ኃራም ገዳ እስከ ተጠማቂዎቹ። 23/10/2020 ዬተፃፈ ነው።

 

23/10/2020 ዬተፃፈ ነው። ምስጋናዬ በአክብሮት ለአጤ ፌቡ ይድረስልኝ። ለአዲስ ወዳጆቼም ዬተደማሪ ከመደመር ጎራ ላፈነገጡትም ይሆናል። ከልባችሁ ሁናችሁ መርምሩን። ለዚህ ነው ተቀድሞ ትግል ስለተደረገበት በጥሞና እያዳመጥኩ ያለሁት።
መቃብር ፈንቅሎ ከወጣ የሞጋሳ ተጠማቂ ድምፅ።
"እኛ ለሥልጣን አይደለም የታገልነው" ያሉት የካባ ኢንተርተይመንት ድርጅት በመላ አማራ ቀዬ የከፈቱት አካል የሆኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ቢሮ መጠበቅ ሰለቻቸው መሰል የፃፋት ሙሉ ቀርቧል። አማራ ሚዲያ አገልግሎት እንደዘገበው።
የአቶ ደመቀ መኮነን ታጠቅ፣ የሳጅን ተመስገን አንታገስም፣ የወሮ ሙፍርያት ስክነት፣ የአቶ ገዱ አማራ ተጎዳ የእንቅልፍ እራሮት የተኃድሶ ጊዜ ይሰጠን ደወል ነው ለእኔ።
አገልግሎቱን ከጨረሰ ባትሪ ብርኃን አይጠበቅም። አዲስ አበባ ላይ ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ሲሰፍር የት ነበሩ?
ከጉለሌወደ ባህርዳር አማራ ሲሸኝስ፣ የታገቱ ተማሪዎች እና ሜዳ የቀሩትስ፣ ቢሮው በሙሉ በወጥነት ሲያዝ፣ የግሎባል እና የአህጉር ክፍት ቦታዎች የአብይዝም መጨፈሪያ ሲሆን፣ ሙሉ ካቤኔ ፀጥታው፣ ባንኩ ኢንሹራንሱ እንዳሻ ሲኮን ከት ኡራኖስ ላይ ተሰብስበው ሰፈሩን?
"ዛሬ በጠዋቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በፌስቡክ ገጹ ይህንን ጽፏል!"
"ዛሬም በጉራ ፈርዳ...
"የአማራ ህዝብ ለፍትህ፣ለነፃነት እና ለአብሮነት ሲታገል ቢኖርም እስካሁን በኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም፣ፍትህና የህግ የበላይነት ሰፍኖ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በየትኛውም የአገራችን ክፍል በሰላም ፣ በነፃነት እና በደስታ መኖር የሚቻልባት አገር ባለቤት መሆን አልተቻለም።ይልቁንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ግፍና መከራው አየተጠናከረ በአሰቃቂ ሁኔታ መጨፍጨፋና በገፍ መፈናቀሉ ተስፋፍቶ ቀጥሏል።
ይህንን ሁኔታ ለመረዳት ብዙም ሩቅ ሳንሄድ ይህንን አንድ አመት ብቻ ወስዶ አዝማሚያውን መገምገሙ ብቻ በቂ ነው።ከጥቅምት እስከ ጥቅምት ያለው አንድ አመት ብቻ በግልፅ የሚነግረን ግፍና መከራው ተጠክሮ መቀጠሉን ነው። ማለቂያ የሌለው የጅምላ ጭፍጨፋ፣በገፍ መፈናቀል፣የዘመናት የልፋት ውጤት የሆነ ንብረት ውድመት የየሳምንቱ መርዶ መስማት የተለመደ እየሆነ መጥቷል።
ስለሆነም ነገሩን ላለማባባስ ሲባል በዝምታ ማለፋ የሚጎዳ መሆኑን በተግባር እያየነው በመሆኑ ያገባናል ባዮች በሙሉ ልንነጋገርበት ይገባል።ይህ በአማራ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመ ያለው በማንም ህዝብ ሳይሆን በጥቂት ቡድኖችና ግለሰቦች ሴራ መሆኑን በመገንዘብ ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ በአጋርነት የሚያሰልፍ የትግል አቅጣጫ ነድፎና ስትራቴጅያዊ ግብ ወስኖ በጋራ መንቀሳቀስ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም። በክስተት ላይ ያነጣጠረ ጩኸት አልቃሻ ከማድረግ የዘለለ ጥቅም የለውምና።"
አቤቱ ህሊና ለለው ሰው ብለህ መፍጠርህ ስለምን መሆኑን ጥበቡን ግለፁልን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ኃራም ገዳ እስከ ተጠማቂዎቹ።





  •  
    Shared with Public
    23/10/2021 ዬተፃፈ ነው። ፕ. ዶር መራራ ጉዲናም የጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቦታ ምኞተኛ ናቸው። ቢሯቸው ግን ዕብድ የዘራው አዝመራ …… መጥኔ ለኢትዮጵያ ………
    ማደራጀት በብዙ መልኩ ይከወናል። መስከ ብዙ ህብራዊ የሆነ የሙያ ዓይነት ነው።…
    See more

    አስተያየቶች

    ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

    ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

    እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

    አብይ ኬኛ መቅድም።