ልጥፎች
ከጁላይ 21, 2022 ልጥፎች በማሳየት ላይ
“አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
“ አበበ እንጂ መቼ ሞተ !” “ አበበ እንጂ መቼ ሞተ !” https://www.goolgule.com/instead-he-blossomed-not-died/ July 19, 2022 04:57 pm by Editor Leave a Comment በአሜሪካ ኦሪጎን ጠቅላይ ግዛት እየተካሄደ ባለው የሰሞኑ የአትሌቲክስ ኢትዮጵያ እንደገና ስሟ ከፍ ብሏል። በፖለቲካው የሚታየው መከፋፈልና ጥላቻ በስፖርቱ አከርካሪውን ተመትቷል። የዚህ ድል ምንጭ ምንድነው ? ብለን ወደ ኋላ እንድናይ ያስገድደናል። ተወዳዳሪ የሌለው ወደፊትም የማይኖረው የጀግኖቹን ጀግና አበበ ቢቂላ ማስታወስ የግድ ይላል። አበበ ሮም ላይ በባዶ እግሩ ሲያሸንፍ የዓድዋ ድል ነው በድጋሚ የተበሰረው። ጣሊያኖቹም ይህንን አልካዱም። የክብር ዘበኛው ወታደር አበበ ሲያሸንፍ “ ሮምን የወረረ ኢትዮጵያዊ ” ብለው ዘግበውለታል። “ ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ግዙፍ ጦር አዝምቶ ነበር፤ ሮምን ለመውረር ግን አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ብቻ በቂ ሆኗል ” በማለትም አትተዋል። እነ ማሞ ወልዴና እነባሻዬ ፈለቀ “ ኢትዮጵያ ” የሚል ቱታ ለብሰው ሲያይ ለአገሩ ተሰልፎ ስሟን ማስጠራት የተመኘው አበበ ሐሳቡ መና ሆኖ አልቀረም። ያውም በሮም ላይ፣ ያውም ባዶ እግሩን፣ ያውም የኦሎምፒክን ሬኮርድ ሰብሮ፣ ያውም የመጀመሪያው አፍሪካዊ በመሆን በድል ላይ ድል በመቀዳጀት እናት አገሩን ከተመኘው በላይ ሰንደቋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርጎ...