ልጥፎች

ከኦክቶበር 27, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ይድረስ ለEthiopian National Dialogue Commission/የኢትዮጵያ ... EthioNDC ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን/ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ምስል
  ይድረስ ለEthiopian National Dialogue Commission/የኢትዮጵያ ... EthioNDC ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን/ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ። "የቅኖች ፀሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው። የኅጥዕ መንገድ በእግዚአብሄር ዘንድ አፀያፊ ነው።" (መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፱፭ ቁ ፰ - ፱) የተከበርከው ብሄራዊ የምክክር ኮሚሽን ሆይ!       #ዕፍታ ። ዘለግ ያለ አቤቱታም፤ ሙግት ነክ ጉዳይ ነው። የማክበር ሰላምታዬን በቅንነት አቀርባለሁኝ። እንዴት ናችሁ? ዬተነሳችሁበት የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ፕሮጀክት ይሳካላችሁ ዘንድ ምኞቴ ነው። ዕውነት እና ፋክት ሸንጋይ ዬሚሹ ባይሆንም፤ ዕውነት እና ፋክት አጃቢ ሠራዊት የለላቸው ቢሆኑም ዕውነት አለን፤ ፋክት አለን ለዛም እንተጋለን ማለት መብት ነውና፦ ይህን ተቀብሎ ግን ሊሳኩ የማይችሉ ሎጅኮችን አቅርቦ መሞገት ደግሞ አስፈላጊ እና መሠረታዊ ጉዳይ ይሆናል። #ውስጠት ። በወፍ በረር እማዳምጣቸው ጉዳዮች አሉ። የአማራን ችግር በተለይ አሁን ያለውን የሞት የሽረት የፋኖ ዕፁብ ድንቅ ተጋድሎ እንዳኛለን፤ እናስማማለን ብላችሁ መነሳታችሁን አዳምጣለሁ። ለመሆኑ ልትታገሉበት ከተሰናዳው ሰነድ አንቀጽ ውስጥ "ፋኖ" የሚል ኃይለ ቃል አለን? የዚህን መልስ መስጠት ስትችሉ፤ እራሱ መልሱ የስኬታችሁ ወቄት መሆን ይችላል። ብዙ ተቋማት የሚወድቁት መሠረታዊ ምክንያት በማኒፌስቷቸው የፖለቲካ ድርጅት ከሆኑ፤ ማህበራት ከሆኑም አታጋይ ሰነዶቻቸው ላይ የሌሉ አቅም እና ጉልበት ሲመጣ ዘለው እንዋኝ ሲሉ አላዋቂ ሳሚ ይሆኑና ሰብዕናቸውም ተቋማቸውም አብሮ ይተናል። የትኛውም ተቋም፤ የትኛውም የፖለቲካ ድርጅት #ከሞረሽ በስተቀር አማራ የሚል ኃይለ ቃል በሌለበት የሐምሌ 5ቱ የአማራ የማንነት እና የህል