ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወረቂ ሳቁ!
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወረቂ ሳቁ!
ከሥርጉተ ሥላሴ 08.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)
„የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሄር
ግን አካሄዱን ያቃናለታል።“
(ምሳሌ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፳)
እንኳን ደስ አለዎት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ። ከታናሽ ወንድመዎት ጋር በድንግልና እና በንጽህና እንዲህ በሰላም፤ በቅንነት እውነተኛ ከሆነው የደም እና የሥጋ ግንኙት በእትብት አሃታዊነት እንኳንም ለመገናኘት አበቃዎት። ዕውነት ለመናገር ከእንዲህ ዓይነት ሰናይ ቀን ጋር ለመገናኘት በመብቃተዎት ዕድለኛ ነዎት።
እንኳን ደስ አለዎት ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ።
ይህችን ቀን ሲጠብቁ ስንቶቹ አለፈዋል። ይህ እንግዲህ በዝምታዎት ውስጥ ያለውን አንድ ጸሎት አሳይቶኛል። መሻተዎትን ፈጣሪ ሰምተዎታል። ቀሪ ጊዜዎትም የሐሴት፤ የሰላም፤ የፍቅር፤ የሳቅ፤ የፈገገታ፤ የውስጥነት እርካታ እንዲሆንለተዎት እምኛለሁኝ። የባከኑ ጊዜዎች ሁሉ ለማማካከስም የግኝኙነቱን መስምር በመጠናከር ተጨማሪ የምሥራችን እንሰዘማ ዘንድ ለዛ ያብቃን ቀሜን! መልካም የውጤት የስኬት የልብ ለልብ ጊዜ።
ከኤርትራ ጋር በጋብቻ ሆነ በማናቸውም ሁኔታ የትውልድ መሠረት የሆኑትን ልጆች የወለዳችሁ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ እናቶች አንኳን ለዚህ ቀን ልዑል እግዚአብሄር አደረሳችሁ አደረሰን።
እንኳን ደስ አለዎት ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ!
ከኤርትራ እና ከኢትዮጵያ የተወለዳችሁ ልጆች ሆይ! እንደገና በመወለዳችሁ እናንተም እንኳን ደስ አላችሁ!
ኤርትራ እና ኢትዮጵያ እንዳይለያዩ አብረው መከራቸውን እንዲታገሡ ልጆቻቸሁን ለገበራችሁ የኢትዮጵያ እናቶች ሆይ! እንኳን ደስ አላችሁ! አንድ ቀን ጀግኖቾቻችን ከወደቁባቸው ቦታዎች ሐውልት እንደሚቆምላቸው አምላካችን ይረዳናል። አሜን!
በኤርትራ መሬት ተውጠው የቀሩ የሰማዕታት ወላጆች ሆይ፤ እህት እና ወንድሞች ሆይ!፤ አጎት እና አክስቶችም ሆይ! ያሳደጋችሁ እናት እና አባቶች ሆይ! ጎበዝ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ውትድርና ሲገቡ እርር ስትሉ የነበራችሁ መምህራን ሆይ! እንኳን ደስ አላችሁ ይህ ቀን ይመጣ ዘንድ ነበር የተደከመው።
በኤርትራም ቢሆን መፍትሄ ይሆናል ብላችሁ የተጋችሁ ነፍሳችሁን ያልሳሳችሁልት ሰማዕታትም እንዲሁ የፍቅር ሙሴ በማጣት የሆነ ነበር እና እንኳንም ለዚህ የሰማዕታት ቀን በጋራ በሚዘከርበት ዕለት አደረሳችሁ አደረስን።
ይህ ቀን ብሄራዊ የሰላም ቀናችን ነው። ይህ ቀን ብሄራዊ የመኖር ቀን ነው። ይህ ቀን ብሄራዊ የነፍስ ቀን ነው። ይህ ቀን ብሄራዊ የመግባባት ቀን ነው። ይህ ቀን የትውልድ ቀን። ለዚህ ቀን ላበቃን ለልዑል እግዚአብሄር ፈጣሪ ክብሩ ይስፋ! ተመስገን።
አንተ ሩቅ ጠበቢ የፍቅር ሐዋርያ ጠቢቡ ቴወድሮስ ቀን ለ ዓንተ ይህቺ ቀን የልደት ቀንህ ነህና ትንቢተኛው ታናሼ ወንድሜ ሆይ! እንኳን ደስ አለህ!
እንኳን ደስ አለን!
በዚህ ዕድሜ ከመሸ ከደስታ ጋር እንዲህ ከፈጣሪ በተላከ የአሮን በትር ምህረት ወርዶ፤ ፍቅር ተበጅቶ፤ ሰላም ተሠርቶ በምንም በምንም በምንም የማይለያይ ህዝብ ከጠላትነትም በከፋ ሁኔታ ይህን ያህል ዘመን ተለያዬን።
የሚያሳዝን ጊዜ ቢሆንም ምላሹ መልካም ነው። ለመልካም ነበር። ማዬት ጥሩ ነው እንዲህ ንጽህናን አምጦ ወልዶ ያስርክባል። ኪሳራ በኪሳራ የተቃጠለው ዘመን ተቀብሮ በፍጹም ቅንነት እና ንጽህና ቀኖቹ በአዲስ መልክ ከዛሬ ጀምሮ ይቆጠራሉ አዲሱ ቀለማም ቀናችን።
ለዚህ ነበር ባለቅኔው ጠ/ ሚር የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ቅዱስ ዮሖንስ አስመራ እንከብራለን ሲሉ ኤርትራም ደግማ ደጋግማ አስባ ወደ ትሩፋቷ ተመልሳ ልዩ የሚያደርጋትን የቀን አቆጠጠሯን ወደ ውስጧ እንድትመልስ አህዱ ለማለት ይመስላል። ትንቢት እና የነብይነት እድምታም ነው።
ይህ ሁሉ የጸጽታቸው ባለቅኔው ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ። የዲጅታል ወራራ የእኛን አልፋ ቤት መለወጥ የሚያስችል የሥልጣኔ አቅም እንደሌለው የገለጹበትን ሊንክ ለጥፈያለሁኝ። የኤርትራ ከዚህ አቅማዊ ብቃት ዕሴቷ መውጣቷ እርር አድርጓቸው ነበር።
Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!
ኤርትራን ቅርቃር ለመስገባት የዲፕሎማሲ ትርፍ ለማስገኝት ሲል ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ያብጠለጠለው የአልጀርሱን ስምምነት ተግራዊ የማድረግ እርምጃን እንደማይሳካላቸው ጠ/ ሚር አብይ አህመድን በርግጠኝነት መግለጹ ብቻ ሳይሆን "ኤርትራን ቅረቃር ለመክተት" የሚለውን ዕስቤ ሰብሮ ግብቶ ሃቁን ያነ ረሧ ፡ይህን ሊንክ በራሱ ይመስለሳዋል፤ ለነገሩ እኔም ሞግቼዎ ነበር ጥሬው ከተለመደው የፖለቲካ ሴራ ጋር እንዳልነበረ እና ባለቅኔው ጠ/ ሚር የሴረኛ ቤተኛ አለመሆናቸውን።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን ለዛ ካሳ ነው ቅዱስ ዮሖንስን አብረን በሥልጣኔ ቀድምትነት ደረጃችን ልክ ማክበር አለብን የሚል የቁጭት ንግግር ያደርጉት የ ኤርትራ ልዑክ ኢትዮጵያ በመጣበት ጊዜ። ኢትዮጵያ በካለንደር ትሩፋቷ ትውቷ ሥልጣኔዋ በዛ ስትቀጥል ኤርትራ ግን ባለመድረጓ ከውስጣቸው ስለነበረ ነው ይህን የገለጹት። ከእኛ ብትለይም እትጌ ኤርትራ ዕሴቷ ግን ውርሷ ትውፊቷ ነው። መጠበቅ አለባት ነበር ዕድምታው።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን ለዛ ካሳ ነው ቅዱስ ዮሖንስን አብረን በሥልጣኔ ቀድምትነት ደረጃችን ልክ ማክበር አለብን የሚል የቁጭት ንግግር ያደርጉት የ ኤርትራ ልዑክ ኢትዮጵያ በመጣበት ጊዜ። ኢትዮጵያ በካለንደር ትሩፋቷ ትውቷ ሥልጣኔዋ በዛ ስትቀጥል ኤርትራ ግን ባለመድረጓ ከውስጣቸው ስለነበረ ነው ይህን የገለጹት። ከእኛ ብትለይም እትጌ ኤርትራ ዕሴቷ ግን ውርሷ ትውፊቷ ነው። መጠበቅ አለባት ነበር ዕድምታው።
የሆነ ሆኖ መለያዬቱ ብቻ ሳይሆን መለያዬቱ እና ጥርጣሬው ተዳምሮ ከዘለቀ ከአብሮነት ይልቅ የዘለቀ ጥላቻ ለልጅ ተውረስ። ዛሬ ያ የውርስ ልዩነት እንሆ በንጹህ ግንኙነት እንደ ገና አህዱ ብሎ ተጀመረ። ኤርትራም ከኢትዮጵያ ተለይታ ያገኘችው እንዳችም ነገር የለም። ትልቁ በዚህ ውስጥ የነበረው መከራ ባህላዊ ዕሴት፤ ሃይማኖታዊ ዕሴት፤ ትውፊታው ዕሴት፤ ትሩፋታዊ ዕሴት፤ ታሪካዊ ዕሴት ሁሉም አይሆኑ ሆነው ነደዱ። ይህ አዲስ ትውልድ የተረከበው የፈረሰ መንፈስን ነበር።
ውዶቼ ቅኖቼ ለመልካም ነገር የተጋችሁት የኔዎቹ … ዛሬ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሐመሌ 7 ቀን 2018 እራሴን ክብድ ብሎኝ ነበር የተነሳሁት። አንግቼ ስለነበር የተኛሁት።
ከጸሎት በፊት እስኪ ምን ሆኖ ይሆን ሰንበት ብዬ አይዋ ዩቱብን ሳይ አዲስ ነገር ተፈጥሯል። ኢትዮ ታይምስ የሚል ዩቱብ የሰጠኝ መረጃ ዕውነት መሆኑን ለማረጋገጥ ከቴሌቪዥን ወደ ኮንፒተሬ አምርቼ ሳተናው ስገባ በትግረኛ ዘጋባ አዳመጥኩኝ። አሁንም አላመንኩም ለማረጋገጥ ዘሃበሻ ስገባ ሌላም መረጃ አገኝሁ።
ሰበር ዜና: ዶ/ር አብይ አስመራ ገቡ
የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት ዕለት ምን ዓይነት ስሜት ሊኖረኝ እንደሚችል አላውቅም ነበር። ባለፈው የኤርትራው ልዑክ አዲስ አባባ ሲጋባ ቦሌ ላይ በነረው ሁኔታ አዲስ ሰው ነበርኩኝ ማለት እችላለሁኝ። ይህን የመሰለ ስሜት ይኖረኛል ብዬ አስቤው አላውቅም ነበር። ምን ያህል በመለያዬታችን ውስጤ የተጎዳ እንደ ነበረ የማላውቀውን ውስጤን ያዳመጥኩት ያን ቀን ነበር። ግን ይህን ያህል እንዲህ ካለ ስሜቴ ጋር ተለያይቼ ሳላውቀው መኖሬን አላውቅም ነበር። ለካንስ ሰው ገጠመኞቹ ካልኖሩ ከበርካታ ከማያውቃቸው ስሜቶች ጋር ነው የሚኖረው የሚለውን አንድ የፍልስፍና ብሄል ያገኘሁት ያን ቀን ነበር። በቀጣይ እስራበታለሁኝ። ለፍቅራዊነት ፕሮጀክቴ ስለሚረዳኝ።
Seregute Selassie YouTube
ዛሬም ያው ስሜት በልጽጎ ተደገመ። የእኔን ትዕዛዝ የማይጠብቁት ሁለቱ የተፈጥሮ መስኮቶች ተከፍተው ኮለል አሉ እንደለመደባቸው ነው። አሁን እዬሄዱ ነው። እንሂድ ካሉ ማን ከልካይ አለባቸው …
ጸሎት አላደረስኩኝም። ይሄው ቀን ጸሎቴ ሆነ። ይሄው ቀን ውዳሴ ማርያሜ ሆነ። ይሄው ቀን ተክለ ትንሳኤዬ ሆነ። በቃ ፈጣሪ የፈቀደው ዕለት ሁሉም እንዲህ ይሆናል። ያ ሁሉ የጥላቻ፤ የመቃቃር፤ የጥርጣሬ ጉም ተገፎ ብርሃን እንደ ለመደባት ወደ 13 ወራቷቿ ወደ አላዛሯ ኢትዮጵያ ቅዱሱን እጆቿን ዘረጋች። „የባድመ ዕድምታ በሥርጉተ ዕይታ“ ጡሁፌም ዘውድ ደፋልኝ። ዘንድሮ ማን እንደ እኔ ጌታ ማሸነፈ ሆነ ሁለመናዬ።
ከዚህ በላይ ቀጥዬ ለመጻፍ ዛሬ አቅም የለኝም። ሻማ መብራት አለበት።
ፈጣሪዬ መመስገን አለበት። የኢትዮጵያ እና የኤርትራ እናቶች ይህን
የሰለም ቀን እንዲያሰቀጥልላቸው፤ እንዲያዘልቅላቸው ለፈጣሪዬ መንገር
አለብኝ። እኔ ደሃ ነኝ። አዎን እኔ ደሃ ነኝ። ግን የመንፈስ ጽናቴ እና በህሊና
ምርት አስተሳቤ ግን ዲታ ነኝ። ስለዚህም ለሁለቱም በጥምረት ዛሬ
እጸልይላቸዋለሁኝ።
ዕንባ፤ ስደት፤ መከራ፤ ጉም ተገፎ ሳቅ - ፍቅር - ፈገግታ መተሳሰብ መረዳዳት ሰው መሆን ይችሉ ዘንድ እንደ ሰው ያስቡ ዘንድ ይጸለያል። የባከነው ትውልድ ጉዳይ አጀንዳዬ ነውና!
Ethiopia: ጠ/ሚ አብይ ዛሬ በጅቡቲ የአለም አቀፍ የንግድ ቀጠና ምርቃት ላይ ንግግር አደረገ
ከትናንት በስትያ ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በጁቡቲ በዓለም አቀፉ የንግድ ቀጠና ምርቃት አከባባር ላይ ንግግር ሲያደርጉ በውስጣቸው መስጥረው የያዟትንም ኤርትራንም አንሰተዋል። „ይህ ደስታ ኢትዮጵያ፤ የሱማሌ፤ የጁቡቲ፤ የሱዳን እና የኤርትራ ነው“ ብለው ነበር። የዛሬውም ደስታ የአፍሪካ፤ የመላው ዓለም እንብርት የሐሴት ቀን ነው። ተመስገን!
- ተጨማሪ ምርኩዝ።
Ethiopia: ዶ/ር አብይ በአስመራ አደባባዮች ሲያልፉ ከህዝቡ የጠበቃቸው ስሜታዊና ደማቅ አቀባበል
Ethiopia: ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በ አስመራ እየተደረገላቸው ያለ አቀባበል
ሰላምን ያፋፋልን! አሜን!
የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ቀን።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ