ዓለም ያልሞከረችው የአሉታዊ ዴሞግራፊ አዲስ ጥላሸት ምዕራፍ በኢትዮጵያ። #በትምህርት፤ #በዕውቀት፤ ዘርፍም።

 

ለም ያልሞከረችው የአሉታዊ ዴሞግራፊ አዲስ ጥላሸት ምዕራፍ በኢትዮጵያ።

#በትምህርት #በዕውቀት ዘርፍም።

"ኃጣን እንደ ሊባኖስ ዝግባም

ለምልሞ አዬሁት።

ብመለስም ግን አጣሁት፦

ፈለግሁት ቦታውንም አላገኜሁት።"

(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፮ - ከ፴፭ ፴፮)

 

 

አንድ የማህበረ ቅንነት አባልተኛ "አጀንዳ ማስቀዬሪያ ነው" ሲሉ ዕይታቸውን በቅንነት አጋሩኝ። አመሰግናቸዋለሁኝ። ትንሽ ግን ማብራራት ገለጥለጥ አድርጎ መፈተሽ ይገባል። ይህ ተራ ዜና አይደለም። መንፈስን አወላልቆ አምሳያውን የሚገጣጥም የመንፈስ ነቀላና ተከላ የገዳ ሥርዓት ሁነኛ የዘመነ አሉታዊ ዴሞግራፊ ነው። ገዳይ ትልም ነው።

#ዴሞግራፊን እኔ በሁለት እከፍለዋለሁኝ።

እንዲህ ……

1) አወንታዊ ዴሞግራፊ።

2) አሉታዊ ዴሞግራፊ።

1) አወንታዊውዴሞግራፊ በተፈጥሮ አደጋ፦ በመሬት ለምነት መበላት፤ በቦታ ጥበት ለኗሪወች ምቹ ሁኔታንለመፍጠር ይከወናል። ይህም ሲሆን በመንግሥት በጎ ፈቃድ ብቻ ሳይሆን ከነባር በዕቱ የሚነሳው ህዝብ ሲያምንበት ብቻ የሚከወን #ሰባዕዊነትም ነው ለእኔ።

2) አሉታዊ ዴሞግራፊ ነዋሪው ፈቃዱ ሳይጠዬቅ ተገዶ ሲለቅ። ወይንም እንደ ዶር አብይ መንግሥት የህዝብ ስብጥርን ለመበወዝ በጭቆና እና በመዋጥ ሲከወን ይሆናል። እንዲህ የሚያደርጉ ሥርዓቶች #የፋሺዝም #ቅኝቶች ናቸው። ለዚህም ነው እኔ በጥዋቱ አሉታዊ ዴሞግራፊ ሲከወን አቅጣጫው ፋሺዝም መሆኑን በመረዳት አቅምን በገፍ ላጎረሱ ደጋፊወች ትክክል አለመሆናቸውን በትህትና ሳስብ የኖርኩት። ማስተባበያ አያስፈልገው። አንድ ፖለቲከኛ፤ አንድ ጋዜጠኛ፤ አንድ ነፍስ ያለው የፖለቲካ ድርጅት መሪ መነሻው ይህ ሊሆን ይገባ ነበር። ይህን እርምጃ በንቃት ተከታትሎ ገና ልጅ እያለ መገደብ ይቻል ነበር። ቢሆን የማፍረስ አቅሙ ይሟሽሽ ነበር።

ይህን ያህል ዓለም እማታውቀው አዲስ ሥር ሰደድ በደል በጠራራ ጠሐይም ለመከወን የዶር አብይ መንግሥት ባልደፈረ ነበር። የተጀመረው ከአናቱ አዲስ አበባ እና ዙሪያው ነበር። ሸገር ከተማ እኮ የህልሙ መከወኛ አንደኛው ማሳም ነው። ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ካለፈቃዱ ተፈናቅሎ የአዲስ አበባ ነዋሪ እንዲሆን ተበዬነ። ለምርጫውም ስኬት ጥሩ ሪሶርስም ሆኗል። ስለምርጫ ጠብቁ የሚሉ ስላሉ ስለሱም ከዚህ ቀደም ሃሳቡን በጀርመንኛ ጽፌበት ነበር። አሁንም እጽፍበታለሁ።

#ወደ መነሻዬ እንዲህ።

በዛን ጊዜ በጉሙሩክ /ቤት የተከወነው ዴሞግራፊ የለት ተደርጎ ዝም ተባለ። ያስፈፀሙት ካፒቴን ወሮ አዳነች አቤቤ ነበሩ። እሳቸው ጆከር ናቸው። ከዛ ቀጥሎ የአዲስ አበባ አመራሮችን #የመበወዝ ንቅናቄ ተከወነ። አሁን ጭራሽ በህግ እንዲፀድቅ፤ ህጋዊ ዕውቅና እንዲያገኝ መንገድ ተጀምሯል። ለሽ ብሎ #በለኝ /// #አልጠቀመኝም የሚለው ዕብኑ የኢትዮጵያ ፓርላማም የምናዬው ይሆናል።

#በትምህርት የተሠራው አሉታዊ ዴሞግራፊ።

1) ይህም አዲስ ነው ለዓለማችን። በትምህርት ዘርፍም፤ በዕውቀት ላይ የሚፈፀም ዴሞግራፊ ዲስክርምኔሽን እና አስምሌሽንም ይጫነዋል። የሆነ ሆኖ ቅልብጭ ያለው ዕውነት ዴሞግራፊ የሚሠራበት #በአማራ #ህዝብ ላይ ነው። 3 ሺህ ተማሪወችን ማፈናቀል መጀመሪያ በኦሮምያ ዩንቨርስቲወች ሙከራ ተደረገ። ባህርዳር ቢጠለልሙ ግርባው ብአዴን ከተስፋቸው የተፈናቀሉትን አዋከበ።

2) / አብይ አህመድ ከመጡበት ዕለት ጀምሮ የአማራ ህዝብ #የተረጋጋ የትምህርት / ጊዜ እንዲኖረው አልተፈቀደለትም። በማዕከላዊ ጎንደር 80 ሺህ አባወራ፤ እና እማወራ በራሱ በዕት ሲፈናቀል ተማሪወች ለአንድ ዓመት ከትምህርት ገበታ ተነጠሉ።

3) በዛ አፍላ "ለውጥ" በሚል ብክል ፌካዊ ማደናበሪያ ጭንብል፦ ማለዘዣ ዘመን በዬዩንቨርስቲው የአማራ ልጆች ይገደሉ ነበር። ይሳደዱም ነበር። ቲም ገዱ ድምጥ የለሽም ነበር።

4) ቀጥሎ በይፋ በኦሮምያ 45 ሺህ የአማራ ተማሪወች ተፈናቀሉ። ይህ የተደረገበት በኽረ ጉዳይ የአማራ ልጅ ወደ ትምህርት ቤት እንዳይሄድ፤ ተስፋ ቆራጭ ይሆን ዘንድ ታቅዶ በትምህርት ላይ የተከወነ #ዴሞግራፊ ነው። ይህም ብቻ አይደለም።

5) 18 የደንቢደሎ ዩንቨርስቲ ተማሪወች ታገቱ፤ ተሰወሩ፤ እስከዛሬዋ ዕለት ድረስ የት እንደደረሱ አይታወቅም። ይህም የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አዲሱ የዴሞግራፊ አጥፊ ስልት ነው። #አቤቾ አቶ ወንድም አቤ ቱኩቻው።ይህን በጥልቀት እንዲመረምረው አሳስበዋለሁ። "በአብቹ" ሥርዓት ተመሳጭ እና ፍልቅልቅ ስለሆነ።

6) ይህም ብቻም አይደለም። ገራገሯን ፈቅደው ለቀቋት አስምራ ሹምዬን። ከዛ ቃለ_ምልልስ ሰጠች። ድንቅ ሰላማዊ ሰልፍ አማራ ክልል ብቻ ተካሄደ። ሌሎች ክልሎች ጉዳያቸውም፤ አጀንዳቸውም አልነበረም። የዛሬው ሥራ ፈላጊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ይቀልዱ ነበር በሚዲያ እዬወጡ። አሳዛኙ ገጠመኝ ያቺ ገራገር አስምራ ሹምዬን መልሰው ሰወሯት። መንግሥት እራሱ። ቤተሰም በምን ሁኔታ እንደሚገኝ አይታወቅም። ይህ የተደረገው የአማራ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዳይልኩ #መቀጣጫ ነበር።

7) በህወሃት እና በፌድራሉ ጦርነት ትግራይን ጨምሮ አፋር እና አማራ ክልል ትምህርት የማይታሰብ ሆነ። ትምህርት ቤቶች በበቀል ወደሙ። ዕቃወቻቸው ተዘረፈ። ተሰባበረ፤ ከጥቅም ውጪ ሆነ። ላይላዩን ግልቢያው ቢቆም በስክነት ቢያንስ በደሉን በሥርዓት በዓይነቱ ልክ መሞገት ይገባ ነበር። ይህን ማስተዋል እንዳይቻልም ዶር አብይ ከመጡ ጀምሮ #ከሰበር ዜና ውጪ መደበኛ ዜና መስማት ብርቅ ሆነ። የሚገርመው እሳቸውን የሚሞግቱትም ዛሬ ያን እንደመልካም ነገር ቆጥረው " ሰበር " ዕርዕሰ ጉዳያቸው ሆኗል። ህዝብ ይረበሻል፤ እርጋታውን ይነጥቀዋል ታስቦ አያውቅም። ሁለመናችን ብክል ነው የሆነው።

ስኮላር ሽፕ በልዩነት ሲከወን ቆይቷል። አጤ ስኮላር ሽፕምዲሞግራፊ እያረሰው ይገኛል።

9) በአንድ የፈተና ወቅት የተበሳጩ ወጣቶች ጥያቄ በማቅረባቸው በቀል አዳሩ፤ ቂም መሐያው የሆነው ኦነጋዊው ኦህዴድ በጎጃም ብቻ 12993 ተማሪወችከመደበኛ 12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና ታገቱ። ውሳኔው ትክክል ነው ብለው የወጡ የራሳችን ኢትዮጵያዊ ወገኖችም ነበሩ። በዚህ ውስጥ 12993 እናቶች12993 አባቶች ወይንም አሳዳጊወች በቤተሰብ ሲሰላ በአማካኝ 12993×5= 64965 ህዝብ በሃዘን እንዲዋጥ ተደርጓል። በተስፋው ላይም ዲስክርምኔሽን ተፈጽሞበታል። እኔ ከውስጤ ስለማዝንበት ሁልጊዜ ሳይሰለቸኝ እጽፈዋለሁ። እንደ የትግል መርሆዬም አዬዋለሁኝ። ሂደቱን በጥልቀት መርምሩት።

10) አሁን ዓመት ሊሞላው ነው የአማራ ክልል እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት ጦርነት ከገቡ። በዚህ ውስጥ ዕውቀት???

11) ገና በጥዋቱ የአማራ ሊሂቃን/ መሪወች/ ማህበራዊ አንቂወች/ የሚዲያ ባለቤቶች/ ፀሐፍት.// የጥበብ ሰወች እዬተለቀሙ መገደል፤ መሰወር፤ መታሰር እና መንገላታት በአማራ ህዝብ የህሊና ጥራት እና ጥረት ታልሞ የሚሠራበት የዴሞግራፊው አካልም ነው።

12) በአማራ ሲቢላይዜሽን የሚደመሙ ኢትዮጵያዊ ዜጎችም መቀጫቸው ሆኗል አማረንትንና ትውፊቱን ማክበር ማድነቃቸው። ለዚህም አቶ ታዲዮስ ታንቱ እና በላይ በቀለ ዓይነተኛ ምሳሌ ናቸው። አይደለም አማራ መሆን አማራን ማክበርም በህግ ያስቀጣል።

#አሁናዊ ምፃት።

ይህ በአደባባይ ያዬነው የታዘብነው መከራ ሲሆን በስውር የተከወነው መዳህኒዓለም ይወቀው። ትናንት ልጅ ሞገስ ምፃት ላይ አልደረስንም ሲል ነበር የወጣት ነገር። የሆነ ሆኖ #የበቀሉ #ፋስ ህጋዊ ዕውቅና ያገኝ ዘንድ ሙያዊ ዴሞግራፊ ለመፈፀም #አና ብለው ህግ አርቅቀው ለመከወን ተሰናድተዋል። ዋናው ዒላማቸው #አማራ ነው። ቀጥሎ ሰሜናዊነት ይሆናል። በማዬው ነገር የተመሰጠረ አንቲ ሴሜቲክ ምልክቶችንም አስተውላለሁኝ።

የሆነ ሆኖ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እና ፀረ አማራ ድርችታቸው " ብልጽግና " የስድስት ዓመቱ የጥድፊያ ነቀላ አላረካቸውም። ሁለመናውን መበቀላቸው አልበቃቸውም። እንጀራን፤ ጤፍን ሳይቀር ለማስቀረት እኮ ንቅናቄ ላይ ናቸው። የበጋ ስንዴ እኮ ሚስጢሩ እኮ ነው። የሙዝ በቆስጣም እሱበእሱ የሆነ ፀረ ጤፍ ምርት ንቅናቄ ነው። የማዳበሪያ እገዳውም የጎጃም ገበሬ ጤፍ እንዳያመርት ለማድረግ እኮ ነው። በጥልቀት እዩት። ግን ከበቀል፤ ከቂመኝነት፤ እላፊ ከመሄድ በመቆጠብ። ትርፍ እባካችሁ አትናገሩ። በአምክንዮ መሞገት ይቻላልና።

ይህ ሁሉ መከራ ግን ተጠቂውን የአማራ ህዝብን ወደ አንድ መንፈስ ሊያመጣ አለመቻሉ ይገርመኛል።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

ሥርጉተ©ሥላሴ

Sergute©Selassie

20/05/2024

ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።