23/1/2021 ዬተፃፈ
#እናንተስ አዲስ አበቤ አይደላችሁንም።
#ግን የማን ናችሁ?
#ማን ነው ባለቤታችሁ?
ግን ባልደራስ ስለአዲስአበቤ አይደለምን?
ዕለተ ሰንበት ርትህወሰባዕዊነት
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራን ቀን እጠብቃለሁ"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
እነኝህ የእኛ ናቸው። ስለ አዲስ አበባ ዝም አንልም ያሉ እንደ ሻማ የቀለጡ ባለቤት አልባወች ናቸው። አቋጥሯቸው። የተሰውም አሉ። 5 በጠራራ ፀሐይ። 
 May be an image of 10 people
 
ፎቷቸው ሥማቸው የለንም። ፎቷቸው ሥማቸው ያለንንም ሰማዕታትም አሉን። ካቴና ላይ ላሉት ቢያንስ ባሊህ ይባሉ። ቢያንስ።
የአቶ እስክንድር ነጋ ከእስር ይፈታ ቅድሚያ ይሰጠው እል የነበረው ለዚህ ነበር። ያን ድርጅቱ አልፈለገውም ነበር።
ሽሚያው ሌላ ነበር። ዕውነት እማትደፈረው ገመናው ስለታወ ነው። የዶር ገመችስ ደስታ ተልዕኮ ድል በድርብ አሳክቷል ያን የአቶ ዮናስ የኋንስን ሰርግ ክርስትያን ዩቱብ ገብቶ የህሊና ነቀላ እና ተከላው እንደምን እንደተከወነ ማዬት ነው። ሰው ማተቡንክዶ ለሆዱ ካደረ ከምኑ ምኑ ይለያል።
ብላሽነት በጠራራ ጠኃይ በሁሉም ዘርፍ የታዬበት ሁሉም ገመናውን ተሸከሞ ደብቁኝ ሊል ሲገባ ገመናው ሳይወሳ የዕለቱ አንበሳ ነኝ ብሎ ሲያገሳ አለማፈሩ ይገርመኛል። በሌላው ይቻላል። በእኔ ግን አይቻልም። ፈፅሞ አይቻልም።
ቅርሻን የሚያስተናግድ ሰብዕና የለኝም። ኑሮኝም አያውቅም። ከትናንት ተነስቼ ዛሬን እመዝናለሁ። ትናንትን በቅንነት ሳይ የዛሬ የተግባር ብልጫ እሻለሁ። ዛሬን እዬገደሉ ትናንት፣ ትናንትን ገድሎ ዛሬ የለም።
አቶ እስክንድር ነጋ ይሁን፣ አቶ ስንታዬሁ ቸኮል፣ ወሮ ቀለብ ስዩም ትሁን ወት አስካለ ደምሌ ዕዳ የለባቸውም። ዕዳ ሳይኖርባቸው የባለ ዕዳ ዕዳ ተሸካሚ መሆናቸው ሳያንስ እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬ የሰው ሰብዕና፣ ዝና፣ ክብር፣ ልዕልና፣ ዝና፣ መወድስ አድማቂ፣ ዳሪ፣ ኳሊ ናቸው።
የሚገርመኝ ይህ ብቻ ነው። የሚያሳዝነኝ ይህ ብቻ ነው። እነሱስ ቢንገላቱም። ቢያንስ ጠያቂ ዋስ ጠበቃ አላቸው። እነኝህኞችስ፣ የተረሱትስ ማን አለቸው? ጥያቄዬ ይህ ነው። አንድም ሚዲያ ፎቷቸውን ለጥፎት አይቼ አላውቅም። አንድም ተቋም ስለ እነሱ ሲቆረቆር ሰምቼ አላውቅም?
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/10/2021
እናንተም የእኛ ናችሁ። አይዟችሁ ወገኖቼ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።