አጋጣሚሰጥ ስሜት ምንድን ነው?
አጋጣሚሰጥ ስሜት። „ከቸር ሰው ጋር ቸር ሁነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ ከንጹህ ጋር ንጹህ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማ ጋር ጠማማ ሁነህ ትገኛለህ።“ (መዝሙር ምዕራፍ ፲፯ ከቁጥር ፳፭ እስከ ቁጥር ፳፮) ከሥርጉተ © ሥላሴ 09.07.2018 (ከገዳማዋቷ ሲዊዝሻ።) ስሜት የሰውነት ቋንቋ ነው። ስሜት የመንፈስ መርከብ ነው። ስሜት የነፍስ ተልዕኮ ነው። ስሜት ረቂቅ ነው። ስሜትን የሚተረጉሙ ሁነቶች የመኖራቸውን ያህል የስሜትን ትክክለኛ ገጸ ባህሪ ሊገልጹ የማይችሉ ሁነቶችም ይገጥማሉ። ሥም የለሽ ስሜቶች እንደ ማለት። ይህን እኔ ያወቅኩት የኤርትራ ልዑክ አዲስ አባባ ሲገባ የተሰማኝን አዎንታዊ ስሜት መልኩ፤ ቁመናው፤ ይዘቱ፤ አፈጣጠሩ፤ ሂደቱ፤ አቅጣጫው በፍጹም ሁኔታ ስሜቴን ማወቅ ከቻልኩበት ዘመን ጀምሮ አዲስ እና የተለዬ ነበር። ለዚህን ያህል ዘመን ይህን መሰል ሥም የለሽ ስሜት እንዳለኝ አለማወቄ ብቻ ሳይሆን ሌላም አጋጣሚ ቢፈጠር እንዲሁ በተቀማጭንት ያሉ ሌሎች የስሜት ዓይነቶችም ሊኖሩ እንደሚችሉ አሁን አዲስ ምናባዊ መስመር ያበጀሁላቸው ይመስለኛል። የታወቁ ስሜቶች በስዕል፤ በምልክት፤ በጹሁፍ፤ በትይንት፤ በምልክት፤ በደወል፤ በንግግር ሲገለጡ ኖረዋል። እኔ ወደዛ መግባት ብዙም አልፈልግም። ለእኔ ሳብ ያደረገኝ ይህ የማላውቀው ስሜትን የመግለጫ ቋንቋ ማጣቴ ብቻ ሳይሆን ተደብቆ የመቆዬቱ ሚስጢርም ነው። ሚሰጢሩን ፍልፍዬ ማግኘትን በቀጣይነት እሻለሁኝ። የኤርትራን ሰው በማዬቴ እንዳልል ሲዊዝ ራስ እግሩ ኤርትራዊ ነው። በዛ ላይ ከኢትዮጵያዊው ሰው የሚለይበት ምንም ነገር የለም። የልሳናችን የድምጽ አወጣጥ ቅላፄያችን ብቻ ነው ልዩነት ለሚለው ተቀራራቢ ነገ...