#ትህትናችሁ ዘወትር ቁሞ ለሚያስተምረኝ ቅኖቼ ሁሉ።
#ትህትናችሁ ዘወትር ቁሞ ለሚያስተምረኝ ቅኖቼ ሁሉ።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።

የምትናፍቁኝ፤ የምሳሳላችሁ፤ አዘውትሬ የማስባችሁ፤ ክብሮቼ የአገሬ ልጆች እንዴት አድራችሁ፤ አርፍዳችሁ፤ ዋላችሁልኝ? እኔ እግዚአብሄር ክብሩ ይስፋ ደህና ነኝ። የምርም ደህና ነኝ።
ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በዓጤ ፌስቡክ ዕይታዬን #በምራፍ ከፋፍዬ ሥሰራ ቆይቻለሁኝ። እስከ አሁን ፲፰ ምዕራፎችን ሠራሁኝ። ሳጠናቅ አዲስ ምዕራፍ ከመጀመሬ በፊት ጥሞና እወስዳለሁኝ።
ምዕረፍ ፲፰ ረጃጅም የወግ ገበታወችን ያቀርብኩበት ምዕራፍ ነበር። በብሎጌ ላይም ሰፊ አንባቢ አግኝቷል። ጹሁፎቹ በብዙ ሁኔታወች ያልተደጋገሙ፤ አትኩሮቱም በተለዬ የእኔ ምርጫ የሆኑትን ብቻ በመለየት አቅም ተመግበዋል።
ምዕራፎቼ ሚዲያው ሁሉ ከሚረባረብበት አጀንዳ #ወጣ ያሉ ሃሳቦች የቀረበበት ነበር። አስፈላጊ ሲሆን ሁሉም እንደ አጀንዳ ያዬው ግን #ሲርገበገብ ሳይሆን ሲሰክን ለመዳሰስ ሞክሬያለሁኝ።
ይህ ፔጅ አክሰሱ ላላቸው ታዳጊ ወጣቶች ከሁሉም የአያያዝ፤ የአመራር፤ የአነጋገር፤ የአፃፃፍ ኢትዮጵያዊ ሥርዓታዊ ሂደት ይማሩበት ዘንድ በፍጹም ጥንቃቄ ለመሥራት ሞክሬያለሁኝ።
ከዚህ ፔጅ ያልተገቡ ፆታዊ ጉዳዮች፤ ቃሎች ኖረው ግን ከደረጃ የሚያወርድ የአፃፃፍ ዘይቤወችን፤ ከፎቶ ላይ የሚፃፋ #ነውረኛ ሁነቶችን፤ ኢትዮጵያ መለያዋ ከሆነው አክብሮ ከመፃፍ፤ ከመሞገት አንፃርም #አንቱታን በማስቀጠል፤ ሙሉ ስድስት ዓመት በትጋት ስለሰራሁበት ፔጃችን በዲስፕሊን የታነጹ የሁሉም ፖለቲካዊ ዕይታወች፤ የሁሉም ዕምነት ዶግማና ቀኖናወች አክብሮ ሲያስተናግድ ቆይቷል።
በዚህ ፔጅ #ሳቅ ይፈቀዳል፤ በእኔ ጹሁፍ ላይ ስላቅም ይፈቀዳል፤ ሙግት ህግ ሳይተላለፋ በታረመ አንደበት ይፈቀዳል። #ዘለፋ፤ ስድብ፤ መዳፈር፤ ጭካኔ ግን አይፈቀድም። የእኔን ሃሳብ ብቻ ሳይሆን በፔጁ ባሉት ወዳጆቼ ፔጅ ላይም ያልረባ መልዕክት ከተፃፈ መራራ ስንብት ይሆናል። በብዙ ድካም፤ በብዙ የራስን ነገር ቸል ተብሎ የሚደከምበት ፔጅ ስለሆነ።
በሰብአዊነት ጉዳይ፤ በሰዋዊነት አመክንዮ፤ በተፈጥሮ ጸጋ ለሚተጉ የአገሬ ልጆች፤ ፔጁ ሁልጊዜም #በክብር ሲያስተናግድ ቆይቷል። ወደፊትም ይቀጥላል።
ለእኔ ትልቁ ምኞቴ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሰዋዊ፤ ተፈጥሯዊ ይሆን ዘንድ መትጋት ነው። በአገሬ በኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኛ እንዲኖር ፈጽሞ #አልፈልግም። ስለሆነም በዚህ ዙሪያ እና በሰብአዊ መብት ጥሰት ከትክክለኛ አካል መረጃውን ካገኜሁኝ በቀጣይም እምተጋበት ይሆናል።
በሃሳብ ይሁን በድርጊት ለተገባው አካል፤ የተገባ የሃሳብ ሙግት ከኖር ተከብሮ ግለሰቡም ይሁን ተቋሙ ተሞግቷል። ወደፊትም ይሞገታል።
ፔጁ የትውስት ሃሳብ፤ ወይንም ከሌላ ኮፒ ሁነት ስለማያስፈልገው በእራሴ ፖለቲካዊ ዕምነት እና ፍልስፍና፤ በህይወት መርሆቼ እና ፋክቶቼን ብቻ ምንጭ አድርጌ ዕይታዬን ዘለግ አድርጌ አቅርቤያለሁኝ። በውነቱ ከቃል እንኳን ከሌላ መኮረጅ አይታሰብም።
በምዕራፍ ፲፰ ብዙ ጊዜ የBBC ዘገባ መነሻ አድርጌ ጽፌያለሁኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የምርጫ ሁነትም በሰላም ለመታገል ለሚሹ የተፎካካሪ ፓርቲወች ዕድላቸውን #እንዳያፈሱ በትህትና ከማሳሰብ በተጨማሪ፤ በፋና ቴሌቪዥን በሚቀርቡ ክርክሮችንም ከውስጤ በማድመጥ ዕይታዬን አጋርቻለሁኝ።
ዛሬም አንድ ያዳመጥኩት ጥሩ ውይይት አለ። ሼር አደርገዋለሁ። የተሻለ ጊዜ እና ጥሩ ውይይት ነበር። መቼ የተፈጠረ እንደሆን፤ ለምን እንደተፈጠረ የማላውቀው "#ህዳሴ" የሚባል ፓርቲም ዛሬ ሰምቻለሁኝ። ፓርቲ ለኢትዮጵያ ከፋፍሪካ የሚመረት ጨርቅ ሆኗል። በውነቱ ሲገርመኝ ነበር ያረፈደው። እንደ እኔ ሙሉ አባሉን አካሉን ይዞ #ከብልፄው ጋር ቢዋህድ ምርጫዬ ነው። አጤ የፖለቲካ ፓርቲ በኢትዮጵያ #ቁጥርን ከሚያጨናንቅ።
የሆነ ሆኖ፤ ስሰራው የቆየሁት ምዕራፍ ፲፰ ህወሃት ፈቅዶ መንበረ ሥልጣኑን የለቀቀበት ፱ኛ ዓመት ተጀምሯል። ይህ ሁነት አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር አስፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል።
እግዚአብሄር ይመስገን #ከህማማት ጋር ግጥም ብሎልኛል። ምክንያቱም ሁልጊዜ ምዕራፎቼን ሳጠናቅቅ የጥሞና ጊዜ ይኖረኛል። ጊዜ አጥቼ ያላዳመጥኳቸውን አዳምጣለሁኝ። ከሞጋችነት ወጥቼም ክስተቶችን ለመገምገም በእጅጉ ይረዳኛል።
ጸጥ ያለ የሰከነ የሃሳብ ጊዜ #ነፍሴ ትሻለች። ይህ የዘወትር የህይወት መርሄ ቢሆንም ምዕራፍ አዲስ ከመጀመሬ በፊት የሚኖረኝ ጊዜ ለራሴ ነፃነት በገፍ ሸልሜ ሰፊ የጸጥታ ጊዜ ይኖረኛል።
ጊዜው ግሎባል፤ አህጉራዊ፤ ብሄራዊ ጉዳዮችን፤ የራሴንም ጤና እና ውበት እምከታተልበት ይሆንልኛል። ስለዚህም #በናፍቆት የምጠብቀው ወቅት ነው።
በተረፈ የእኔ ክብሮች #በልግሥና ለሰጣችሁኝ ጊዜ፤ #በትህትና ላጋራችሁኝ ልምድና ተመክሮ፤ በጓዳም መጥታችሁ ለምትነግሩኝ፤ ለምትሰጡኝ ገንቢ ሃሳብ ውለታ ሸላሚው አማኑኤል የልባችሁን ያድርስልኝ። አሜን።
ህማማቱን ከውስጣችን ሆነን ለአገራችን እና ለዓለም ሰላም ብንተጋበት ጥሩ ነው። ለተንሳኤ ስለማላገኛችሁ ለብርኃነ ተንሳኤው አማኑኤል አባቴ ያድርሳችሁ፤ ያድርሰን። አሜን።
ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን።
ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።
ኑሩልኝ። አሜን።
ሥርጉተ©ሥላሴ።
Sergute©Selassie.
05/04/026.
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ