማቸውን ግን አማርኛ ቋንቋ ስላልተናገሩ ማንም ሊሰጣችውም ማንም ሊነሳቸወም አይቻለውም። በዚህ ጉዳይ ላይም በዝርዝር በ2006 ላይ ጽፌበታለሁኝ።
ትግራይ መሬት ላይ አክሱም የተወለደ አማራ፤ አማርኛ ባለመናገሩ፤ ወይንም አርሲ በቆጂ ላይ የተወለደ አማራ አማርኛ ቋንቋ ስላልተናገር አማራ አይደለህም ሊባል አይችልም።
የዘር ሐረጉ የወላጆቹ አማራ ከሆነ። አማራ መሬት ተወልደው ያደጉት እነሳጅን በረከትም ጎንደር ተወልደው ስላደጉ አማርኛን የፍልስፍና ያህል በማወቃቸው አማራ ነህ ሊያሰኛቸው አይችልም። መከራውም ይሄ ነው ያልሆኑትን ማንነት ተሸከሙ ስለተባሉ።
ንጥረ ነገሩ ከሌላ ኮንፓውንዱን መፍጠር አይቻልም። አሁን የዶር ገዱ አንዳርጋቸው እና የዶር አንባቸው ፍለስፍና ይሄውን መንገድ ተቀብሎ የተጓዘ ነው። ይህም ብቻ አይደለም ይህን ተጫኝ መንፈስ ተቀበሉን ነው ተማህጽኖው። ማንም አይቀበላቸውም። እኔ እራሴ ኢትዮጵያዊነትም አፍሪካዊነትም አብዝቶ የሚጫነኝ፤ በሶሻሊዝም ርዮት የሰለጠንኩት፤ የሠራሁበትም። ይህማ 43 ዓመት አማራን ባለቤት አልቦሽ አድርጎ ከዘሩ ነቀለው፤ ሥነ - ልቡናውን ሸለተው።
ውጪ አገር ተሰደን ሌላ ተጨማሪ የግለት ሰድት የተበዬንብ እኮ አማራነታችን ብቻ እንጂ ጨዋነቱማ ሆነ አቅሙ ተርፎ ባይናኝም ለራሳችን የሚሆን እቴጌነት ግን ከነሙሉ ስብዕናው አለን።
እራሱ የአማራነት ፍልስፍና የተፋለሰ እና በዚህም በዚያም አማራ በወጥ አቅሙ፤ ችሎታው፤ በመክሊቱ ራሱን በቻለ ውክል እና በማንነቱ በቅሎ እንዳይጸድቅ የተፈጠሩ መስናክሎች ናቸው።
በሌላ በኩል አማራነት የችሮታ፤ የመሟካሸ፤ ይይሉኝታ የሥጦታም ቁስ ተደርጎ የተወሰደበትን ሁኔታ ባለፉት ጊዜያት ተመልክቼአለሁ። የ አማራን መንፈሳዊ የሃብት አቅም ተጭኖ የሌላ የመንፈስ አቅም ይምራህ ወንጀልም ነው። ህግ ቢኖር የሚያስከስ።
ከአማራ ተጋድሎ ዘመን በኋዋላም በፊትም በመአህድ አመራር አካልነት ውጪ አገር የነበሩት አማራ ዝርያ ብጣቂ ያልነበራቸው በግልጽ እና በይፋ የሌላ የደም ሐርግ ያላቸው እንደ ነበሩ አስተውል ነበር።
ለዚህም ነው መአህድ ፈተናዎቹ ጠንክረው እኒያ ትውልድ የማይተካቸው የሰብዕዊ መብት ተሟጋች ፕ/ አስራት ወልደየስ አጋዥ አጥተው ልክ አንድነት ፓርቲ የነጠሩ ንዑዳን ተገፍተው የዕድሜ ልክ እስራት እንደተዳረጉት እና መጨረሻ ላይም ድርጀቱ በብሄራዊ ደረጃ ፈርሶ ዛሬ እነ አቤቱ ሰማያዊ የሚንፈራሰሱበት የእውቅና መንበር የተተከለውም በዚህ የሴራ ገመድ ነበር።
በአንድነት ሆነ በመኢህአድ መከራውን ሁሉ የተሸከሙት የአማራ ልጆች ናቸው። ወደፊትም በጠራ መሥመር መጓዝ እስካልተቻለ ድረስ ኤንም ቢንም ሲንም ዲንም እንዳይከፋው የዶር ገዱ አንዳርጋቸው እና የዶር አንባቸው ልዝ ፖለቲካ የትም የሚያደርስ አይደለም። ልዝ እንጨት ወይ አይነድም ወይም አያነደም።
ሌላው የአማራ ድርጅት ፈተና በ2006 በስፋት ጽፌበታለሁኝ አማራነትን ከሶሻሊዝም ርዕዮት ጋር የማጠበቅ ጉዳይም ወጣቶ ገፍቶ ሄዶ እንዲህ መሰሉን አይዲኦሎጂዊ ነቀርሳ ጋር ፊት ለፊት ሊጋፈጠው የሚገባው ጉዳይ ነው የአማራ ተጋድሎ። ይህ መርዛማ መንገድን የተሸከሙ ባይረሶችን ነቅሎ እስከ አላስወገደ ድርስ የነገ የአማራ ትውልድ ዕጣ ፈንታ የኩርድሾች መሆኑ አይቀሬ ነው።
- · ዕድል አና ለማ ሰምና ወርቅ ናቸው። በተረገጡ ሲፈተሽ!
እኔ የለማ እና የአብይ መንፈስን እምወደው ከዛ በፍጹም ሁኔታ የራቀ ስለሆነ ነው። እንደ ድርጀት ኦህዴድ እጅግ የታደለ ነው። እንደ ግለሰብ ጥንካሬም ኦህዴድ እጅግ የታደለ ነው። እንደ መንፈስ ብአዴን የገዱን መንፈስ ማግኘቱ ጥሩ ነው። ግን የገዱ መንፈስ እንቅልፍ ላይ ነው። ለሽ ብሎ ተኝቷል። ጥሩ አማካሪም የለውም።
እኔ አብይ ሆይ! በሚለው አቤቱታዬ ላይ በስፋት አማራን በሚመለከት ያቀርብኳቸው ጉዳዮች ምን ያህሉን እንዳነበበው ራሱ የገዱ መንፈስ አላውቅም። ኦህዴድ ብልህ ስለሆነ በዬጊዜው የሚሰጠውን ኮሜንት ልቅም አድርጎ ሰብስቦ የሚያረካ እርምጃ በክልሉ እዬወሰደ ነው።
በዚህ 100 ቀን የአብይ ካቢኔ የባከነውን ያህል ኦህዴድ ባትሏል። ግድፈቶችን ለማስተካከል እና ባገኘው መልካም የብረት መዝጊያ አጋጣሚ ለመጠቀም። ኦህዴድ ወደፊት እራሱን ለማምጣት ያለመበት አብዩ ጉዳይም ትልሞቹ ብረት መዝጊያ ድጋፍ እንዲያጘኑ ነው። ይህንንም ጽፌበታለሁኝ፤ የፈለገ ጠንካራ በግልም በጋራም ቢሆነም ፌድራል ላይ ቁልፍ ባይኖረው አንዲት ስንዝር መራመድ እንደማይችል ስለሚያውቀው ተሟሟተ፤ ተሰካለት፤ አወቀበትም። አማራሮቹ እራሱ ከዓይነት ያውጣችሁ የሚያስብሉ ናቸው። በሁሉም ዘርፍ።
ኦህዴድ 40 ሺህ እስረኞችን አስፍትቷል። ኦህዲድ በሺህ የሚቆጠሩ መሪዎቹን ካዳሬዎችን ከፊሎችን ከሃላፊነት አባሯል፤ ከፈሎችን ከሃላፊነት ዝቅ አድርጓል፤ ከፊሎችን ደግሞ ከፍ ወደ አለ ደረጃ አዘጋጅቷል፤ አዳዲስ ትንታጎችን ተቀብሏል። ቄሮምን በሙሉ ፖለቲካዊ አቅሙ እዬተጠቀመበት ነው። የለማ መንፈስ ሚስጢሩም ይሄው ነው። የእኞቹ የአማራ ተጋድሎ ትንታጎች ደግሞ ወንጀለኞች ናቸው።
- · ዕድልና ገዱ ሰምና ሰም ሆነዋል፤ ይብላኝላቸው።
የአማራ ተጋድሎ አንበሶች ተገላይ ናቸው። ቃሉን እራሱ ብአዴን ደፍሮ አይናገራትም። እራሱን ፈራው። ቄሮ እኮ አሁን በፖለቲካው ሙሉ ተሳታፊ፤ አራጊና ፈጣሪ፤ አማካሪም ነው። አማራ ተጋድሎ ግን ሁሉን ለሥልጣን አበቃ አሁን ሚዲያው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሳይቀር በይፋ እንደ አገለለው ነው የሚገኘው። የተጋድሎ አንበሶቻችን በፍጹም ሁኔታ በለውጡ መንፈስ ውስጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አልተደረገም። አልተፈቀደም። ይህ ምን ሊያመጣ እንደሚችል ነገን ያዬ ...
ይህን ብአዴን ሙሉ ለሙሉ ባዶ ከሮጆውን እንዲረከብ የሚያደርገው የማዕት ሞገድ ነው። ይጠበቀው። ሰማያዊ ፓርቲ በሽታውን ተሸክሞ እመጣለሁ ቢልም ከእንግዲህ የአማራ ወጣት በጅ የሚል አለመሆኑን ከዚህ አንበሳ ወጣት ማድመጥ ችያለሁኝ።
ትንታጉ ኦህዴድ ሰሚናርም ለአዲሶቹ አማራር ሰጥቷል። ኦህዴድ በአዲስ አባባ ማሳተር ፕላን ለተፈናቀሉ ወገኖቹም መሰሉን የመልሶ ማቋቋም ተግባር ከውኗል። ከ700ሺህ በላይ ለተፈናቀሉ ወገኖቹ የሚችለውን ያህል ጥርት አድርጓል። ገንዘብ በማሰባሰብ እራሱን የቻለ ዝግጅት አድርጓል። በጠቅላላ ኦህዴድ ለቀጣዩ የሥራ ዘመን ምቹ የመንፈስ ይሁንታዊ ሃዲድ ዘርግቷል።
ኦህዴድ ባገኘው ምቹ ሁኔታ እኛ በምናውቀው እና በማናውቅም ጉዳይ ላይ በማዕከላዊ መንግሥትም እኩልና ሙሉ ተሳትፎ እዬደረገ እንደሆን የሚታዬውን እናያለን ግልጽ ሆነው፤ በማይታይት ጉዳዮች ላይም ደግሞ በፖለቲካ ዓለም ለቆዬነው የማይጠፉን ነገሮች አሉ።
ኦህዴድ እና ብአዴን ማወዳደር ቀርቶ ሥሙን ለመጥራት እንኳን ማንሳት አይቻለም። ሌላው ቀርቶ በሚዲያው እንኳን አማራ መሬት ላይ የተካሄዱ ሁለገብ የድጋፍ ሰልፎችን ከነመንፈሳቸው ለማቅረብ የኢትዮጵያ ቴሌቬዥን ባይደፍረም ብአዴን ግን የህዝብን ድምጽ ማሰተጋባት ሲጋባው በዝግ ነው ያለፈው።
ኦህዴድ ከኦቦ ሌንጮ ለታ ጋር ያደረገውን ውይይት ሲዘግብ ብሄራዊ ሚደያውም ያን ሲያስተጋባ ትናንት የተከበረውን የሐምሌ 5 በዓለ ተጋድሎ አልተላለፍም። ግለቱ አባ ዝምታን ያመጣል።
- · አባዝምታ እና መጪው ጦሮው።
አባ ዝምታ ደግሞ አይደለም የአማራ ብሄርተኝነትን ከዚህም ያለፈ ነገር ይዞ ይመጣል። የአዬያዝ፤ የአቀራረብ፤ የአማራር እንከኖች ናቸው ህዝብን የሚያስቆጡ … ሴቶችን መድረክ ላይ አይቻለሁኝ። ከኦህዴድ የጽ/ቤት ሃላፊ እና ከኦህዴድ ምክትል ፕሬዘዳንት ጋር ሳነጻጽረው 100/10 ነው።
ስለዚህ ወደፊት ሴት መሪዎችን ለማምጣት ትግራይም፤ ደቡብ ህዝቦችም፤ ኦህዴድ በጥምር ብቁ ሴቶችን ፌድራል ላይ እዬዬን ነው። ብአዴን ዳሽ ተሸላሚ ነው። ስለሆነም በሁሉም ዘርፍ በሞተ ተስፋ ላይ ነው ብአዴን ያለው።
ሌላው ወጣት አመራሮችን በማምጣት እረገድም ቢሆን ኦህዴድ በትጋት እዬሠራ ነው፤ ብአዴን ደግሞ ከነምርጉዙ ጋር እንደ የትግራይ ተፎካካሪም መሪም ድርጅት ነው ሆኖ ኮከብ በመቁጠር ላይ የሚገኘው። ከ66ቱ መንፈስ መውጣት አልተቻለውም ብአዴን። ያ ማራታዊ፤ ዝገታዊ፤ ብልዘታዊ ሁኔታ ደግሞ ራሱን በራሱ የሚቀበረው ይሆናል።
- · የዜሮ ግርሻ።
ዜሮ ሲባዘ በዜሮ ዜሮ ነው። ዜሮ ሲደምር ከዜሮም ዜሮ ነው፤ ዜሮም በዜሮ ሲካፍል ያው ዜሮ ነው። በዜሮ ላይ ቆሞ ተስፋን ማሰብ እጅግ ከባድ ነው። የገዱ መንፈስ ሰው የማብቀል እና የማብቃት አቅሙ ፈተና ውስጥ ነው። ስለምን? አማራ ተጋድሎን እንዳገለለው የ66ቱ የማርክሲስት ፖለቲካ እሱም የዛ ቢክተም ስለሆነ።
ከአማራ ውጪ አማራን ሊመራ ሊያሰተዳር ሊያዳምጠው ውስጡ ሊሆን የሚችል ምንም ነገር የለም። የራስን ጥረት የሚታካም ምንም ነገር የለም። እኔ ለገዱ መንፈስ የተለዬ አክብሮት አለኝ። ነገር ግን ለቀጣይነት ማርከሻ ካልሆነ እና የጥቃት መሰላል ማስፈጸሚያ ምርኩዝ ከሆነ ምን ያደርግልኛል … ይሉኝታ ለማህበራዊ ኑሮ አንጂ ለህልውና ቀጣይነት መፍትሄ ሊሆን ከቶውንም አይችልም። ቆራጥ ውሳኔ፤ ቆራጥ እርምጃ ያስለፍጋል። መቁረጥ ያልቻለች ነፍስ መኖርን አልጀመረችም። ብኤደን እና የ አብዩ መንፈስ እንደተፋቱ ነው እኔ የሚሰማኝ ... አደጋው ሰፊ ረቂቅም ነው።
ቀድሞ ነገር ለዚህ ሁሉ አቅም መሠረቱ እኮ „የኦሮሞ ደም ደሜ ነው“ ይህ ሆኖ ሳለ ተጋድሎው በራሱ በብአዴን የተጋፋ እና ዕውቅና የተነሳው ስለመሆኑ አብረን በመንፈስ ስላለን አሁን ግልጽ ነው። በፊትስ እንዳላችሁም ስለማንቆጥራችሁ ብዕራችንም ብራናችንም የሰረዛችሁ ነው የነበራችሁ። የወያኔ ሃርነት ትግራይ የአማራ አጥፊ ድርጅት አስፈጻሚ ማህብረ ሳጅን ስለነበራችሁ።
- ቁስልን ቢሸፍኑት መምገሉ አይቀሬ ነው።
ስለምን ይህን ዕውቃና የፈድራል መንግሥትስ፤ ብአዴንስ አህዴድስ አልስጠም ቢባል ቄሮ ሺ ሚሊዮን ጊዜ እዬተነሳ ሲባል የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማኒፌስቶን መንፈስ ስለሚያናጋው ነው፤ የውሽማ ሞት ሆኖ ተጠቅልሎ ተጀቦኖ የተቀመጠው።
የፈንዳ ዕለት ግን ያው ሞት እና እስራቱ ቀጣይ ይሆናል። ኢትዮጵያም እንደ ገና ትታመሳለች። የፈለገ ያህል ሰው ቢፈናቀል፤ የፈለገ ዓይነት ንቅናቄ ቢነሳ አማራ ካልተነሳ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅም፤ መንግሥታዊ ጭካኔዊ እርምጃም አይወሰደም።
አሁን አማራ ላይ ያለው አባ ዝምታ ቢነሳ ግን አገር ቀውጢ ይሆናል። ምድር ግልብጥ ትላለች፤ ውጤቱም የከፋ ይሆናል። ምንም አይድነበትም፤ አሁን የተጀመረው የተስፋ ጉዞም ይጨናጎላል። ምክንያቱም መግልህን ተሸክመህ ኑርም ተብሎ እሱ ባመጣው ለውጥ የሌላ አንጋች ሁን አያስኬድም። ትክክልም አይደለም። ፍትህ ሆይ! የት ነሽ ስለ መከረኛው አማራ?!
- · ፍጥነት በጥራት።
መፍትሄው አማራውን በትክክል የወከለ ድርጅት መፍጠር ነው። ብአዴን የመጨረሻ ዕድሉ ይህቺ ሰሞናት ብቻ ናት። አስተውሉ ይህቺ ሰሞናት ብቻ ናት። ይህቺ ዓመት አላልኩኝም። ይህቺ ሰሞናት ብቻ ናት።
የጠቅላይ ሚኒስቴር አብዩ ካቢኔ እንዳይታወክ መረጋጋቱ እንዲቀጥል ከተፈለገ ብአዴን ጥገናዊ ለውጡን ትቶ ሥር ነቀል ለውጥ ማምጣት አለበት። አሁን የሰሞኑ ስብሰባ ላይ አቶ አለምነህ መኮነን ምን ያደርጋሉ? ምናቸው ነው? እሳቸው የሁለት ድርጅት አባል ናቸው እሳቸውን መሰል አሰራዊ አስተሳብ ያላቸውን ሁሉ በፍጥነት ማስወገድ አለበት ብአዴን ነፍሱ እንድትቀጥል ከተፈለገ።
ይህም ብቻ አይደለም ተከታዮቻቸውን በሙሉ ማስወገድ አለበት። በስተቀር ግን የአማራ ወጣት ብቻ አይደልም ሙሉ ዕድሜ ላይ የምንገኘውም በልቦናች ውስጥ ያለውን ቋያ የሚገደበው ማንም ምንም ሃይል የለም።
አማራ ብቻ ሳይሆን ከአማራ ጋር ተፈርጆ 27 ዓመት ሙሉ በፖለቲካዊ አውቅና ስውር ማዕቀብ የተጣለበትም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማንያም የት አሉ? የት ናቸው? ስለዚህ ብአዴን ቀንም ሌትም ሠርቶ አይገፋውም፤ እዬሠራሁ ነው እንዳይለኝ እዬሠራ አይደለም። ተኝቻለሁ ቢለኝ ግን ይገባኛል፤ አሟሟቂ ነኝ ቢለኝ ይሰማማኛል፤ ቀለም ቀቢ ነኝ ቢለኝ አረዳዋለሁኝ... ምክንያቱም እያንዳንዱን ነገር ሥራዬ ብዬ ስለምከታታል .. 27 ዓመት ተጣቃሚነቱ ቀርቶ በሞት እና በውግዘት የነረ ማህበረስብ የተለዬ እንክብካቢ ሊደረገለት ሲጋባ፤ በድሎ፤ በምቾት አይንህና ጥርስህ እዬተባለ የተባጀው እንክብካቤ በእንክብካቤ ... ሰው ነን ይከፋናል ...
ብአዴን ከአቤቱ ሰማያዊ ጋር ቁጭ ብሎ የተወያዬበትን ጊዜ አንበሳው ኦህዴድ ስንት ታምር ፈጥሮበታል … ኦህዴድ ኦሮሞ ጠቀም ጉዞውን ነው እያጧጧፈው ያለው … ስለምን አውነተኞቹ ኦሮሞዎች ስለሚመሩት።
- · የፋታ ፖሊሰ ለእንቅልፍ መጫጫኛ ነው።
ጊዜ ስጡን አይሰራም። ጊዜ የለም ይሠራል። ደሴ ላይ እኮ አዳራሽ ጠፍቶ ሜዳ ላይ ነው የሚሰበሰቡት። የትናንት አዋሳ ከአዲስ አባባ በላይ ናት ልክ እንደ ኪጋሊ የማነን ጎፈሬ ሊያበጥር ነው ብአዴን …
ወጣቶቹ ያነሱት በፖሊሲ ደረጃ እንዲጠፋ የተፈረደበት ማሀብረሰብን እምራለሁ ያለ ድርጅት አሁንም አመራሩ ከዬት መጣ አትበሉን ነው። ይህ ማለጋጥ ነው። ግፍም ነው። ግፍም ፍሩ። አማራን አማራ ነው መምራት ያለበት። ይህን ያህል የሁሉም ነገር የጥቃት እንደ ጥንቸል መሞከሪያ የሆነው አንድ ቀንጣ ተቆርቋሪ የእኔ ባይ ስለሌለው ነው። አሁንም የደሙ ክፋይ አለሆኑ አንበርክከው ይሰልቁህ ነው?
ቢያንስ አማራ መሬትህ ነው ተብሎ በተሰጠው መሬት ላይ እዛው ያሉ ብሄረሰቦችም አገው እና ቅማንት የተገባቸውን ውክልና ጠብቆ እራሱን የቻለ ጥርት ያለ አቋም ሊኖረው ይገባል ብአዴን። ሁሉንም ዘርፍ ደሙን ደሙ መምራት አለበት፤፡ ዓርማው እራሱ፤ ባንዴራው፤ ገዳዩን ግንቦት 20 ያለውን አውሮፕላን ማረፊያ ሥያሜ ሁሉ መቀዬር አለበት፤
በዬመሥሪያ ቤቱ ቁልፍ ቦታ የሠጣቸውን ሁሉ በሚመለከት ፈጣን እርምጃ ካለወሰደ አይደለም ብአዴን ኦህዴድም አሁን ያገኘውን ሁለገብ የበላይነት እና የወሳኝነት መስመር ያጠዋል።
ከአማራ ውጪ ኦህዴድን ማን አምኖ ይደግፈዋል። የትናንቱ ህብረ ብሄር ፓርቲ የተቀላቀሉት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ እኮ ሰሞኑን ያሉትን አዳምጠናል። ትናንትም ዶር ነገዎ ዲማም የሰጡትን ቃለ ምልልስ አዳምጠናል … አደጋው ብዙ ነው።
- · ኦህዴድም ስለ አንድ ዓይኑ ይሰብበት፤ ብቻውን አይሩጥ!
ስለዚህ ኦህዴድ እራሱ አማራ መሬት ላይ ያለውን የዘበጠ፤ የዘገጠ የአይዲኦሎጆ መፋለስ፤ ማዕከል ላይ ያለውን መንግሥቱ የሚመራበትን አማራን የማጥቃት፤ የማስጠቃት ፖለሲ ሙሉ ለሙሉ ማስወገድ ካልተቻለ ኦህዴድ አንዱም የኦሮሞ ድርጅት የውስጥ ድጋፉን ሰጥቶ እንዲቀጥል የሚያስችለው አይሆንም። ምክንያቱም ምክሩና ዝክሩ ኦህዴድን ከባህር የወጣ አሳ መድረግ ነውና። ይህ የሴራው ፖለቲካ ዶግማው ነው።
ለኦህዴድ አንድ ዓይኑ የገዱ መንፈስ ብቻ ነው። የገዱ መንፈስ ከወደቀ አበቃ ነው። ለአላዛሯም ኢትዮጵያ ቢሆን ይሄው ነው መንገዱ። ኢትዮጵያዊነቱ በስተርጅና እንኳ ያለተጠነሰሰበትን የመከራ ደማና ተሸክመህ ደሙን ኢትዮጵያ ያደረገውን አማራ ማግለል ውለታ ቢስነት ነው።
በዛ ላይ ላንመለስበት የቆረጥን ሚሊዮኖች ነን። አማራ ነኝ ማለትን አናፍርበትም። አማራነት ባያንጠራራም የምንፍርበት ማንነት አይደለም። ምን አሳጥቶን አማራነተችን? ምንስ ነስስቶን ኣመራነታችን? አውሮፓን ራሱ የውስጥ ራድ አስይዞ የኖረ ማንነት ነው አማራነት። የሥልጣኔም ምንጩ ነው። ስለምን? ከኢትዮጵያዊነት ጋር ውህድ ስለሆነ።
ፍጥነት በንጽህና እና በድንግልና!
ሩጫ ያስፈልጋል የተቀናጀ ሩጫ …. የውጪው አጋዢ ነው እንጂ ወሳኙ ሞተር ያለው አገር ውስጥ ነው። አብሶ አማራ ላይ የሚሠሩ ተጨባጭ ሥራዎች ወሳኝ ናቸው የአብይን መንፈስ ለማስቀጠል … ባለፈውም ጽፌ ነበረ ሊቀለበስ ይችላል ብዬ።
አሁንም እደግመዋለሁ የለውጡን ሞተር አማጪው የአማራ መንፈስ አያያዝ ምንም ነው። ምንም። ከቁጥርም አልገባም። ቤተኛም አይደለም። እራሱ የኤርትራ ጉዞ እና ዕድማታውም እንዲሁ መላጣ ነበር። ሁሉን እንታዘባልን። ለሚበልጠው ቅድሚያ እንስጥ ብለን እንጂ ...
ስለዚህ ከጊዜ ቀድሞ መሮጥ ያሰፈልጋል። እኔ ለአማራ መሬት የመሪነት የፖለቲካ ተሳትፎ አማራ ስለመሆን ቅድመ ሁኔታ አያስፈልገውም። ፌድራል ላይም የት አለ አማራ? ማነው አማራ? የለም እኮ! በዚህ ዝንቅ ጉዞ ቀጣዩን ምርጫ ማሰብ ቀርቶ ምርጫ የሚለውን ቃል ስለመግለጽ ይከብዳል።
- · ክወና።
ወጣቶቹ በብአዴን ላይ ዕምነት እንዲኖራቸው ለማድረግ የአማራ ወጣት መሪዎች ከታች እስከላይ ካለተዋቀረ ውክል ሆኖ ፌድራል የሚሄደው አማራ ያልሆነ ስለሚሆን አማራ አብሰንት ነው። 27 ዓመት እንዲህ ተቀልዷል። ከእንግዲህ ግን የሚሆን አይደለም። ብአዴንም ይዋጣል በቁጣ እና በማዕበል። ይህ ደግሞ አይቀሬ ነው። „ልብ ያለው ሸብ“
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ