ልጥፎች

ከጁን 4, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ፍቅር ቁጥር አይደለም።

ምስል
           የፍቅር ተፈጥሯዊ መርህ                 ቁጥር አይደለም።                                          ከሥርጉተ ሥላሴ 03.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)                        „የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሄርን መፍራት ነው። ሰነፎች ግን ጥበብን ተግሳጽን ይንቃሉ።“                                         (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፯) ፍቅር ቁጥር አይደለም፤ አንድ ሁለት ሦስት እዬተባለ በጥቁር ሰሌዳ ላይ በጠመኔ የሚጻፍ። ፍቅር መስፈሪያ የለውም። ፍቅር ዳርቻ ዲካ የለውም። ፍቅር ስፋት እና ቁመት የለውም። ፍቅር ቅርጽም ፎርምም ሊወጣለት አይችልም። ፍቅር አልፋ እና ኦሜጋ ነው። ፍቅር ነፍስ ነው። ፍቅር ደም ነው አብሮ የተፈጠረ። አብሮ የሚኖር። ልባም ከሆንክ ለትውልድ የምታወርሰው ቋሚ ቅርስ ነው። ትውልድንም የምታስቀጥልጥ...