ልጥፎች

ከኤፕሪል 5, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#ትህትናችሁ ዘወትር ቁሞ ለሚያስተምረኝ ቅኖቼ ሁሉ።

ምስል
  #ትህትናችሁ ዘወትር ቁሞ ለሚያስተምረኝ ቅኖቼ ሁሉ።   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       የምትናፍቁኝ፤ የምሳሳላችሁ፤ አዘውትሬ የማስባችሁ፤ ክብሮቼ የአገሬ ልጆች እንዴት አድራችሁ፤ አርፍዳችሁ፤ ዋላችሁልኝ? እኔ እግዚአብሄር ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። የምርም ደህና ነኝ።   ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በዓጤ ፌስቡክ ዕይታዬን #በምራፍ ከፋፍዬ ሥሰራ ቆይቻለሁኝ። እስከ አሁን ፲፰ ምዕራፎችን ሠራሁኝ። ሳጠናቅ አዲስ ምዕራፍ ከመጀመሬ በፊት ጥሞና እወስዳለሁኝ።    ምዕረፍ ፲፰ ረጃጅም የወግ ገበታወችን ያቀርብኩበት ምዕራፍ ነበር። በብሎጌ ላይም ሰፊ አንባቢ አግኝቷል። ጹሁፎቹ በብዙ ሁኔታወች ያልተደጋገሙ፤ አትኩሮቱም በተለዬ የእኔ ምርጫ የሆኑትን ብቻ በመለየት አቅም ተመግበዋል።    ምዕራፎቼ ሚዲያው ሁሉ ከሚረባረብበት አጀንዳ #ወጣ ያሉ ሃሳቦች የቀረበበት ነበር። አስፈላጊ ሲሆን ሁሉም እንደ አጀንዳ ያዬው ግን #ሲርገበገብ ሳይሆን ሲሰክን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁኝ።   ይህ ፔጅ አክሰሱ ላላቸው ታዳጊ ወጣቶች ከሁሉም የአያያዝ፤ የአመራር፤ የአነጋገር፤ የአፃፃፍ ኢትዮጵያዊ ሥርዓታዊ ሂደት ይማሩበት ዘንድ በፍጹም ጥንቃቄ ለመሥራት ሞክሬያለሁኝ።   ከዚህ ፔጅ ያልተገቡ ፆታዊ ጉዳዮች፤ ቃሎች ኖረው ግን ከደረጃ የሚያወርድ የአፃፃፍ ዘይቤወችን፤ ከፎቶ ላይ የሚፃፋ #ነውረኛ ሁነቶችን፤ ኢትዮጵያ መለያዋ ከሆነው አክብሮ ከመፃፍ፤ ከመሞገት አንፃርም #አንቱታን በማስቀጠል፤ ሙሉ ስድስት ዓመት በትጋት ስለሰራሁበት ፔጃችን በዲስፕሊን የታነጹ የሁሉም ፖለቲካዊ ዕይታወች፤ የሁሉም ዕምነት ዶግማና ቀኖናወች አክብሮ ሲያስተናግድ ቆይቷል።   በዚ...

ኢራንን #በእግረኛ ጦር ……… እና ተስፋው በስሱ።

ምስል
  ኢራንን #በእግረኛ ጦር ……… እና ተስፋው በስሱ።    "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።       ስጋትን ለማስወግድ ቁልፋ በእግዚአብሄር በአላህ #መታመን ነው። 1) ኢራንን የሚሰጉ አገሮች አሉ። 2) አሜሪካንን የሚሰጉ አገሮች ይኖራሉ። 3) ራሺያን የሚሰጉ አገሮች አሉ። 4) እስራኤልን የሚሰጉ አገሮች አሉ። 5) እንደ ቃልኪዳን የጦር አቅም ኔቶንም የሚሰጉ አሉ። 6) ተስፋን የሰጠ፤ ተስፋችን የሚጠብቅ፤ ለተስፋችን ተፈፃሚነት እርግጠኛ የሚያደርግ አምላክን፤ አላህን ከውስጥ ማመን ቢቻል #ስጋቱ አቅም እንዳይኖረው አድርጎ የማክሸፍ ሥልጣነ ክህሎቱ #የእዮር ሊሆን ይገባል።   የሰው ልጅ በአምላኩ ካለው መታመን ይልቅ #ለፖለቲካ ፍላጎቱ #መታመን ስለሚያደላ እንሆ ትውልድ ሁልጊዜ #በጦርነት ጢስ እና #ጭንቅ ይታመሳል።    የሰው ልጅ #በመሸነፍ ውስጥ #ማሸነፍ መኖሩን ቢመረምር፤ በስክነት ስኬቱን ቢይ፤ ተሸንፎም ባለ ዕድል የመሆን አቅሙ ሊጎለብት ይችላል። በተለይ በጦርነት መሸነፍን ተቀብሎ የእግዚአብሄርን የአላህን ፍጡር መታደግ #የጽድቅ ጎዳናም ነው።    ይህም ብቻ አይደለም ይህ መርዛማ ኬሚካል ምድርን #ይበክላል ። ቀጣዩ ትውልድ በሙሉ የጤና ሁኔታ #ስለመፈጠሩም እርግጠኛ የሚደርግ ጭብጥ የለም። መሬትም #ተሰቃዬች ። አዝዕርትም #ፍዳቸውን አዩ። ተፈጥሮ ተሳቀቀ። እግዚአብሄርም አላህም #አለቀሰ ። #ኢራንን በእግረኛ ለመግጠም ባይሞከር ምርጫዬ ነው። ለምን?    #መስዋዕትነቱ የከፋ ስለሚሆን።    #እንዴት ? #የገዢ መሬት እና #የሙት መሬት ዕጣ።    1) የኢራን እግረኛ ዘገባወች እንደሚያመለክቱት...