ልጥፎች

ከኤፕሪል 5, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ምንሽን ነው እማ፧

ምስል

ፍላጎትን ያለማወቅ ዕዳ።

ምስል
  ፍላጎትን ያለማወቅ ዕዳ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።"   ወይ መዳህኒዓለም አባቴ ሰው በስንቱ ያዝናል? የትምህርት ተቋማት መደበኛ ተግባራቸው ስለምን ተቋረጠ የአባት? የጤና አገልግሎት ተስተጓጓለ የተገባጥያቄ፦ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ የጥቃት ዒላማ ማስፈፀሚያ የሆኑ የድሮን ጭፍጨፋ ስለምን ቆመ? ሚስጢሩ ምንድን ነው? የጤና አይመስለኝም? ምነው ድሮን የሚያመርቱ ተቋማት ባሉበት በአምላኬ ሰይፍ በያሉበት ንድድ ኩምትር ብለው አመድ በሆኑልኝ። እኔ ስለምን የሰው ልጅን የመኖር ዋስትና የሚያሳጡ መርዛማ መዳህኒቶች ለምን ይመረታሉ?   ስለምን ዓለማችን ከፍ ያለ በጀቷን ለጦር መሳሪያ ማዘመኛ ታውላለች? ከዛ ይልቅ ተፈጥሯዊነት ይሰፍን ዘንድ ስለምን በጀት መድባ ሥርዓተ ትምህርት ነድፋ አታስተምር ወደ ዘጠኝ ዓመት የሞገትኩበት ጉዳይ ነው። ለነፃነት የሚደረጉ፤ ከጭቆና ለመላቀቅ የሚከወኑ ህዝባዊ ንቅናቄወች የተገቡ ናቸው ግን መስዋዕትነትን በሚቀንስ ሁኔታ ሊሆን ይገባል። ነገር ግን ብረት ብቻውን ተጉዞ የሚያደርሰው ጥፋት ስለምን ተግ አለ ብሎ ሙግት ግን ከሰብ ህሊና ፈጽሞ ሊወጣ የማይገባው ነውር ነው።   የድሮን ጭፍጨፋ በኢትዮጵያ ስለመቆሙ ፖለቲካዊ ጉዳይ፤ ኢኮኖሚያዊ ትራጀዲ ለእኔ አጀንዳዬ ሆኖ አያብሰለስለኝም። የድሮን ጭፍጨፋ እንዲቆም ተግቼ ሲቆም ተመስገን ማለት ሲገባኝ ለምን ብዬ የምርምር ፕሮጀክት ከፍቼ የምጎረጉርባት አንዳችም ጉዳይ የለኝም። ተመስገን ነው የምለው። አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ ነው የምለው። የፈጣሪን ጥበብ አድንቅበታለሁ። ክብሩን ለአማኑኤል ለአላህ እሰጣለሁ። ሁለቱም አንጋፋ ሃይማኖቶን ፆም ላይ ናቸው። ድዋቸው፤ ሱባኤያቸውን ፈካጣሪ አድምጦ ሊሆን ይችላል።    የሆነ ሆኖ ፍላጎትን ማወቅ በእጅጉ ያስፈልጋል። ትግሉ፤ ድካሙ ዕንቅል