አቶ ያሬድ ዘሪሁን ወደ ኬኒያ ሊሸሹ ሲሉ

የአቤል እንባ ወደ እዮር ይጮሃል …
„ማንም እራሱን አያታልል ከእናንተ ማንም በዚች ዓለም
ጥበበኛ የሆነ ቢመስለው ጥበባኛ ይሆን ዘንድ ሞኝ ነው።“
ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፲፱ እስከ ፳  
ከሥርጉተ ሥላሴ
15.11.2018
 ከገዳማዊቷ፡ሲዊዘርላንድ።


የቀድሞው የመረጃ እና የደህነንት ሃላፊ እና የፌድራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ጄኒራል አቶ ያሬድ ዘሪሁን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢቢሲ ዘገበ። የአቤል ዕንባ ባክኖ መቼም አይቀረም። የድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶች የ27 ዕንባም ፈሶ አይቀርም። 

እሳቸው ኬኒያ ሌላኛው አቶ ክንፈ ዳኘው ወደ ሱዳን ሌላው ደግሞ ወደ ጁቡቲ ይቀጥላል እንዲህ እያለ ማለት ነው … ቢያንስ  የኢትዮጵያ መንግሥት መረጃውን የጨረሰውን ተጠያቂዎች መቅደም ካልቻለ ሾልከው ይሄዳሉ፤ መሄዳቸው ሳይሆን ክፋቱ እዛም ሆነው ማነኮራቸው አይቀሬ ይሆናል። 

ስለዚህ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ዳታ ብዙ ከእንግዲህ አዋጪ አይመስለኝም። እራሱ ግብረ መልሱም የከፋ ሊሆን ይቻላል፤ እንዲህ ዓይነት ሰው ከጭካኔ ስለማይመለስ በዬቦታው የፍንዳታ የቦንብም ሊሆን ይቻላል ሊከሰት ይችል ይሆናል። አጥፍቶ መጥፋት ተስፋ ከቆረጡ ሰብዕናዎች ስለሚመጡ።

በሌላ በኩል ብዙ ዜናውን አለማሟቅ እና በተደሞ እና በትእግስት ሁኔታውን መከታተል በእጀጉ ያስፈልጋል። በተለይ ከተሞች አካባቢ በጊዜ መግባትን ጨምሮ ሁሉም ዘብ መቆም ይኖርበታል ለዬአካባቢው ደህንነት። 

ዘመን ያሉ ጥያቄዎችንም ተግ አለማድረግ፤ በመንግሥት ላይ ጫና የሚፈጥሩ ሁኔታዎችንም ማስታገስ ያስፈልጋል። ከባድ ሁኔታ ነው አሁን ያለው ሃላፊነት። ሃላፊነት የሁሉም ነውና። በመንፈስም በጸሎትም መንግሥትን መርዳት የዜግነት ግዴታችን ነው።

ዝርዝሩን ውዴቼ ከኢቢሲ ተከታታሉት እንሆ …
# EBC የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት
 ምክትል ሀላፊ የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን በቁጥጥር ስር ዋሉ

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።