የቅኔ ማህበርተኝነት እልልታ!

አሥመራ አና ሎሬቱ!


ከሥርጉተ ©ሥላሴ 
08.07.2018
(ከገዳማዊቷ ሲዊዝሻ።)

„ጥቂት መከራ ተቀብለው በብዙ ክብር ይዘጋጃሉ።“
(መጽሐፈ ጥብብ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፭)
  • መነሻ፤

  • Ethiopia: የዶ/ አብይ ታሪካዊ ንግግር በኤርትራ ምድር !!
    (ፕሬዝደንት ኢሳያስን ሳቅ በሳቅ ያደረገው ንግግር)


ዛሬ ኤርትራ አሥመራ ላይ የሆነውን ሁሉ እልልታ ሳይ ታቦቴ የቅኔው ልዑል
ብላቴ ጌታ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን ስንኞቹ እንደምን የውስጥ አና የቀደሙ ነበሩ?የሚለውን በምለሰት ቃኘሁት።
  
ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በትግረኛ የተናገሩት ስለ አስመራ ከተማ የዓለም ቅርስነት፤ ንጽህና፤ ታሪካዊነት ላይ ሰፊ አትኩሮተ ዕድምታ ነበረው። የቅኔ ማህበርተኝነታቸውንም እስኪ ከታቦቴ ሥንኝ ጋር ቃኙት ቅኖቹ። ያው እኔ እምጽፈው ለቅኖች ብቻ ነው። ጎድጓዶች አይጥማቸዋም ቅኝቱ ... 

አሥመራ።
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አሥመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያዬሱ ቢጠራ
የአውራ ጎዳናሽ ጠለላ፤ ሁሉን በአክናፍ እዬጠራ
አሥር ሰዓት ላይ ሲደራ
ለመንገደኛሽ መዝናኛ ሲያጠላ ሲያብብ ሲያፈራ፤
ምነው ሁሉ እንደ አንቺ አሥመራ
አደባባይ ሲያነጥፉ
አድባራት መስኪዱን ካቴድራሉን በዬረድፉ
ገብያውን በየመልኩ እንዳውታር እያሰለፉ
በወግ አዬደረደሩ
በሥምረት እያሰመሩ
በውበት እያደባሩ
እያሳመሩ ቢያደሩ፤
በዬክፍሉ በዬበሩ፣ በዬመልኩ በዬተራ
ፋኑሱን እንደ ደመራ
ቡና ቤቱን እንደ ሦራ
ምነው ሁሉ እንዳ ንቺ አሥመራ
እንደ ከተሞቹ መዲና አቀያዬሱ ቢጠራ።

  • ·       ጣፈ፲፱፶፰ አሥመራ።
  • ·       ከቅኔው እጬጌ ከሎሬቱ እሳት ወይ አበባ መድብል ገጽ 201 የተወሰደ።
  • ·       ስታወሻ።


ብላቴ ከተማዋን እንዳዬድንቀቱን፤ ግራሞቱን ውስጡን መንፈሱን የገለጸበት ጭማቂ የ ዕውቀቱ ሥንኛትን ያቀለሙክት የሃይለ ቃላት ጉልበት ከሥንኛት ጋር እንዴት እንደ ተዋደዱ ለማጠዬቅ ነው። የቅኔው ስዋሰው የብላቴው ሎሬቱ  ነፍስ የፊደላት ቅምረት ብክነት የለበትም። ፊዳላት ቃላትን ሲፈጥሩ እና ሥንኛት ቃላትን ሲፈቅዱ በአቅማቸው ልክ ነው የሚዋቀሩት። ስለዚህም ነው የነፍስ አባቴን የቅኔው ንጉሥ ብላቴ ጸጋዬ ገ/መድህን ቅኔ ጣዕም ልዩ ዜማዊ የሚያደርገው። 

ያለቦታው የሚሠነቀር፤ አላቅሙ የሚንጠለጠል ቃል የለም። ስለዚህም ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት ተዛነፍ የለበትም። የቃላት አደረጃጀት ፍሰቱ ሆነ አወቃቀሩ ማዕድ ተሠሪነታቸው አላቅማቸው የሚሸከሙት የሃላፊነት ጣሪያ የለውም። ሁሉም በልኩ እና በቁመናው ነው በተሟላ ሁኔታ የሚደራጁት የሚተዳደሩት። 

ስለሆነም ለእኔ ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን የቃላት አደራጅም፤ መሪም፤ አዋዳጅም ነው ብዬ ነው የማስበው። እኔ አምልኮተ ጸጋዬ ስላለብኝ አገለለጼ የማይመቻቸው ሊኖሩ ቢችሉም እኔ ግን ሲከፋኝም ሻማዬን አብርቼ እባክህን መድህን ሁነኝ እለዋለሁኝ። እለምነዋለሁኝ። ወጮፎው በግራ በቀኝ ሲበዛብኝ። 


ዓለሞቼ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።