“አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”


አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”

 

አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”

https://www.goolgule.com/instead-he-blossomed-not-died/         

July 19, 2022 04:57 pm by Editor Leave a Comment


በአሜሪካ ኦሪጎን ጠቅላይ ግዛት እየተካሄደ ባለው የሰሞኑ የአትሌቲክስ ኢትዮጵያ እንደገና ስሟ ከፍ ብሏል። በፖለቲካው የሚታየው መከፋፈልና ጥላቻ በስፖርቱ አከርካሪውን ተመትቷል።

የዚህ ድል ምንጭ ምንድነው? ብለን ወደ ኋላ እንድናይ ያስገድደናል። ተወዳዳሪ የሌለው ወደፊትም የማይኖረው የጀግኖቹን ጀግና አበበ ቢቂላ ማስታወስ የግድ ይላል።

አበበ ሮም ላይ በባዶ እግሩ ሲያሸንፍ የዓድዋ ድል ነው በድጋሚ የተበሰረው። ጣሊያኖቹም ይህንን አልካዱም። የክብር ዘበኛው ወታደር አበበ ሲያሸንፍ ሮምን የወረረ ኢትዮጵያዊ ብለው ዘግበውለታል። ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ግዙፍ ጦር አዝምቶ ነበር፤ ሮምን ለመውረር ግን አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ብቻ በቂ ሆኗል በማለትም አትተዋል።

እነ ማሞ ወልዴና እነባሻዬ ፈለቀ ኢትዮጵያ የሚል ቱታ ለብሰው ሲያይ ለአገሩ ተሰልፎ ስሟን ማስጠራት የተመኘው አበበ ሐሳቡ መና ሆኖ አልቀረም። ያውም በሮም ላይ፣ ያውም ባዶ እግሩን፣ ያውም የኦሎምፒክን ሬኮርድ ሰብሮ፣ ያውም የመጀመሪያው አፍሪካዊ በመሆን በድል ላይ ድል በመቀዳጀት እናት አገሩን ከተመኘው በላይ ሰንደቋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ አድርጎ ያለፍ ዘመን የማይሸረው በማንም የማይረታ ጀግና ነው።

ይህ የኢትዮጵያዊነት ወኔ ወደ እነ ምሩጽ፣ መሐመድ፣ ኃይሌ፣ ደራርቱ፣ ቀነኒሳ፣ መሠረት፣ ጥሩነሽ፣ እና እጅግ በርካታዎች ደም ውስጥ አልፎ አሁን ደግሞ በኦሪገኑ ሌሎች ወርቆችን አፍርቷል። በዚህ ሁሉ ውስጥ አበበን ማሰብ ድሉን እጅግ ስለሚያደምቀው አዲስ አድማስ ጋዜጣ የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ “… ሳተናው እግረ ጆቢራ፤ ሎጋ ቢቂላ ዋቅጂራ …” በሚል ርዕስ ያስነበበውን እዚህ ላይ አትመነዋል።

ታላቁ ገጣሚ ጸጋዬ ገብረመድኀን በትክክል እንዳስቀመጠው አበበ አልሞተም። አለመሞቱን በኦሪገኑ እልህ አስጨራሽ ፉክክር አይተነዋል። ጀግናው አበበ ቢቂላአበበ እንጂ መቼ ሞተ?” ገና ወደፊትም ይኖራል። ዛሬም ባለድል ነው፤ ወደፊትም ባለድል ሆን ይቀጥላል። ኢትዮጵያም ባሸናፊነትና በክብር ትቀጥላለች።

“…ሳተናው እግረ ጆቢራ፤ ሎጋ ቢቂላ ዋቅጂራ…”

አበበ በቂላ በልጅነቱ ስፓርተኛ ነበርበትውልድ መንደሩ፡፡ በወጣትነቱ ክብረ ወሰኖችን በመስበር የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ሆኗልዓለምን ያስደነቀ፡፡ በጎልማሳነቱ በመኪና አደጋ ተሸከርካሪ ወንበር ላይ ሆኖም ስፖርተኛ ነበርተወዳድሮ ያሸነፈ፡፡

ደብረብርሃን አቅራቢያ ጃቶ በተባለች ቦታ የተወለደው አበበ በቂላ፤ እንደአገሬው አኗኗር በልጅነቱ ቄስ ትምህርት ቤትሄዷል፤ የቤተሰቡን ከብቶች አግዷል፡፡ በትውልድ አካባቢው ተወዳጅ የሆነው ግን በስፖርት ነውየገና ጨዋታ ላይ ጎበዝ ስለሆነ፡፡

1944 .. በኋላ፤ በሃያ አመቱ፤ ክቡር ዘበኛ ሠራዊት ውስጥ ሲገባም፤ ከስፖርት ጋር ይበልጥ ተቀራረበ እንጂ አልተራራቀም፡፡ ከውትድርና አገልግሎት ጎን ለጎን፤ በሠራዊቱ የስፖርት እንቅስቃሴ በተለይም በአትሌቲክስና በገና ጨዋታ ጎልቶ ለመታየት ጊዜ አልፈጀበትም፡፡

ከአራት አመታት በኋላ ደግሞ፤ የአበበን የህይወት አቅጣጫ የሚቀይር፤ የኋላ ኋላም የኢትዮጵያን ስም የሚያደምቅ፤ አፍሪካውያንን የሚያኮራ፤ ዓለምን የሚያባንን አጋጣሚ ተፈጠረ፡፡ የበአል ሰልፍ ላይ፤ኢትዮጵያየሚል ፅሁፍ ያረፈበት ቱታ የለበሱ ስፖርተኞችን ሲመለከት፤ በዝምታ ማለፍ አልቻለም፡፡

እነዚህ ስፖርተኞች እነማን ናቸውብሎ ጠየቀ። ስፖርተኞቹ እነማሞ ወልዴና እነባሻዬ ፈለቀ ናቸው፤ ኢትዮጵያን በመወከል በሜልቦርን ኦሎምፒክ የተካፈሉ አትሌቶች፡፡ ከዚያች አጋጣሚ ነው፤ ውስጡ የነበረው የአትሌቲክ ፍቅር ወደ ውሳኔ የተቀየረው፡፡ኢትዮጵያተብሎ የተፃፈበት ቱታ ለመልበስና በዓለም አቀፍ ውድድር አገሩን ወክሎ ለመሳተፍ ቁርጠኛ ጥረት ጀመረ፡፡ በዚሁ አመት የጦር ሠራዊት ብሄራዊ ሻምፒዮና የማራቶን ውድድር ተካፈለበወቅቱ ታዋቂ ከነበሩት አትሌት ዋሚ ቡራቱና ሌሎችም ጋር ተወዳደረ፡፡

ዋሚ ቢራቱ 5ሺና 10 ሜትር የኢትዮጵያ ሪከርድ የጨበጡ ጀግና ስለነበሩ፤ በዚሁ የማራቶን ውድድር እንደሚያሸንፉ ቢጠበቅ አይገርምም፡፡ ሩጫውን በቀዳሚነት እየመሩ ነበር፡፡ ከተወሰኑ .ሜትሮች በኋላ ግን ስታዲዮም የነበረው ህዝብ ያልተጠበቀ ዜና ሰማውድድሩን ከሚዘግቡ ጋዜጠኞች፡፡ አበበ ቢቂላ እየመራ ነው፡፡ማን ነው አበበ፤ ይህ አዲስ ባለታሪክ ማነውበማለት በአድናቆት ሲጠብቅ የነበረው ህዝብ መልስ አገኘአበበ ቢቂላ ለመጀመርያ ጊዜ በተሳተፈበት የማራቶን ውድድር አሸነፈ፡፡ የጥረት እንጂ የአጋጣሚ ጉዳይ አይደለም፡፡ ጀግና፤ ጀግናን ያፈራል፡፡

አበበ ቢቂላ በሌሎች ውድድሮችም አሸነፈ፤ 5 10 ሜትር በአትሌት ዋሚ ቢራቱ ተይዞ የቆየውን ብሔራዊ ሪኮርድ ሲሰብር፤ ኢትዮጵያ አዲስ ጀግና አትሌት ማፍራቷን ተመልክታ በተስፋ በራች፡፡ የአበበ የመጀመሪያ ህልምም እውን ሆነበውድድሮች ባሳየው ድንቅ ብቃት ለኦሎምፒክ ቡድን ተመረጠ፡፡ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለሁለተኛ ጊዜ በምትሳተፍበት የሮም ኦሎምፒክ፤ኢትዮጵያተብሎ የተፃፈበት የብሄራዊ ቡድን ትጥቅ በማድረግ ወደ ሮም አመራ፡፡

ነገር ግን፤ 83 አገራት የተውጣጡ 5 በላይ አትሌቶች በተካፈሉበት የሮም ኦሎምፒክ ላይ፤ የዓለም ህዝብ ትኩረት በአውሮፖውያን አትሌቶች ላይ ነው፤ ስለኢትዮጵውያን አትሌቶች በተለይም ስለ አበበ በቂላ የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ አበበ ቢቂላ ወይም ሌላ አፍርካዊ አትሌት ሊያሸንፍ እንደሚችል አልተጠበቀምከዚያ በፊት አንድም አፍሪካዊ በኦሎምፒክ ታሪክ ሜዳሊያ አግኝቶ አያውቅም፡፡

የሮም ኦሎምፒክ የማራቶን ውድድር ግን፤ የዓለምን ታሪክ ቀየረ፡፡ የውድድሩ ውጤት፤ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፤ ለመላው አፍሪካና ለዓለም ጥቁር ህዝብ ድል ያበሰረ ችቦ አቀጣጣለ፡፡ ኢትዮጵያዊያው አትሌት አበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ  ሮጦ ታላቁን የኦሎምፒክ ማራቶን በአንደኝነት ከማሸነፍም በተጨማሪ፤ 2162 በሆነ ሰዓት አዲስ የዓለም ሪከርድ አስመዘገበ፡፡ በኦሎምፒክ ታሪክ; የሜዳሊያ ባለቤት ለመሆን የቻለ የመጀመሪያው አፍሪካዊ ስፖርተኛ ሆኖ ስሙ በታሪክ መዝገብ በወርቃማ ቀለም ሰፈረ፡፡

አበበ ቢቂላ የማራቶንን ርቀት ሮጦ ያሸነፈውና ሪከርድ ያስመዘገበው፤ በባዶ እግሩ መሆኑ ደግሞ የመላ ዓለም ስፖርት አፍቃሪዎችን በእጅጉ ያስደነቀ ነበርየአበበ በቂላን ስምና የኢትዮጵያን ዝና በመላው ዓለም ተቀርፆ እንዲቀር ያደረገ። ጋዜጠኞች አበበ ለምን ያለ ጫማ በባዶ እግሩ እንደሮጠ ጠይቀውታልዓለም ሁሉ እንዲያውቅ ፈልጌ ነው ሲል የተናገረው አበበ፤ እኛ ኢትዮጵያውያን ሁሌም የምናሸንፈው በጀግንነትና በወኔ እንደሆነ፤ ለዓለም ህዝብ ለማሳወቅ በመፈለጌ ነው ብሏል፡፡ የጣሊያንና የኢትዮጵያን የጦርነት ታሪክ እየጠቀሰ ይሆን

የማራቶን ሩጫው አለወትሮው በምሽት ነው የተደረገው። የሮም ከተማን በቲቪ ለዓለም ህዝብ ለማስቃኘት ውድድሩን እንደጥሩ አጋጣሚ ስለተቆጠረ፤ የሩጫው መስመር የከተማዋን ዋና ዋና ክፍሎችና አደባባዮችን እንዲያካልል ሆኗል፡፡ ፈፅሞ ያልተጠበቀው አበበ በቂላ፤ ከጥቂት .ሜትሮች ሩጫ በኋላ ከሌሎች ሶስት አትሌቶች ጋር ይመራ ጀመር፡፡ የአበበ ሃሳብ ከሃያ ኪሎሜትር በኋላ መሪነቱን ለብቻው ለመቆጣጠር ነው። ግን ቀላል አልሆነለትም፡፡ ሞሮካዊው አትሌት ርሃዲ ወጥሮ ይዞታል፡፡ እንዲህ ጎን ለጎን እንደተናነቁ አርባ ኪሎሜትር ሮጠው፤ የአክሱም ሃውልት የተተከለበት አደባባይ ላይ ደርሰዋል፡፡ አበበ ድንገት ፍጥነቱን ሲጨምር፤ ሞሮካዊው አትሌት ሊቋቋመው አልቻለም፡፡ ከውድድሩ በኋላ ከጋዜጠኛ የቀረበለት ጥያቄም፤ለምንድነው ሃውልቱን ስታይ ፍጥነትህን የጨመርከው;› የሚል ነበር፡፡ ሃውልቱን ሳይ ቁጣ ስለተሰማኝ ነው ብሎ መለሰ አበበ፡፡

ምሽት ነው፤ ሃውልቱን እንዳለፉ ያለው መንገድ ላይ የተተከሉት ኤሌክትሪክ አምፑሎች ግን ጠፍተዋል፡፡ ሮም ሃያል በነበረችበት በጥንት ዘመን፤ ቆፍጣና ወታደሮች አካባቢውን እያንቀጠቀጡ በሰልፍ የሚያልፉበት ታሪካዊ መንገድ ነው። ይህንን ታሪክ ለማስታወስም ነው በአምፑሎች ፋንታ፤ በጥንታዊ የወታደር አለባበስ ያሸበረቁ ሰልፈኞች ችቦ ይዘው መንገዱን ለሯጮች እንዲያበሩ የተደረገው፡፡ የሮምን ሃያልነት ያስታውሳል በተባለው የወታደሮች ሰልፍ መሃል ሰንጥቆ በመግባት ታሪክ ቀየረአበበ፡፡ በማግስቱ የጣሊያን ጋዜጦች በትልልቅ ፊደሎች ጎልቶ የሚታይ ርእስ በመፃፍ፤ አዲስ ስም አወጡለት፤ ሮምን የወረረ ኢትዮጵያዊ የሚል፡፡ የክብር ዘበኛ ወታደር እንደሆነ ጋዜጠኞቹ ስለሚያውቁ፤ ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ግዙፍ ጦር አዝምቶ ነበር፤ ሮምን ለመውረር ግን አንድ ኢትዮጵያዊ ወታደር ብቻ በቂ ሆኗል በማለት ፅፈዋል፡፡

በሚቀጥለው አመት በግሪክ፤ በጃፓንና በቼኮዝላቫኪያ በተደረጉ የማራቶን ውድድሮች ያሸነፈው አትሌት አበበ፤ ከዚያ በኋላ ለበርካታ ወራት በዓለም አቀፍ ውድድሮች ባይካፈልም፤ ስሙ ከዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አልጠፋም። አንዳንዶቹ ኢትዮጵያ ውስጥ ልምምዱንና ውድድሩን እንደቀጠለ ይዘግባሉ፡፡ ሌሎቹ ጋዜጦች ደግሞ፤ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ባለው የጦርነት ስጋት ሳቢያ ወደ ድንበር እንዲዘምት መመደቡ ይወራል በማለት ፅፈዋል፡፡    

የዓለም ሚዲያዎች እንዲህ እንደጓጉ አራት አመት አለፈና የጃፓን የቶክዮ ኦሎምፒክ ደረሰላቸውዝነኛውን አበበ በኦሎምፒክ ማራቶን ለማየት፡፡ ይሁንና፤ በዚህ የጉጉት ፈንጠዝያ መሃል፤ አስደንጋጭ ወሬ ተሰማአበበ ታመመ፡፡ ኢትዮጵያውያን በድንጋጤና በሃዘን ሲዋጡ፤ ስፖርት አፍቃሪ የዓለም ህዝብ ግራ ተጋባ፡፡ አበበ በትርፍ አንጀት ህመም መሮጥ ተቸግሯል፤ ካልታከመ መኖር አይችልም፡፡ የቀዶ ጥገና ህክምና ቢደረግለት ደግሞ የማገገሚ ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡ ለኦሎምፒክ የቀረው ጊዜ ከሁለት ወር ያነሰ ነው፡፡ ወከባ ሆነ፡፡
የቶኪዮ ኦሎምፒክ 6 ሳምንታት ሲቀሩት፤ የቀዶ ህክምና ተደረገለት፡፡ በፍጥነት እንደሚያገግም ተስፋ በማድረግ፤ የኦሎምፒክ ቡድን ውስጥ መካተቱ አልቀረም፡፡ ገና ጤናው ስላልተመለሰ እያነከሰ ነው የሚራመደው፡፡ ቢሆንም በቶክዮ የተደረገለት ልዩ የአድናቆትና የፍቅር አቀባበል፤ በፍጥነት እንዲያገግም እንዳገዘው ይነገራል፡፡ እንዲህም ሆኖ፤ በውድድር ይሳተፋል ተብሎ አልተጠበቀም፡፡ በእርግጥ በሮም ከተማም ያሸንፋል ተብሎ ሳይጠበቅ ነው፤ ዓለምን ጉድ ለማሰኘት የበቃው፡፡ በቶክዮ ተመሳሳይ ታሪክ እንዲደገም ተስፋ ያደረጉ አልጠፉም፡፡

አበበ ከእነማሞ ወልዴ ጋር እዚያው ቶክዮ ውስጥ ለጥቂት ቀናት አነስተኛ ልምምድ ለማድረግ ከሞከረ በኋላ፤ ሙሉ ለሙሉ ባያገግምም ለሩጫው ብቁ ነኝ ብሎ ገባ፡፡ እንደለመደው ከዋና ዋናዎቹ መሪዎች ጋር መሮጥና ከግማሽ ርቀት በኋላ መሪነቱን ለመቆጣጠር አስቧል፡፡ ያሸንፋል ብለው ያላሰቡት አድናቂዎቹ፤ በውድድሩ በመሳተፉ ብቻ ፈንድቀዋል። ገና ብዙ ደስታና ፈንጠዝያ እንደሚጠብቃቸው አላወቁም፡፡ ከግማሽ ርቀት በኋላ በቀዳሚነት መምራት ጀመረ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ 6 ሳምንት በፊት ቀዶ ጥገና የተደረገለት አይመስልምአሯሯጡ የአትሌቲክስ ባለሙያዎችን የሚያስደንቅ ነበር፡፡
የኦሎምፒክ ማራቶን አስደናቂ ውድድሮች ተብለው በመፅሃፍ ከታተሙት ታሪኮች ውስጥ፤ አበበ በቶክዮ ያሳየው ብቃት ዋና ተጠቃሽ በመሆን፤ እንከን የለሽ ማራቶን ሯጭ የሚል ስያሜ አስግኝቶለታል፡፡

መፅሃፉ እንዲህ ይላል -‹አበበ ደረጃ በደረጃ ፍጥነቱን ጨመረ፤ ሳይዋዥቅ በሚፈልገው ፍጥነት እቅጩን ነው የሚሮጠውከተሟላ ትኩረት ጋር፡፡ ከዚህ የላቀ ፍፁምነት የለም፤ እንከን የለሽ ማራቶን ሯጭ እንዲህ ነው፡፡ የቀዶ ጥገና ህክምናውም ሆነ የቶክዮ ከባድ የአየር ፀባይ አበበን የሚበግሩ አልሆኑም፡፡ ብዙ ጉልበት ሳያባክን የመሮጥ ጥበብ የተካነው አበበ፤ አንገቱን እንዳቀና የመፍሰስ ያህል ይሮጣል፤ የሩጫው መንገድ በአበበ እግሮች ስር የተንሳፈፈ ይመስላል፡፡

የማራቶን ጥበበኞች የተሰኘ ሌላ መፅሃፍም፤ ተመሳሳይ አድናቆት አስፍሯልጎበዝ ሯጮች በርካታ መመዘኛዎችን ያሟላሉ፤ አበበ ግን የማራቶን አትሌት ሊመኝ የሚችለውን ሁሉ መመዘኛ ያሟላል፤ ታይቶ የማይታወቅ አትሌት ነውሲል ፅፏል፡፡ በውድድር መሳተፉ አጠራጣሪ የነበረው አበበ በአስደናቂ ብቃት፤ ሌሎች ተወዳዳሪዎችን በአምስት ኪሎሜትር ርቀት አስከትሎ ስቴድዮም ሲገባ70 የሚበልጥ ህዝብ በዚህ ዓለም እንደገና ለማየት የሚናፍቅ ጀግንነት በአይናቸው በብረቱ ለመመልከት በመብቃታቸው ከተቀመጡበት ተነስተው፤ ደስታና አድናቆታቸውን በሆታ ገለፁ፡፡ አድናቆታቸው ሳይበርድ፤ ሌላ ተጨመረበት፡፡

ከቀዶ ጥገናው ሙሉ ለሙሉ ሳያገግም አሸናፊ የሆነው አበበእሱን ተከትለው የገቡ አትሌቶች እየተዝለፈለፉ ድጋፍ ሲፈልጉ፤ አበበ ግን ጅምናስቲክ በመስራት ስፖርት አፍቃሪውን ህዝብ አስገረመ፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፤ በድጋሚ የዓለም ሪከርድ አሻሽሏል – 21211 በሆነ ሰአት በመግባት፡፡ በሁለት የኦሎምፒክ ማራቶን አከታትሎ ሁለት የወርቅ ሜዳልያዎች በማግኘት፤ አበበ ብቸኛው አትሌት ነው፡፡

እንዲህ ታሪክን በመቀየር፤ ዓለምን ያስደነቀው፤ ለኢትጵያና ለአፍሪካ አነቃቂ ጀግንነትን ያስመሰከረው አበበ በቂላ፤ በሌሎች ሶስት ማራቶኖችም አሸንፏል፡፡ ከዚህ በኋላ የአበበ እግሮች ያለሙት ወደ ሜክሲኮ ኦሎምፒክ ነበር። የሜክሲኮ ከፍተኛ የመሬት አቀማመጥ ከአዲስ አበባ ጋር ስለሚቀራረብ እንደሚስማማው አውቋልለሌላ አገር አትሌቶች ግን ይከብዳል፡፡ በዚያ ላይ ጥሩ የብቃት ደረጃ ላይ እንደሆነ ቀደም ብለው በተደረጉ ውድድሮች አሳይቷል፡፡ አበበ እንደሚያሸንፍ ምንም ጥርጥር አልነበረኝም በማለት ማሞ ወልዴ የመሰከረውም ይህንን በመመልከት ነው፡፡ ነገር ግን እግር ውስጥ የተሰበረ አጥንት ይዞ እንዴት መሮጥ ይቻላልለዚያምው ማራቶን፡፡

ኢትዮጵያን በመወከል ለመወዳደር የተሰለፈው አበበ ቢቂላ 15 ኪሎሜትሮችን ከሮጠ በኋላ፤ እንደተፈራው ህመሙ ከአቅም በላይ ሆኖበት ውድድሩን ለማቋረጥ ተገደደ፡፡ አበበ ውድድር ሲያቋርጥ፤ የኢትዮጵያውያንና የአፍሪካዊያን አሸናፊነት አልተቋረጠም፡፡ ጀግና ጀግናን ያፈራል፡፡ ከአበበ ጋር እየሮጠ የነበረው ኢትዮጵያዊ ጀግና አትሌት ማሞ ወልዴ፤ ሳይጠበቅ ድል አድርጎ የማራቶንን ክብር ለኢትዮጵያ አጎናፀፈ።

26 በላይ ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድሮችን የተካፈለው አበበ፤ ከኦሎምፒክ ውጤቱ በተጨማሪ 1952 እና 54 .. የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በማራቶን አከታትሎ በማሸነፍ ድንቅ ታሪክ ሰርቷል፡፡

በማራቶን ታሪክ በወንዶች የመጀመርያው የዓለም  ሪከርድ የተመዘገበው እኤአ 1908 በለንደን ማራቶን በአሜሪካዊው ጆን ሄይስ 2 ሰዓት 35 ደቂቃ 18 ሰኮንዶች በሆነ ጊዜ ነበር፡፡ ይህ የመጀመርያ ሪከርድ ከተመዘገበ 32 ዓመታት በኋላ የዓለም ማራቶን ሪከርድ ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያዊ አትሌት የተመዘገበው 1960 እኤአ ላይ በሮም ኦሎምፒክ በባዶ እግሩ ሮጦ ባሸነፈው አበበ ቢቂላ ነበር፡፡ በወቅቱ አበበ ያስመዘገበው የማራቶን ክብረወሰን 2 ሰዓት 16 ደቂቃዎች 23 ሰኮንዶች በሆነ ጊዜ ነበር፡፡ 4 ዓመታት በኋላ አበበ ቢቂላ ለሁለተኛ ጊዜ የማራቶን ሪከርድን 1964 እኤአ ላይ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ያስመዘገበ ሲሆን ጊዜውም 2 ሰዓት 12 ደቂቃዎች 11 ሰኮንዶች፡፡ አበበ በቂላ በኦሎምፒክ መድረክ ባስመዘገበባቸው ሁለት የዓለም የማራቶን ሪከርዶች ለአምስት አመታት ነግሶ ቆይቷል፡፡ የዓለም ማራቶን ሪከርድን ሊያዝ የበቃው ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ከአበበ ቢቂላ ሪከርዶች 24 ዓመታት  በኋላ በላይነህ ዴንሳሞ ነበር፡፡

ዓለም በመሰከረለት ጀግንነቱና ብቃቱ፤ ዘላለማዊ ህያውነትን የተቀዳጀው አበበ በቂላ፤ 1960 .. ከአዲስ አበበ ወጣ ብላ በምትገኘው ሸኖ ከተማ መኪናውን እያሽከረከረ የትራፊክ አደጋ ሲደርስበት፤ ዓለም ሁሉ ከኢትዮጵያውያን ጋር ደንግጧል፤ አዝኗል፡፡ በአገር ውስጥና በእንግሊዝ ህክምና ቢወስድም፤ በአደጋው የደረሰበት ጉዳት ከፍተኛ ስለነበረ፤ ከወገቡ በታች የሰውነት አካሉንና እግሮቹን ማንቀሳቀስ አልቻለም፡፡ ነገር ግን፤ የአትሌትነትና የስፖርተኛነት መንፈሱ እንደድሮው ብርቱ ነበር፡፡ በተሸከርካሪ ወንበር የአካል ጉዳተኞች በሚሳተፉባቸው ዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ለማሸነፍ በቅቷል፤ እንደገና የሀገሩን ባንዲራ በዓለም መድረክ እንዲውለበለብ አድርጓል፡፡ ከደረሰበት የትራፊክ አደጋ በኋላ ሁለት አመት በማይማላ ጊዜ፤ በኖርዌይ በተከናወነው 25 እና 10 .. የአካል ጉዳተኛ ውድድሮች በማሸነፍ ፈር ቀዳጅነቱን በድጋሚ አስመስክሯልለአገራችን የአካል ጉዳተኞች ስፖርት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ በመሆን፡፡

አበበ ቢቂላ ከሺ አመት እስከ አመት ሲወደስ የሚኖር ህያው የጀግንነት ታሪክ የሰራው፤ በዚህ ዓለም በቆየባቸው 41 አመታት ውስጥ ነው፡፡ በአንጎል የደም መፍሰስ ምክንያት አበበ 1965 .. ሲያርፍ፤ በከፍተኛ ሃዘን የተመታው የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቁን ጀግና ባለታሪክ በክብር ሽኝቷል፡፡ የአበበ ቢቂላ የቀብር ስነስርአት የተፈፀመው ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በተገኙበት በአዲስ አበባ የቅዱስ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን መካነ መቃብር ነው፡፡

ለማራቶኑ አምበል ሻምበል አበበ ቢቂላ ባለቅኔ ጸጋዬ ገብረመድህንአበበ እንጂ መቼ ሞተ!!” ሲል የፃፈው ሥነግጥም  እንዲህ ይላል፡፡

የጎበዝ ነባቢት ነፍሱ
የሰው መዝርዕቱ አርአያ፤ የማይታጠፍ መንፈሱ
በጥራት የታጠፈለት፤ የምድር አጥናፍና አድማሱ
የየብስ የአየሩ ነበልባል
የማራቶን እፁብ አይጣል
የምድር አለሙ ገሞራ
አገሩን በክብር ያስጠራ
ሳተናው እግረ ጆቢራ
ሎጋ ቢቂላ ዋቅጂራ፤
የጎበዛዝ ንጥረ ወዙ
የተስፋ ብርሃን መቅረዙ።
ስሙን ላገር ስም ሰይሞ፤ የምስራች ያስደወለ
ስንቱን ስንቱን ልበ ሙሉ፤ ከአድማስ አድማስ ያስከተለ፡፡
የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ
ያረጋት የኦሎምፒክ አርማ
በወገኖቹ ልቦና፤ ቀና ኩራት ያሳደረ
እንደፍላፃ በአክናፉ፤ የአየርን ሰርጥ የሰበረ
የፍስሃዋን አዋጅ ለዓለም፤ በአቅመ ወዙ ያስነገረ
በአገር ፍቅር ልቡን ሞልቶ፤ ላቡን ነጥቦ የዋተተ
የዓለምን ጀግና በአድናቆት፤ በቅን ቅናት ያስሸፈተ
አልሞተም እንበል እባካችሁ፤አበበ እንጂ መቼ ሞተ!”   

(ግሩም ሠይፉ፤ አዲስ አድማስ፤24 December 2017)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።