23/1/2021 ዬተፃፈ ነበር። አቤቶ አብን የፎቶ ሾፓችሁ ቋቅ ብሎኛል

 

23/1/2021 ዬተፃፈ ነበር።
አቤቶ አብን የፎቶ ሾፓችሁ ቋቅ ብሎኛል፣ ያው የቤተ መንግስቱ የቡና ቤተኝነታችሁ ለመኮንኖች መፈታት አውሉት። ቢያንስ።
ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህወሰባዕዊነት
በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራ
በቢሆነኝ የተብራራ ብራ
በሰብለ ህይወት አዝመራ
ለራህብ የሚራራ።
"ዝም ብዬ የመከራ ቀን እጠብቃለሁ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯)
1) አርበኛ መሳንፍትጀግንነታቸውን አውቃለሁ። ግን ተንቤን ሄደን ሂሳብ እናወራርዳለን ሲሉ እረፋ ብዬ ተግሳፅ ፃፍኩኝ። ወቅንን ጠብቁ፣ ዳሽንን ጠብቁ፣ ደባርቅን ጠብቁ፣ ደባርቅን ጠብቁ አልኩ።
የሆነውን አያችሁ ወቅን ጭና አጅሬ ድረስ ሄደው ያን የመሰለ ጭካኔ አስታቀፋን። ግን ትርፍ ንግግሩን አስቆምኩት። በእኔ ቤት ቀልድ የለም። አልወድም እኔ መንጠራራት። የፈለገ ቢመላ ቢተርፍ ሰው በልኩ መኖር አለበት። ከእኔ ቤት የሚደፋ ነገር የለም።
ግማሽ አፍል ቢበላሽ። የተበላሸውን የአፍል ክፍል ቁርጥ አድርጌ ጥዬ ቀሪውን እጠቀምበታለሁ። እራሱ ስገዛ ባዮ ነው እምገዛው ውድ ነው በቁጥር ነው እምገዛው። ውኃ ስጠቀም። እዬከፈትኩ እዬዘጋሁ ነው።
ካንፕ እያለሁ። ክፍሉን ሁሉ እዬዞርኩ አላግባብ የበሩ መብራቶችን አጠፋለሁ፣ አላግባብ የሚፈሱ ውኃወችን እዘጋለሁ። ኃላፊነት በዬትም ሁኔታ ነው ሊኖር የሚገባው።
2) አቶ ጋሻው መርሻ ደቡብ ጎንደር እንደዛ ተዝረክርኮ ሰሜን ጎንደር አሰኜው እና ደባርቅ ተከሰተ ተባለ። ፃፍኩኝ። የምታለዘው ነገር ካልኖረ አልሄድካትም አልኩ። የሆነውን አያችሁ የጀምላ መቃብር።
አቅሙ ካለው ካለሙያው ገብቶ ፎቶ ከሚደረድር፣ ከሚያስደረድር የተደራጀበትም ተልዕኮ ለኮረጆ ማድረጉን ስላስተዋልን እስኪ ባለሙያወችን መኮንኖችን ያስፈታ። "አንድ አማራ ለሁሉም አማራ" ብሎን የለም።
3) የሠርግ ቅልቅሉ፣ የሠርግ ግጥግጡ ከባልደራስ ጋር ከቂሊንጦ እና ከቃሊቲ መልስ ነው ወይ? በቃ የቤተ መንግሥት ቅልጥም፣ ፍርንቢያ የሳይንስና ቴክኖሎጂ የሚያምሩ የግቢ አበባወችን ማሳመሪያ፣ ማስዋቢያ መኳኳያ ብቻ ሆነን?
4) አቤቶ አብን የሰማዩ ጌታ የሚያውቀውን የዛን የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ሰማዕትነት ተቀብለው ያገዙን የተጉ የውጭ አገር ታላላቅ መሪወችን ሳይቀር ያዘከረ ቃል ኪዳን ጠባቂው ለምስራቅ ጎጃም፣ ለባህርዳር ህዝብ ምን የምስጋና ቀን አሰናድቷል? እኔ ይህን ማወቅ እፈልጋለሁኝ።
ዕውነቱ አብን ለዳግም ላልታወቀ የአማራ የምፃት የስቃይ ዘመን አብን የጉሮሮ አጥንት ነው የሆነው። ይህን ማቆላመጥ፣ ይህን ማሽሞንሞን አያስፈልግም። የተደራጀው። ለአማራ ህዝብ ነበር።
ፍቅሩን ደፍቶ ግርድናን የለመነ ድርጅት አሁን ምን አድርጉልኝ ብሎ በሞት መንደር እንደተገኜ ይገርመኛል። ለኦነግ የነበረው ልልስልስ ልብ "ለትህነግ" አልነበረው።
እንዲያውም ኦህዴድን ተክቶ ሠርቷል። ያለልኩ የተሰፋ እጀ ጠባብ ነበር። የአማራን ጨዋ ህዝብ ዲስፕሊን የመሸከም አቅም እንደ ድርጅት የለውም። የአሁኑ ጉዞ የከፋ ችግር ከመፍጠር ውጪፋይዳ የለውም።
የአማራ ህዝም ዘኔንወማስሬን ይከተል። መድህኑ ያ ብቻ ነው። ኮነሬል ደመቀ ዘውዴም በቀለማቸው ከማንም ጋር ሳይለካለኩ በጭምትነት በማስተዋል ሁሉንም በማቻቻል፣ በበቃ ዲስፕሊን አያያዛቸው መልካም ነው።
በጀርባ ካላስወጓቸው። ኦነጋዊውን ኦህዴድ አላምነውም። አብን እንደ ድርጅት አላምነውም። አዲስ አበባን ለቲም ዶር ገመችስ ደስታ ነው ያስረከበው።
አዲስ አበባ ላይ የአብን ዓርማ አልተወዳደረም። የሞት ሞት። የክህደት ክህደት። ቀና ብለው ሲሄዱ አለማፈራቸው ይገርመኛል። የዬኔታ ፕሮፌሰር ኃብታሙ ተገኜ ታሪካዊ፣ ሳይንሳዊ መፅሐፍን ተፃሮ የቆመ ድርጅት ምን እንበለው?
ለመሆኑ ጭንቅላታችሁ ኦሮምያ ከአዲስ አበባ ልዩ ጥቅም ያስፈልጋታል ባይ እኮ ነው? ይህ ደግሞ አሊ አይባል? ስንብት።
#ማን እንበለው?
አማራ ካለ ርዕሰ መዲና? ለመሆኑ ስለምን ስለማንስ ተደራጄ።ጃችሁ? ቂጥ ገሊቦ ራስ ተከናኒቦ የሆነ ነገር? ፎቷችሁ ቋቅ ብሎኛል። እባካችሁ ተውን። እባካችሁን? ትንሽ ደበቅ? ያ ነው ያባት። በሰብዕናችሁ በግል የምናከብራችሁ እንኳን አብራችሁ ጭልጥ ማለታችሁ ያሳዝናል።
አብን አቅሙ ካለው ካለሙያው ገብቶ ከሚዳክር ባለሙያወችን ያስፈታ እና ጦሩን ይምሩት። አለቃቸውን በቡና ተርቲማቸው ላይ ያናግሩ። ሙያ ይህ ነው።
ያን የጋለ የበቃኝ ተጋድሎ አብርደው የተቃጠለ አንፖል ተመራጭ ያስደረጉ እራሳቸው ናቸው። እራሳቸውን አብርደው አራጃቸውን ያስገነኑ። ፍሬነገሩን እጬጌው ዘመን ጊዜ ሲሰጠው ይዘረግፈዋል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
23/10/2021
እንቅጭ እንቅጩን እንናገራለን!
የአማራ ህዝብ ባስከበረ ሊካድ አይገባም።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።