የአቅም ጥገትን መንገዱን ማንበብ ይቻላል!
የሚቀድመውን የመለዬት ጥበብ ለሁሉም መርሁ ቢሆን ምን አለበት? „የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ እንደሆናችሁ የእግዚአብሄርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁንም?“ ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 15.11.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ የአቅም ጥገትን መንገዱን እንደ መጸሐፍ ማንበብ ይቻላል። · እ ፍታ አላዛሯ ኢትዮጵያ የ27 ዓመታት ግዞታዊ ኑሮዬ በቃኝ ብላ ማዕበል ውስጥ ኑሯውን ካደረገች ወደ ስድስት ሰባት ዓመት ሊሆናት ነው። ከድምጻችን ይሰማ ሉላዊ፤ ሰላማዊ ድንቅ አብዮት ጀምሮ ሲሰላ፤ በቃኝን ተከትሎ ያሉ ወጀቦች ሁሉ ተነሱም፤ ተቀመጡም ፍሬዎቿን ሲለቀሙ ኖረዋል። ለቃሚዎች ደግሞ አሁን ተለቃሚዎች ሁነዋል። ወጀቡ እንደ አገር ለአላዛሯ ኢትዮጵያ እኩል ነው። አደጋውም ያን ያህል ሴንሲቲብ ነው። አሁንም አውሎ ላይ ናት እናት ኢትዮጵያ። ቀላል እርምጃ አይደለም የሰሞናቱ ውሳኔ እና ቁርጠኝነት። እጅግ ደፋር እና እጅግም ልብ የተሸለመው ልባም ድርጊት ነው። አፈጻጸሙ እራሱ ተውኔታዊ ነው። ለነገሩ እኔ በመንፈሳዊ ስለማምን የአምላክ ስራ ነው። በቃችሁ ብሎናል አማኑኤል። ድፍን 50 ዓመት ሲባክን ለነበረው ተከታታይ ትውልድ እንደገና የመፈጠር ያህል ነው። ከአነጋገር ይፈረዳል፤ ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ። · ብ ይን እስቲ ስጡበት። አንድ ሙሉ ቤት በጉንዳን ቢወረር፤ ልብሱ ሁሉም ጉንዳን ቢወረው፤ ምግቡንም ሁሉ ጉንዳን ቢወረው፤ መኝታውንም ሁሉ ጉንዳን ቢወረው የቤቱ ባለቤት መጀመሪያ የቱን ቢያሰቀድም ራሱን አረጋግቶ ከጉንዳን እርግጫ እና ቁንጥጫ...