ፍላጎትን ያለማወቅ ዕዳ።
ፍላጎትን ያለማወቅ ዕዳ።
ወይ መዳህኒዓለም አባቴ ሰው በስንቱ ያዝናል? የትምህርት ተቋማት መደበኛ ተግባራቸው ስለምን ተቋረጠ የአባት? የጤና አገልግሎት ተስተጓጓለ የተገባጥያቄ፦ የጠቅላይ ሚኒስተር አብይ የጥቃት ዒላማ ማስፈፀሚያ የሆኑ የድሮን ጭፍጨፋ ስለምን ቆመ? ሚስጢሩ ምንድን ነው? የጤና አይመስለኝም? ምነው ድሮን የሚያመርቱ ተቋማት ባሉበት በአምላኬ ሰይፍ በያሉበት ንድድ ኩምትር ብለው አመድ በሆኑልኝ። እኔ ስለምን የሰው ልጅን የመኖር ዋስትና የሚያሳጡ መርዛማ መዳህኒቶች ለምን ይመረታሉ?
ስለምን ዓለማችን ከፍ ያለ በጀቷን ለጦር መሳሪያ ማዘመኛ ታውላለች? ከዛ ይልቅ ተፈጥሯዊነት ይሰፍን ዘንድ ስለምን በጀት መድባ ሥርዓተ ትምህርት ነድፋ አታስተምር ወደ ዘጠኝ ዓመት የሞገትኩበት ጉዳይ ነው። ለነፃነት የሚደረጉ፤ ከጭቆና ለመላቀቅ የሚከወኑ ህዝባዊ ንቅናቄወች የተገቡ ናቸው ግን መስዋዕትነትን በሚቀንስ ሁኔታ ሊሆን ይገባል። ነገር ግን ብረት ብቻውን ተጉዞ የሚያደርሰው ጥፋት ስለምን ተግ አለ ብሎ ሙግት ግን ከሰብ ህሊና ፈጽሞ ሊወጣ የማይገባው ነውር ነው።
የድሮን ጭፍጨፋ በኢትዮጵያ ስለመቆሙ ፖለቲካዊ ጉዳይ፤ ኢኮኖሚያዊ ትራጀዲ ለእኔ አጀንዳዬ ሆኖ አያብሰለስለኝም። የድሮን ጭፍጨፋ እንዲቆም ተግቼ ሲቆም ተመስገን ማለት ሲገባኝ ለምን ብዬ የምርምር ፕሮጀክት ከፍቼ የምጎረጉርባት አንዳችም ጉዳይ የለኝም። ተመስገን ነው የምለው። አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ ነው የምለው። የፈጣሪን ጥበብ አድንቅበታለሁ። ክብሩን ለአማኑኤል ለአላህ እሰጣለሁ። ሁለቱም አንጋፋ ሃይማኖቶን ፆም ላይ ናቸው። ድዋቸው፤ ሱባኤያቸውን ፈካጣሪ አድምጦ ሊሆን ይችላል።
የሆነ ሆኖ ፍላጎትን ማወቅ በእጅጉ ያስፈልጋል። ትግሉ፤ ድካሙ ዕንቅልፍ አጥቶ መባተሉ ለሰው፤ ስለሰው የመኖር ዋስትና ከሆነ። ብዙ ጊዜ ዝም እምለውም ገና በጋሜዬ የጀመርኩት የፖለቲካ መደበኛ ሥራዬ እና የዘመኑ ሁኔታ ስለማይገባኝም ነው። እርግጥ ነው የድሮን ጭፍጨፋ ሲኖር ሚዲያው አልባብበአልባብ ይሆናል። ሐዘን ለዛውም ድንገተኛ ደራሽ መርዶ መዋለ ሐሴት ከሆነ ስለምን እንባትላለን? የሚዘጋው በር፤ የሚፈታው ሞፈር እናቀንበር እኮ የአካላችን ነው። ቅኔው ጎጃም አካባቢ ያ ታዳጊ ወጣት የመላ ቤተሰቡ ቤት ዝግትግት ሲል ሲባትል ወንድሙን ሲጠራ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አላያችሁትንም? እኔ እኮ ታምሜ ነበር። ጦርነቱ ከጀመረ ጀምሮ ጤና በእጅጉ ነው ያጣሁት። በእኔ ዕድሜ በባሩድ ወተት፤ ዛሬም?????
እኔ ለረጅም ጊዜ ፕሮፋይሌ ድሮናዊ ድብደባ ይቁም የሚል ነበር። ለአውሮፓውያን አዲስ ዓመት ነው ያነሳሁት። የታዳሚወቼን ሰላም እንዳላውክ ተሳቅቄ። በዛ ላይ አዲስ ዓመትንም ተስፋ አጭቸበት። እኔ የምተገው ሰሚ ባገኝ ድሮን የሚባል ቴክኖሎጂ በምድራችን እንዲጠፋ ነው። የሰይጣን ሥራ ስለሆነ። አዋን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ያለማል ያሉት መንገድ እኔን ለመሰሉ ዜጎች የማይመቸን መሆኑን ተገንዝበው የህዝብ መቀነስ ፕሮጀክታቸውን እና ጭካኔያቸውን ቢያስታግሱት ጤናችን ይመለሳል። ቢያንስ? ሐሴቱ ቀርቶ ደስታ እንኳን ባናገኝ።
ከማለፋችን በፊት መሠረት ልናስይዛቸው የሚገባ ስንት የአደራ ጥሪ እያለብን ዛሬም በዕንባ እና ካቴና፤ በጦርነት እና ሰቆቃው ዕለታዊ ህይወታችን መጠመዱ ያሳዝነኛል። በእጅጉ።
ክብሮቼ እንዴት ናችሁ??? አቅም ስናዋጣ ፍላጎታችን እያወቅን ቢሆን ጥሩ ነው። የሰው ልጅ ዳንቴል አይደለም። የጀንበር ውጤትም አይደለም። አንዲት ቀን ማሃያ ቆርጠን ያላስተዳደርነውን ሰብዕና ጉዳይ ሊያሳስበን ይገባል። የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባም ትንሽ ይሰማን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ሥርጉትሻ 2024/04/05
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ