ዓለም ያልሞከረችው የአሉታዊ ዴሞግራፊ አዲስ ጥላሸት ምዕራፍ በኢትዮጵያ። #በትምህርት፤ #በዕውቀት፤ ዘርፍም።
ዓ ለም ያልሞከረችው የአሉታዊ ዴሞግራፊ አዲስ ጥላሸት ምዕራፍ በኢትዮጵያ። # በትምህርት ፤ # በዕውቀት ፤ ዘርፍም። " ኃጣን እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አዬሁት። ብመለስም ግን አጣሁት፦ ፈለግሁት ቦታውንም አላገኜሁት። " ( መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፮ ቁ - ከ፴፭ ፴፮ ) አንድ የማህበረ ቅንነት አባልተኛ " አጀንዳ ማስቀዬሪያ ነው " ሲሉ ዕይታቸውን በቅንነት አጋሩኝ። አመሰግናቸዋለሁኝ። ትንሽ ግን ማብራራት ገለጥለጥ አድርጎ መፈተሽ ይገባል። ይህ ተራ ዜና አይደለም። መንፈስን አወላልቆ አምሳያውን የሚገጣጥም የመንፈስ ነቀላና ተከላ የገዳ ሥርዓት ሁነኛ የዘመነ አሉታዊ ዴሞግራፊ ነው። ገዳይ ትልም ነው። # ዴሞግራፊን እኔ በሁለት እከፍለዋለሁኝ። እንዲህ …… 1) አወንታዊ ዴሞግራፊ። 2) አሉታዊ ዴሞግራፊ። 1) አወንታዊውዴሞግራፊ በተፈጥሮ አደጋ፦ በመሬት ለምነት መበላት፤ በቦታ ጥበት ለኗሪወች ምቹ ሁኔታንለመፍጠር ይከወናል። ይህም ሲሆን በመንግሥት በጎ ፈቃድ ብቻ ሳይሆን ከነባር በዕቱ የሚነሳው ህዝብ ሲያምንበት ብቻ የሚከወን # ሰባዕዊነትም ነው ለእኔ። 2) አሉታዊ ዴሞግራፊ ነዋሪው ፈቃዱ ሳይጠዬቅ ተገዶ ሲለቅ። ወይንም እንደ ዶር አብይ መንግሥት የህዝብ ስብጥርን ለመበወዝ በጭቆና እና በመዋጥ ሲከወን ይሆናል። እንዲህ የሚያደርጉ ሥርዓቶች # የፋሺዝም # ቅኝቶች ናቸው። ለዚህም ነው እኔ በጥዋቱ አሉታዊ ዴሞግራፊ ሲከወን አቅጣጫው ፋሺዝም መሆኑን በመረዳት አቅምን በገፍ...