ልጥፎች

ከኤፕሪል 21, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የአቶ ዮናስ ደስታ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ስለመነፈግ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  የጠ/ሚር አብይ አህመድ            ሦስተኛው … ው መዶሻ በአቶ ዮናስ ደስታ።   „ሳቅን እብድ ነህ፤ ደስታንም፤ --- ምን ታደርጋለህ? አልኩት።“ መጽሐፈ መክብብ ፪ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ። Seregute©Selassie 21.04.2019 ከእመ ብዙኃን ሲዊዚሻ። ·        ክ ፍል አንድ። እንዴት ናችሁ ውዶቹ ክብረቶቼ። ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ሦሰተኛውን መዶሻ ደግሞ እናያለን። ሦስተኛው መዶሻ በአቶ ዮናስ ደስታ ላይ የነተሰነዘረ ነው። የቀድሞው የቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፤ እኔ ልክ እንደ ሁለት አገሮች ጦርነት የመከፈት ስሜት ነበር የተሰማኝ ዜናውን ሳነብ። መጀመሪያ ዜናውን ያገኘሁት ሪፐርተር ላይ ነበር። እና እጅግ ደነገጥኩኝ። የሚገርማችሁ ለአንድ ወዳጄ ዶር አብይ አህመድ ለጠ/ሚኒሰተር እጩ ተወዳዳሪ በነበሩበት ጊዜ በቅርበት አብሬው እሰራው ከነበረው ወድንዴሜ ጋር መልእክት ስንጻጻፍ ዶር አብይ አህመድ ጠ/ሚር ከሆኑ ወደፊት ያመጧቸዋል ብዬ ካሰብኳቸው ወገኖች ፈላስማ ዶር ምህረት ደበበ፤ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ፤ አቶ ዮናስ ደስታ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጽፌለት ነበር። ምክንያቱም ያን ጊዜ ኢትዮጵያዊ ራዕያቸው ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ ሪኮመንድ በማድረግ፤ እውቅና በመስጠት ምስክር በመሆን የጎለበተ አቅም አያ ብቻ ስለነበር እነዚህ ወጣት ሊሂቃን የቲማቸው አካል የመንፈሳቸው ቤተኛ ያድርጓቸዋል የሚል እሳቤም ዝንባሌም ነበረኝ። የላኩለትም ኢሜል አለ ከእጄ ላይ እሱም የጹሑፌ ታዳሜ ስለሆነ አይረሳውም። ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋዋላ ግን ያዬሁት የጎላ እርምጃ አልነበረም። ይባስ ብሎ አሁን በቅጽበታዊ ውሳኔ ያን የመሰለ ልምድና ተመክ