#የአማራ ማህፀን የ30 ዓመት ህማማት አቶ ደመቀ መኮነን።23/11/2023 ዬተፃፈ ነበር።
23/11/2023 ዬተፃፈ ነበር። #የአማራ ማህፀን የ30 ዓመት ህማማት አቶ ደመቀ መኮነን። ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ። "ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯) የአማራ እናት ማህፀን አንድነት ነኝ ሲል ለዛ ማገዶ እሷ ናት። የዜጋ ነኝ ሲባልም እሷ የቄራ ናት። የብሄራዊ ነኝ ሲባልም የልጅ ልኳንዳ ቤት አቅራቢ እሷ ናት። አማራ ነኝ ብሎ ሲመጣም እሷ ናት። ለእሷ መገደል፣ መፈናቀል፣ ለልጇ መታገድ ግን አንድም ከጎኗ የሚቆም ድርጅት የለም። አንድም። አንድም የለም። እንደ ግለሰብ እምንቆም ብንኖርም የቆምንለት ነፍስ እኛኑ ተዋጊ ሆኖ ያርፋልዕድሉን አግኝቶ ለወግ ሲበቃ። እኔ እምለው አንድ ነገር አለኝ። ይሳካለት እና ይካደኝ። አሁንም እምለው ይህንኑ ነው። እኔው ልማገድ የቁሩት ከሞት ይትረፋ እና ይካዱኝ። መካዱ ብቻ ሳይሆን ይታገሉኝ። ችግር የለም። የእነሱን ትቼ ለባለተረኞች ባለ ካቴና አይታክቴ ደግሞ እንደ አሙሏ ትማገዳለች። ስለ አቶ እስክንድር እና ሰርኬ የዛሬ 15 ዓመትም ከጋዜጠኛ ብያንካ ጋር እታጋል ነበር ዛሬ ብቻዬን እታገላለሁኝ። ይኽው ነው ጥሪዬ። አያውቀኝ፣ አላውቀው። ሆላንድ መጥቶ ነበር። አልሄድኩም። ዙሪክ ቢመጣም አልሄድም። የሆነ ሆኖ እነኝህ ተሰውረው የቀሩ የአማራ ልጆች ናቸው። የማናውቃቸው ብዙ ናቸው። በወለጋ ብዙ በጣም ብዙ። በነገሌ ቦረናን አሁን ስለተቆጣጠሩት ብዙ ይኖራሉ። ህወኃት በያዛቸው በስሜን ወሎም እንዲሁ። የአማራ እናት ማህፀን ቄራ ነው። ይህን ለማስቆም የረባ አስተሳሰብ ያለው የፖለቲካ አቅም የለም። ትነት ብቻ። በቃ ትነት ብቻ። መጀመር እንጅ ፍፃሜ አልቦሽ ዳንኪራ። ...