ልጥፎች

ከሜይ 11, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የቃልቋንጣ (የወግ ገበታ)

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ  የቃል ቋንጣ ። „የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፤ እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብን ና ክብርን ያጠፋል።“ መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፲ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 10.05.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። የወግ ገባታ። ከሥርጉተ© ሥላሴ (Sergute© Selassie) የአላዛሯ ኢትዮጵያ ራህቧ እውነት ብቻ ነው። ·          መ ቅድም ። ·          በ ድምጽ። ·            https://www.youtube.com/watch?v=HS0Gm_tMll8 የቃልቋንጣ (10 05 2019) ·          እ ፍታ። እንደምን ናችሁ የኔዎቹ ቅኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? የንጉሦች ንጉሥ አጤ ቴወድሮስ የሚታወቁበት ሥነ - ቃል „ቃል የዕምነት ዕዳ ነው“ የሚለው ዘመን ተሻጋሪ ፍልስፍናቸው ነው። ለነገሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድም በአብዛኛው ሰው ልብ ሊመሰጠሩ የቻሉበት „ቃል ይተክላል፤ ቃል ይነቅላል፤ ኢትዮጵያም የተተከለችውም፤ የተነቀለችውም በቃል ነው“ ያሉት ሁላችንም ልባችን የሸለምንበት አምደ ጉዳይ ነበር። ምን ያህል በቃላቸው ውስጥ እንዳሉ ህዝብ መስታውቱ ስላለው የህዝብ ህሊና ይዳኘው። መይሳው ካሳ አጤ ቴወድሮስ ግን በቃላቸው ውስጥ ሰክነው፤ ቃላቸውን ቋንጣ ሳያደርጉ፤ ቃላቸውን ሳያጠንዝሉ፤ ቃላቸውን ፍርሃትን ሳይቀልቡ ፤ ለውጭ አገር ጠላት እጄን አሳልፌ አልሰጥም፤ ትውልዱንም ዕድሜ ልኩን በቅኝ መንፈስ አንገት አላስደፋም ሲሉ ጀግናውን ገብርዬን ተከትለው የድል ጽዋውን እንደ ቃላቸው አጬጌውታል። ·          መ ሪና ቃሉ። መሪ ማለት ቃ